ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፳፱


ክፍል ፻፳፱

በየካቲት ፱፣ ፲፰፻፵፫ (እ.አ.አ.) የአገልጋይ መላዕክት እና የመናፍስትን ትክክለኛ ተፈጥሮን ለመለየት የሚቻልበትን ሶስት ታላላቅ ቁልፎች ለማሳወቅ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የሰጣቸው መመሪያዎች።

፩–፫፣ ከሞት የተነሱ እና የመንፈስ አካላት በሰማያት ውስጥ አሉ፤ ፬–፱፣ ከመጋረጃው አልፈው የሚመጡ መልእክተኞችን ለይቶ የማወቂያ ቁልፎች ተሰጥተዋል።

ሁለት አይነት የሰማይ ፍጥረታት አሉ፣ እነርሱም፥ ከሞት የተነሱ ሰዎች፣ የስጋ እና የአጥንት አካል ያሏቸው መላዕክት

ለምሳሌ፣ ኢየሱስ፥ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው።

ሁለተኛ፥ ከሞት ያልተነሱ፣ ነገር ግን ያንን አይነት ክብር የሚወረሱ፣ ፍጹም የሆኑ የጻድቅ ሰዎች መናፍስት

ከእግዚአብሔር መልእክት አለኝ ብሎ መልእክተኛ ሲመጣ፣ እጆቻችሁን ስጡት እና ከእናንተም እጆች ጋር እንዲጨባበጥ ጠይቁት።

መልአክ ከሆነ ይህን ያደርጋል፣ እና እጁንም በመዳደስ ይሰማችኋል።

ፍጹም የሆነ የጻድቅ ሰው መንፈስ ከሆነ በክብሩ ይመጣል፤ ሊመጣም የሚችልበት መንገድ ይህ ብቻ ነውና—

ከእጆቻችሁም ጋር እንዲጨባበጥ ጠይቁት፣ ነገር ግን አይንቀሳቀስም፣ ምክንያቱም ይህ ፍጹም የሆነው ሰው ይታለል ዘንድ ከሰማይ ስርዓት ጋር የሚቃረን ነውና፤ ነገር ግን መልዕክቱን ያበስራል።

ዲያብሎስ በብርሀን መልአክ አምሳል ቢሆን፣ እጆቻችሁንም እንዲጨብጥ ብትጠይቁት እጁንም ይሰጣችኋል፣ እና ምንም ነገር አይሰማችሁም፤ በዚህም ልታውቁት ትችላላችሁ።

እነዚህም ከእግዚአብሔር የመጡ አገልግሎቶች እንደሆኑ ለማወቅ የምትችሉባቸው ሶስት ታላቅ ቁልፎች ናቸው።