30. ቆሮንቶስ
ቆሮንቶስ የሮሜ ክልል አካይያ ዋና ከተማ ነበረች። ፔሎፖነሱስን ከግሪክ ምድር ጋር በሚያገናኝ በምስራቅ እና በምዕራብ በኩል ወደብ ያለው ባህረ ሰላጤ ላይ የምትገኝ ነበረች። የሀብት እና ተፅዕኖ የሚገኝበት የወደብ ከተማ ነበረች።
ታላቅ ድርጊቶች፥ ጳውሎስ ለአንድ አመት ከስድስት ወር በቆሮንቶስ ኖረ እና በእዚህ ቤተክርስቲያኗን መሰረተ (የሐዋ. ፲፰፥፩–፲፰)። ጳውሎስ በቆሮንቶስ አካባቢ ውስጥ ላሉት አባላት ብዙ ደብዳቤዎች ጻፈ፣ ሁለቱም አሁን በአዲስ ኪዳን ውስጥ ናቸው (፩ እና ፪ ቆሮንቶስ)። ለሮሜ የተጻፈው ደብዳቤ ከቆሮንቶስ የተጻፈ ሳይሆን አይቀርም።