የጥናት እርዳታዎች
22. ታቦር ተራራ


22. ታቦር ተራራ

ፎቶ ፳፪

ወደ ሰሜን በስተምስራቅ ወደ ታቦር ተራራ ትእይንት። የታቦር ተራራን የሚከብበው ምድር የኢይዝራኤል ሸለቆ ክፍል ነው፣ ደግሞም የእስድሬሎን ሜዳ ተብሎ ይታወቃል። ናዝሬት ከታቦር ተራራ አጠገብ ከሚገኙ ኮረብታዎች ውስጥ ይገኛል።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ዲቦራ እና ባርቅ የጌታን ሰራዊት በአሶር ንጉስ ኢያቢስን በመቃወም ሰበሰቡ (መሳ. ፬፥፬–፲፬)። የታቦር ተራራ አዳኝ ተቀየረበት ተብሎ በባህል ከሚታመንበት ቦታ አንዱ ነው (ማቴ. ፲፯፥፩–፱)፤ ሌላው የአርሞንዔም ተራራ ነው። (ቅ.መ.መ. መለወጥ ተመልከቱ።)