የጥናት እርዳታዎች
29. አቴና


29. አቴና

ፎቶ ፳፱

ከአርዮስፋጎስ (ማርስ ኮረብታ) የተነሳው ይህ ፎቶ በአቴና ውስጥ የተለያዩ ጣዖቶች ማምለኪያ የሚገኝበት የፓርቴኖን ፍራሽ ያሳያል። አቴና የጥንት ግሪክ አቲካ ዋና ከተማ እናም በአዲስ ኪዳን ጊዜዎች ውስጥ የሮሜ የአካይያ ክልል ነበረች። ስሟም የተሰጣት የግሪክ ሴት ጣዖት አቴናን ለማክበር ነበር። በአዲስ ኪዳን ጊዜዎች፣ አቴና የድሮ ታላቅነቷን እና ክብሯን አጥታ ነበር፣ ነገር ግን “ከማይታወቅ አምላክ” በተጨማሪ፣ የብዙ ወንድ እና ሴት ጣዖቶች ሀውልቶች እና ቅርሶች ነበሯት (የሐዋ. ፲፯፥፳፫)።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ሐዋሪያው ጳውሎስ ከተማዋን ጎበኘ እናም በማርስ ኮረብታ ላይ ቆሞ “ስለማይታወቅ አምላክ” ሰበከ (የሐዋ. ፲፯፥፲፭–፴፬)። ሚስዮኖች ከአቴና ወደ ሌሎች የክሪክ ክፍሎች ተልከው ነበር (፩ ተሰ. ፫፥፩–፪)።