የጥናት እርዳታዎች
24. ቅፍርናሆም


24. ቅፍርናሆም

ፎቶ ፳፬

ቅፍርናሆም፣ በገሊላ ባህር ዳር በሰሜን በኩል የሚገኘው የኢየሱስ የገሊላ አገልግሎት ዋና ቦታ ነው (ማቴ. ፱፥፩–፪ማር. ፪፥፩–፭)። አስፈላጊ እና ውጤታማ የአሳ ማጥመጃና የንግድ ዋና ቦታ የነበረችው፣ የአህዛብ እና የአይሁድ መኖሪያ ነበር። የመጀመሪያው መቶ አመት የህዝብ ብዛት ከ፩ ሺህ በላይ አልነበሩም። ቅፍርናሆም በለማ ቦታ ተከብቦ፣ የአስፈላጊ የንግድ መንገድ የሚገኝበት ነበር። የሮሜ ወታደሮች ገንዳ መታጠቢያ እና ማከማቻ ቦታዎችን በእዚህ ገነቡ። በእዚህ ቦታ ብዙ ተዓምራት ቢፈጸሙም፣ ህዝቡ የአዳኝን አገልግሎት አስወገዱ። ኢየሱስ ስለዚህ ከተማዋን ረገማት (ማቴ. ፲፩፥፳፣ ፳፫–፳፬)። ከጊዜ በኋላም፣ ቅፍርናሆም ተሰባበረች እናም በእዚያ የሚኖሩትም ወጥተው ሄዱ።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ቅፍርናሆም የአዳኝ የእርሱ ከተማ ነበር ተብሎ ይታወቃል (ማቴ. ፱፥፩–፪ማር. ፪፥፩–፭)። በእዚህ ቦታ ብዙ ተዓምራትሰራ። ለምሳሌ፣ ከመቶ አለቃ አገልጋይ (ሉቃ. ፯፥፩–፲)፣ ከጴጥሮስ አማች (ማር. ፩፥፳፩፣ ፳፱–፴፩)፣ በጣራ በኩል መኝታው ከወረደው ሽባ (ማር. ፪፥፩–፲፪)፣ እና እጁ ከሰለለች ሰው (ማቴ. ፲፪፥፱–፲፫) በተጨማሪ ብዙ ሰዎችን ፈወሰ (ማር. ፩፥፴፪–፴፬ )። በዚህም ብዙ እርኩስ መንፈሶችን አስወጣ (ማር. ፩፥፳፩–፳፰፣ ፴፪–፴፬)፣ የኢያኢሮስ ሴት ልጅን ከሞት አስነሳ (ማቴ. ፱፥፲፰–፲፱፣ ፳፫–፳፮ማር. ፭፥፳፪–፳፬፣ ፴፭–፵፫)፣ እና በቅፍርናሆም ምኩራብ የህይወት-እንጀራ የሚለውን ስብከትን ሰጠ (ዮሐ. ፮፥፳፬–፶፱)። አዳኝ ጴጥሮስን ከገሊላ ባህር አሳ እንዲያጠምድ፣ አፉን እንዲከፍት፣ እና ቀረጥ የሚከፍልበት ሳንቲም እንዲያገኝ አዘዘው (ማቴ. ፲፯፥፳፬–፳፯)።