ክፍል ፻፲፰
በሀምሌ ፰፣ ፲፰፻፴፰፣ በፋር ዌስት ሚዙሪ ውስጥ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል “ጌታ ሆይ፣ አስራ ሁለቱን በሚመለከት ፈቃድህን አሳየን” በሚለው ልመና መልስ የተሰጠበት ራዕይ።
፩–፫፣ ለአስራ ሁለቱ ቤተሰቦች ጌታ ያቀርብላቸዋል፤ ፬–፮፣ በአስራ ሁለቱ ውስጥ ያሉት ክፍት ስፍራዎች ተሞልተዋል።
፩ በእውነት፣ እንዲህ ይላል ጌታ፥ ጉባኤ ወዲያው ይሰብሰብ፤ አስራ ሁለቱም ይደራጁ፤ እና እነዚያን የወደቁትን ክፍተቶች ለሙላት ሰዎች ይመደቡ።
፪ አገልጋዬ ቶማስ ቃሌን ለማተም በፅዮን ለጥቂት ጊዜ ይቆይ።
፫ ከእዚያ ሰአት ጀምሮ የሚቀሩትም በመስበክ ይቀጥሉ፣ እና ይህንንም በልብ ርህራሄ፣ በየዋህነት፣ በትህትና፣ እና በትዕግስት ሁሉ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ቢያደርጉ፣ እኔ ጌታ ለቤተሰቦቻቸው እርዳታ እንደምሰጥ፣ እና ከዚህም ጊዜ የበረከት በር እንደሚከፈትላቸው ቃል እገባላቸዋለሁ።
፬ እና በሚቀጥለውም ጸደይ በታላቅ ውሀዎች ተሻግረው ይሂዱ፣ እና በዚያም ወንጌሌን፣ የእርሱንም ሙላት ያውጁ፣ እና ስለስሜም ምስክርነትን ይስጡ።
፭ በፋር ዌስት ከተማም በሚያዝያ ሀያ ስድስት ቀን ላይ በቤቴ መገንቢያ ስፍራ ላይ ከቅዱሳኔ ተለይተው ይሂዱ፣ ይላል ጌታ።
፮ አገልጋዬ ጆን ቴይለር፣ እና ደግሞም አገልጋዬ ጆን ኢ ፔጅ፣ እና ደግሞም አገልጋዬ ዊልፈርድ ዉድረፍ፣ እና ደግሞም አገልጋዬ ዊለርድ ሪቻርድስ የወደቁትን በእነዚያ ቦታ ክፍተቶቹን እንዲሞሉ ይመደቡ፣ እና መመደባቸውም በህጋዊ መንገድ ይነገራቸው።