ክፍል ፻፲፯
በሀምሌ ፰፣ ፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) በፋር ዌስት ሚዙሪ ውስጥ የውልያም ማርክስ፣ የኒዌል ኬ ዊትኒ፣ እና የኦሊቨር ክሬንጀርን ሀላፊነት በሚመለከት ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ።
፩–፱፣ የጌታ አገልጋዮች ምድራዊ ነገሮችን መመኘት የለባቸውም፣ “ለጌታ ንብረት ምኑ ነውና?”፤ ፲–፲፮፣ የነፍስን አሳንሶ ማየትን ይተዉ፣ እና መስዋዕታቸውም ለጌታ የተቀደሰ ይሆናል።
፩ ለአገልጋዬ ዊልያም ማርክስ፣ እና ለአገልጋዬ ኒዌል ኬ ዊትኒ ጌታ እንዲህ ይላል፣ ጉዳዮቻቸውን በፍጥነት ይፈፅሙ እና እኔ ጌታ በምድር ላይ በረዶ ከመላኬ በፊት ከከርትላንድ ምድር ይጓዙ።
፪ ንቁ፣ እና ተነሱ፣ እና ኑ፣ እናም አትዘግዩ፣ እኔ ጌታ ይህን አዝዤአለሁና።
፫ ስለዚህ ቢዘገዩ ከሆኑ መልካም አይሆንላቸውም።
፬ ለኃጢአታቸው ሁሉ፣ እና ለምኞቶቻቸው ሁሉ በፊቴ ንስሀ ይግቡ ይላል ጌታ፤ ለእኔ ንብረት ምኔ ነው? ይላል ጌታ።
፭ የከርትላንድ ንብረቶችም ለእዳ ይተው፣ ይላል ጌታ። ተዉአቸው፣ ይላል ጌታ፣ እና የሚቀረው ማንኛውም በእጆቻችሁ ይቆይ፣ ይላል ጌታ።
፮ የሰማይን አዕዋፋት፣ እና የባህርን አሶች፣ እና የተራራዎቹ እንስሳት የሉኝምን? ምድርን አልሰራሁምን? የአለም ህዝብ ሰራዊት እጣ ፈንታ አልያዝኩምን?
፯ ስለዚህ፣ ብቸኛ ስፍራዎችን እንዲፈኩ እና እንዲያብቡ፣ እና ብዙም እንዲያፈሩ አላደርግምን? ይላል ጌታ።
፰ በአዳም-ኦንዳይ-አማን ተራራ ላይ፣ እና በኦሌያ ሺኔሀ ሜዳ ላይ፣ ወይም አዳም በኖረበት ምድር ብቁ ስፍራ ስለሌለ ነው ጠብታ የሆነውን የምትመኙት፣ እና ከፍተኛ ተፅዕኖ ያላቸውን ጉዳዮች ችላ የምትሉት?
፱ ስለዚህ፣ ወደዚህ ወደ ህዝቤ ምድር፣ እንዲሁም ወደ ፅዮን ኑ።
፲ አገልጋዬ ውልያም ማርክስ በትንሽ ነገሮች ታማኝ ይሁን፣ እና እርሱም በብዙ ነገሮች መሪ ይሆናል። በፋር ዌስት ከተማ ውስጥ በህዝቤ መካከል ይምራ፣ እና በህዝቤ በረከቶችም ይባረክ።
፲፩ አገልጋዬ ኒውል ኬ ዊትኒ ስለ ኒቆላውያንን ስራ እና ስለ ስውር ርኩሰታቸው ሁሉ፣ እና በፊቴ ነፍስን አሳንሶ ማየትን ሁሉ ይፈር፣ ይላል ጌታ፣ እና ወደ አዳም-ኦንዳይ-አማን ምድር ና፣ እና የህዝቤም ኤጲስ ቆጶስ ሁን፣ ይላል ጌታ፣ በስም ብቻ ሳይሆን በተግባር ይሁን፣ ይላል ጌታ።
፲፪ ደግሞም እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ኦሊቨር ግሬንጀርን አስታውሳለሁ፤ እነሆ፣ እውነት እለዋለሁ ስሙ ከትውልድ ወደ ትውልድ፣ ለዘለአለም በቅዱስ መታሰቢያ ይያዛል፣ ይላል ጌታ።
፲፫ ስለዚህ፣ ለቤተክርስቲያኔ ቀዳሚ አመራር ደህንነት በቅንነት ይስራ፣ ይላል ጌታ፤ እና ቢወድቅ ዳግም ይነሳል፣ መስዋዕቱ ለእኔ ከፍሬው በላይ ቅዱስ ነው፣ ይላል ጌታ።
፲፬ ስለዚህ፣ ፈጥኖም ወደዚህ፣ ወደፅዮን ምድር ይምጣ፤ እና በጊዜውም ለህዝቤ ጥቅም በስሜ የሚያተርፍ ይሆናል፣ ይላል ጌታ።
፲፭ ስለዚህ፣ ማንም ሰው አገልጋዬ ኦሊቨር ግሬንጀርን አይጥላው፣ ነገር ግን የህዝቤ በረከቶች በእርሱ ላይ ለዘለአለም ይሁኑ።
፲፮ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በከርትላንድ ምድር ውስጥ ያሉት አገልጋዮቼ ጌታ አምላካቸውን፣ እና ደግሞም ቤቴን እንዲቀድሱ እና እንዲጠብቁ፣ እና የገንዘብ ለዋጮችን በጊዜዬ ይሽሩ ዘንድ ያስታውሱ፣ ይላል ጌታ። እንዲህም ይሁን። አሜን።