8. ኢየሩሳሌም
ከኢየሩሳሌም አልፎ ወደ ሰሜን ሲመለከቱ። በፎቶው መካከለኛ ቦታ ላይ ያለው የአለት ክብ ጣራ ተብሎ የሚጠራው ጣራው በወርቅ የተሸፈነበት የእስላም የተቀደሰ ስፍራ ነው። በጥንት ጊዜ አይሁዶች እዚህ በነበረ ቤተመቅደስ ያመልኩ ነበር። በአለት ክብ ጣራ አጠገብ ያለው ግድግዳ የጥንት የኢየሩሳሌም ከተማን ይከብባል። በግድግዳው በስተቀኝ በኩል፣ በፎቶው ውስጥ የማይታይ፣ የቄድሮን ሸለቆ አለ። ከእዚያም በሚርቅ በስተቀኝ በኩልም የደብረ ዘይት ተራራ አለ። ወደ ሰሜንም፣ ከአለት ክብ ጣራ አልፎ፣ ምናልባት ጎልጎታ ወይም ቀራንዮም ይገኝ ይሆናል።
ታላቅ ድርጊቶች፥በጥንት ጊዜ ሰሌም ተብላ ትጠራ ነበር (መዝ. ፸፮፥፪)። አብርሐርም አስራት ለመልከ ጼዴቅ ከፈለ (ዘፍጥ. ፲፬፥፲፰–፳)። አብርሐም ይስሀቅን ለመሰዋት መጣ (ዘፍጥ. ፳፪፥፪–፲፬)። ዳዊት ኢየሩሳሌምን ከኢያቡሳውያን መልሶ ያዘ (፪ ሳሙ. ፭፥፬–፱)። ንጉስ ሰለሞን ቤተመቅደስን ሰራ (፩ ነገሥ. ፮–፯)። ሌሂ ወደ ቃል ኪዳን ምድር ለመሄድ ወጣ (፩ ኔፊ ፩፥፬፤ ፪)። አዳኝ አገለገለ፣ ለኃጢያት ዋጋ ከፈለ፣ እናም በትንሳኤ ተነሳ (ማቴ. ፳፩–፳፰)። አዳኝ እንደተነበየው፣ ኢየሩሳሌም ከሞተ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ተደመሰሰች (ጆ.ስ.—ማቴ. ፩፥፫–፳)። ኢየሩሳሌም በመጨረሻው ቀናት ትወረራለች (ሕዝ. ፴፰–፴፱፤ ኢዩ. ፪–፫፤ ራዕ. ፲፩፤ ፲፮)። እንደ ዳግም ምፅዓት ድርጊቱ አዳኝ ወደ እዚህ ይመጣል (ዘካ. ፲፪–፲፬፤ ት. እና ቃ. ፵፭፥፵፰–፶፫)። (ቅ.መ.መ. ኢየሩሳሌም፤ ሳሌም ተመልከቱ።)