የጥናት እርዳታዎች
18. ዶታይን በሰማርያ ውስጥ


18. ዶታይን በሰማርያ ውስጥ

ፎቶ ፲፰

ዶታይን በጉብታና በሸለቆ የሚታወቅ ነው። ይህም ለግጦሽ አመቺ መሬት ነው። እስራኤላውያን በምድሩ ሲሰፍሩ፣ ይህ ክልል ለምናሴ ተሰጥቶ ነበር።

ታላቅ ድርጊቶች፥ በዶታይን ሸለቆ፣ ዮሴፍ ወደ ግብፅ ተሸጠ (ዘፍጥ. ፴፯፥፲፪–፳፰)። ኤልዛቤል የእስራኤል ነቢያትን ለመግደል በሞከረችበት ጊዜ አብድዩ ብዙ መቶ ነቢያትን በዋሻ ውስጥ በመደበቅ አዳነ (፩ ነገሥ. ፲፰፥፲፫)። የሶርያ ሰራዊት ጌታ በተአምራት ያዳነውን ኤልሳዕን እና አገልጋዩን ከበቡ (፪ ነገሥ. ፮፥፲፫–፳፫)።