7. ቤተ ልሔም
ይህ ፎቶ በፊት ለፊት የሚያዩትን በድንጋይ የተሞሉ ተራራዎችን እና የእረኞች ሜዳዎችን እያሳየ፣ ከኋላም የእዚህ ዘመን የቤተ ልሔም ከተማን ያሳያል።
ታላቅ ድርጊቶች፥ ራሔል ለእዚህ በሚቀርብ ቦታ ነበር የተቀበረችው (ዘፍጥ. ፴፭፥፲፮–፳)። ሩት እና ቦዔዝ በእዚህ ይኖሩ ነበር (ሩት ፩፥፲፱–፪፥፬)። ዳዊት በእዚህ ተወልዶ እና ንጉስ እንዲሆን ተቀብቶ ነበር (፩ ሳሙ. ፲፮፥፩–፲፫)። አዳኝ በእዚህ ተወልዶ እናም እረኞቹና ሰብአ ሰገል እርሱን አምልከውት ነበር (ማቴ. ፪፥፩–፲፩፤ ሉቃ. ፪፥፬–፲፮)። (ቅ.መ.መ. ቤተ ልሔም ተመልከቱ።)