ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፸፩


ክፍል ፸፩

ታህሳስ ፩፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በሀይረም ኦሀዮ ውስጥ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህን ራዕይ እስከሚቀበል ድረስ ነቢዩ ከጸሀፊው ከስድኒ ሪግደን ጋር መፅሐፍ ቅዱስን መተርጎም ቀጥሎ ነበር፣ በጊዜውም ይህም በዚህ የተሰጣቸውን መመሪያዎች ያሟሉ ዘንድ ትርጉምን ለጥቂት ጊዜ አቁመው ነበር። ቤተክርስቲያኗን የካደው እዝራ ቡዝ በጻፋቸው ደብዳቤዎች ምክንያት በቤተክርስቲያኗ ላይ የነበረውን የጥላቻ ስሜት ለማቃለል ወንድሞች ለመስበክ ሊሄዱ ይገባል።

፩–፬፣ ጆሴፍ ስሚዝ እና ስድኒ ሪግደን ወንጌሉን እንዲያውጁ ተልከዋል፤ ፭–፲፩፣ የቅዱሳኑ ጠላቶችም ያፍራሉ።

እነሆ፣ ለእናንተ አገልጋዮቼ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ እና ስድኒ ሪግደን ጌታ እንዲህ ይላል፣ በእውነትም አንደበታችሁን ከፍታችሁ፣ እንደተሰጣችሁ መንፈስ እና ሀይል፣ እንዲሁም በፈቃዴ ወንጌሌን የምትሰብኩበት፣ የመንግስቱንም ነገሮች፣ ሚስጥራት ከቅዱስ መጻህፍቶች ውስጥ የምታብራሩበት አስፈላጊ እና በእኔም ጠቃሚ መስሎ የሚታይበት ጊዜ መጥቷል።

እውነት እላችኋለሁ፣ በየአካባቢው ላሉት ለአለም እና ለቤተክርስቲያኗም፣ ለአንድ ወቅት፣ እንዲሁም እንድታውቁት እስከሚደረግ ድረስ አውጁ።

በእውነት፣ ይህም የሰጠኋችሁ የወቅቱ ተልዕኮ ነው።

ስለዚህ፣ በወይን ስፍራዬ አገልግሉ። የምድር ኗሪዎችንም ጥሯቸው፣ እናም መስክሩ፣ እናም ለሚመጡት ትእዛዛት እና ራዕዮችም መንገድን አዘጋጁ።

አሁን፣ እነሆ ይህም ጥበብ ነው፤ የሚያነበውም ይረዳው እና ደግሞም ይቀበለውም

ለሚቀበለውም ለእርሱ በብዛት፣ እንዲሁም ሀይል ይሰጠዋልም።

ስለዚህ፣ ጠላታችሁን አሳፍሩ፤ በግልጽ እናም በግል እንዲያገኟችሁ ጥሯቸው፤ እናም ታማኝ ብትሆኑ እፍረታቸው ይገለጣል።

ስለዚህ፣ ብርቱ ማስረጃቸውን በጌታ ላይ ያምጡ።

በእውነትም፣ ጌታ እንዲህ ይላችኋል—በእናንተ ላይ እንዳትበለጽጉ የሚከላከል መሳሪያ አይከናወንም፤

እናም ማንም ሰው በእናንተ ላይ ድምጹን ቢያነሳ እኔ በወሰንኩት ጊዜ ያፍራል።

፲፩ ስለዚህ፣ ትእዛዛቴን ጠብቁ፤ እውነተኛ እና ታማኝ ናቸውና። እንዲሁም ይሁን። አሜን።