1. አባይ ወንዝ እና ግብፅ
በአባይ ወንዝ ዳር ያደጉት አትክልቶች። በእንደዚህ አይነት ቦታ፣ የሙሴ እናት ህጻን ወንድ ልጇን ደበቀች። የግብፅ አብዛኛውን ቦታ የሸፈነው በረሀ ከአትክልቶቹ በኋላ ይታያሉ።
ታላቅ ድርጊቶች፥ ምድሩ በግብፅዎስ ተገኝቶ ነበር (አብር. ፩፥፳፫–፳፭)። አብርሐም ወደ ግብፅ ሄደ (ዘፍጥ. ፲፪፥፲–፳፤ አብር. ፪፥፳፩–፳፭)። ጆሴፍ ወደ ግብፅ ተሸጠ፣ መሪ ሆነ፣ እናም ቤተሰቡን ከረሀብ አዳነ (ዘፍጥ. ፴፯፤ ፴፱–፵፮)። የያዕቆብ ትውልዶች በግብፅ ኖሩ (ዘፍጥ. ፵፯፤ ዘፀአ. ፩፤ ፲፪፥፵)። የፈርዖን ሴት ልጅ ህጻኑ ሙሴን በወንዙ ላይ አገኘችው እናም አሳደገችው (ዘፀአ. ፪፥፩–፲)። ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ መርቶ አወጣ (ዘፀአ. ፫–፲፬)። ማርያም፣ ዮሴፍ፣ እና ኢየሱስ ከሄሮድስ ለማምለጥ ለትንሽ ጊዜ ወደ ግብፅ ሄዱ (ማቴ. ፪፥፲፫–፲፭፣ ፲፱–፳፩)። በመጨረሻው ቀናት፣ ግብጻውያን ጌታን ያውቃሉ፣ እናም ጌታ ግብፅን ይባርካል (ኢሳ. ፲፱፥፳–፳፭)። (ቅ.መ.መ. ግብፅ ተመልከቱ።)