የጥናት እርዳታዎች
20. ኢዮጴ


20. ኢዮጴ

ፎቶ ፳

ወደ ሰሜን በስተምዕራብ የወደብ ከተማ ወደ ሆነችው ወደ ኢዮጴ ትእይንት።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ዮናስ ወደ ተርሴስ በመርከብ ለመሄድ ወደ ኢዮጴ ሄደ (ዮና. ፩፥፩–፫)። ኢዮጴ በመጀመሪያ ሰለሞን እና በኋላም ዘሩባቤል ከሊባኖስ የጥድ ዛፍ ጫካ ቤተመቅደሱ የሚገነባበት ሳንቃ ለማምጣት ይጠቀምበት የነበረ የባህር ወደብ ነበር (፪ ዜና ፪፥፲፮ዕዝ. ፫፥፯)። በእዚህም ጴጥሮስ ዶርቃ ተብላ የምትታወቀውን ጣቢታን ወደ ህይወት መልሶ አስነሳ (የሐዋ. ፱፥፴፮–፵፫)። ጴጥሮስ ደግሞም በአህዛብ መካከል የመስበክ አስፈላጊነትን የሚገልፅለት ንጹህ እና እርኩስ የሆኑትን እንስሳት ራዕይ አየ (የሐዋ. ፲)። ኦርሰን ሀይድ በ፲፰፻፵፩ (እ.አ.አ.) ቅዱስ ምድርን ለመቀደስ በእዚህ ደረሱ።