28. ዳን
እስራኤላውያን ምድሯ ከማሸነፋቸው በፊት፣ ሌሼም (ኢያ. ፲፱፥፵፯) ወይም ሌሳ (መሳ. ፲፰፥፯፣ ፲፬) ተብላ የምትጠራ የጥንት የዳን ከተማ። በእዚህ ቦታ የሚገኙት ምንጮች፣ በፊልጶስ ቂሣርያ ከሚገኙት ምንጮች ጋር የዮርዳኖስ ወንዝ ዋና መንጮች ናቸው።
ታላቅ ድርጊቶች፥ አብርሐም ሎጥን አዳነ (ዘፍጥ. ፲፬፥፲፫–፲፮)። የዳን ጎሳዎች ይህን ክልል አሸንፈው ያዙ እናም ዳን ብለው ጠሩት (ኢያ. ፲፱፥፵፯–፵፰)። ኢዮርብዓም ለሰሜን አስር ጎሳዎች መውደቅ ምክንያት የነበረውን የወርቅ ጥጃ ያለው የሀሰት ቤተመቅደስ ሰራ (፩ ነገሥ. ፲፪፥፳፮–፴፫)። ዳን የእስራኤል የሰሜን ከተማ ነው—በዚህም ምክንያት ነው ቅዱሳት መጻህፍት ስለእስራኤል ምድር “ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ድረስ” ብለው ይጠቅሷት ነበር (፪ ዜና ፴፥፭፤ ቤርሳቤህ በደቡብ ጫፍ የምትገኝ ከተማ ነበረች)። (ቅ.መ.መ. ዳን ተመልከቱ።)