ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፳፪


ክፍል ፳፪

ሚያዝያ ፮፣ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በማንችስተር፣ ኒው ዮርክ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህ ራዕይ የተሰጠው ቀደም ብለው የተጠመቁ ሰዎች ቤተክርስቲያኗን ያለዳግም ጥምቀት ለመዋሀድ በመፈለጋቸው ምክንያት ነው።

፣ ጥምቀት አዲስ እና ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን ነው፤ ፪–፬፣ በስልጣን የተከናወነ ጥምቀት ያስፈልጋል።

እነሆ፣ እላችኋለሁ፣ በዚህ ነገር ሁሉም የጥንት ቃልኪዳኖች እንዲሻሩ አድርጌአለሁ፤ ይህ ከመጀመሪያው ጀምሮ የነበረ አዲስ እና ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን ነው።

ስለዚህ፣ ሰው መቶ ጊዜያት ቢጠመቅ ምንም አይጠቅመውም፣ ምክንያቱም በሙሴ ህግም ሆነ በሞተ ስራዎቻችሁ በጠባቡ ደጅ መግባት አትችሉምና።

ልክ እንደጥንቱ፣ ይህ የመጨረሻው ቃል ኪዳን ዳግመኛ እንዲመጣ እና ይህች ቤተክርስቲያን ለእኔ እንድትገነባ ያደረግሁት በሞቱ ስራዎቻችሁ ምክንያት ነው።

ስለዚህ እንዳዘዝኳችሁ በደጃፉ ግቡ፣ እናም አምላካችሁን ለመምከር አትሹ። አሜን።