የጥናት እርዳታዎች
26. ፊልጶስ ቂሣርያ


26. ፊልጶስ ቂሣርያ

ፎቶ ፳፮

ፊልጶስ ቂሣርያ የሚገኘው በአርሞንዔም ተራራ ነው። ይህ ምንጭ ከዮርዳኖስ ወንዝ ምንጭ አንዱ ነው። ይህን አካባቢ የሚገዛው ሄሮድስ ፊልጶስ ቂሥርያኑን እና እራሱን ለማክበር በእዚህ ቦታ ከተማ ገነባ፤ ከእዚህ በፊት ከተማው ጳኒያስ ተብሎ ይጠራ ነበር እና አሁን ባኒያስ ወይም ፊልጶስ ቂሣርያ ተብሎ ይጠራል።

ታላቅ ድርጊቶች፥ አዳኝ ከደቀመዛሙርቱ ጋር በፊልጶስ ቂሣርያ ተገናኘ። በእዚህም ጴጥሮስ አዳኝ “ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ” ነው ብሎ አወጀ። አዳኝም ለጴጥሮስ “የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ” ብሎ ቃል ገባለት (ማቴ. ፲፮፥፲፫–፳)።