21. ኢይዝራኤል ሸለቆ
ከታቦር ተራራ በላይ ወደ ኢይዝራኤል ሸለቆ፣ ደግሞም የእስድሬሎን ሜዳ ተብሎ ወደሚታወቀው፣ ወደ ደቡብ በስተምዕራብ የሚመለከት ትእይንት። ምንም እንኳን የኢይዝራኤል ሸለቆ በብዙ ጊዜ ከነበሩት ታላቅ ሸለቆዎች አንዱ እንደሆነ ቢታሰብበትም፣ ይህ የአኮ ሜዳን ከዮርዳኖስ ሸለቆ ጋር እና የገሊላ ባህርን ክልል ጋር የሚያገናኝ ተከታታይ ሸለቆዎች ነው። የመጊዶ ሸለቆ፣ ለምሳሌ፣ በእዚህ ሸለቆ በስተምዕራብ በኩል ነው። የኢይዝራኤል ሸለቆ በምዕራብ በሚገኘው ሜድትሬኒያን ባህር እና በምስራቅ በሚገኘው በዮርዳኖስ ሸለቆ መካከል ቅዱስ ምድርን የሚያልፍ ዋና መንገድ ነው።
ታላቅ ድርጊቶች፥ ግብፅን እና መስጼጦምያን የሚያገናኘው ታላቁ መንገድ በእዚህ ሸለቆ በኩል ያልፋል፣ እናም በእዚህም ብዙ ጦርነቶች ነበሩ (መሳ. ፩፥፳፪–፳፯፤ ፭፥፲፱፤ ፪ ነገሥ. ፳፫፥፳፱–፴)። ታላቁ የመጨረሻው ጦርነት በእዚህ ምድር የሚጀመረው በአርማጌዶን ጦርነት ነው፣ ይህም ከአዳኝ ዳግም ምፅዓት ከአጭር ጊዜ በፊት ይዋጉታል፤ ይህም ስያሜውን ከሀር ማጌዶን ወይም የማጌዶን ተራራ የሚያገኝ ነው (ሕዝ. ፴፰፤ ኢዩ. ፫፥፱–፲፬፤ ዘካ. ፲፬፥፪–፭፤ ራዕ. ፲፮፥፲፬–፲፮)።