10. የቤተመቅደስ ደረጃዎች
የቤተመቅሱ ስፍራ በክፍሎች የተከፋፈለ ነበር፣ እናም የውጪው ክፍል በመሬት የሚገኘው የፎቅ ክፍል ነው። የሚያመልኩት ከበታች ወደ ውጪው ክፍል እና ከእዚያም ወደ ውስጠኛው ክፍል ከሚያስገቡት ከእነዚህ ደረጃዎች በተጨማሪ በተለያዩ በሮች ይገባሉ። ከእግዚአብሔር ልጅ በተጨማሪ፣ ብዙ ሺህ ሰዎች እነዚህን ደረጃዎች ወጥተውባቸዋል። የቲቶ ሰራዊት ቤተመቅደስን በ፸ ዓ.ም. ሲደመስሱት፣ ደረጃዎቹ በተሰባበሩ ነገሮች ተሸፍኖ ነበር። የድሮ የኢየሩሳሌም ከተማ የጥንታዊ ታሪክ በሚያጠኑ ሰዎች በ1970 (እ.አ.አ.) ተቆፍሮ በሚወጣበት ጊዜ እነዚህ ተገልጠው ነበር።
ታላቅ ድርጊቶች፥ ሕዝቅኤል የወደፊት ቤተመቅደስ ምን ያህል ሰፊ እንደሚሆን እና እንደሚመስል በራዕይ አየ (ሕዝ. ፵)። (ቅ.መ.መ. ቤተመቅደስ፣ የጌታ ቤት ተመልከቱ።)