ክፍል ፺፩
በመጋቢት ፱፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ነቢዩ በዚህ ጊዜ ብሉይ ኪዳንን በመተርጎም ላይ ነበር። አፖክርፋ በሚባለው የጥንት ፅሁፎች ክፍል ላይ ሲደርስ፣ ጌታን ጠየቀ እና ይህን መመሪያ ተቀበለ።
፩–፫፣ አፖክርፋው በትክክል የተተረጎመ ነው ነገር ግን በውስጡ በሰዎች እጆች እውነት ያልሆኑ ብዙ ተጨማሪዎች ነገሮችን ይይዛል፤ ፬–፮፣ ይህም መንፈስ የበራላቸውን ይጠቅማል።
፩ በእውነት፣ ጌታ አፖክርፋን በሚመለከት እንዲህ ይላል—በውስጡ እውነት የሆኑ አያሌ ነገሮችን ይዟል፣ እና አብዛኛውም በትክክል የተተረጎመ ነው፤
፪ በውስጡ፣ በሰዎች እጆች የተጨመሩ፣ እውነት ያልሆኑ ብዙ ነገሮችም አሉ።
፫ እውነት እላችኋለሁ፣ አፖክርፋው መተርጎሙ አስፈላጊ አይደለም።
፬ ስለዚህ፣ የሚያነበው፣ ይረዳው፣ መንፈስ እውነትን ይገልጣልና፤
፭ እና መንፈስ ያበራለት እርሱም ከዚህ ጥቅም ያገኛል፤
፮ እና በመንፈስ የማይቀበለውም፣ አይጠቀምበትም። ስለዚህ መተርጎሙ አስፈላጊ አይደለም። አሜን።