ክፍል ፷፪
በነሀሴ ፲፫፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በቻርተን ሚዙሪ ውስጥ፣ በሚዙሪ ወንዝ ዳርቻ ላይ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ከኢንድፐንደንስ ወደ ከርትላንድ በጉዞ ላይ የነበሩት ነቢዩ እና ቡድኖቹ ወደ ፅዮን ምድር የሚጓዙትን ብዙ ሽማግሌዎች ተገናኙአቸው፣ እናም ከደስታ ሰላምታ በኋላ፣ ይህን ራዕይ ተቀበለ።
፩–፫፣ ምስክርነቶች በሰማይ ይመዘገባሉ፤ ፬–፱፣ ሽማግሌዎች ይጓዙ እናም በማመዛዘን እና በመንፈስ እንደተመሩ ይስበኩ።
፩ እነሆ፣ የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች ሆይ፣ እናም አድምጡ፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ፣ እንዲሁም፣ የሰውን ድክመት እና የሚፈተኑትን እንዴት እንደሚረዳቸው የሚያውቅው፣ አማላጃችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ።
፪ እናም በእውነትም አይኖቼ ወደ ፅዮን ምድር ገና ባልተጓዙት ላይ ናቸው፤ ስለዚህ ተልዕኮአችሁ ገና አልተሟላም።
፫ ይሁን እንጂ፣ የተባረካሁ ናችሁ፣ የሰጣችሁት ምስክርነት መላእክት እንዲመለከቱት በሰማይ ተመዝግበዋልና፣ እናም በእናንተም ተደስተዋል፣ እና ለኃጢአታችሁም ይቅርታን አግኝታችኋል።
፬ እና አሁንም ጉዞአችሁን ቀጥሉ። ራሳችሁንም በፅዮን ምድር ሰብስቡ፤ እናም ተሰብሰቡ አብራችኁም ተደሰቱ እና ለልዑሉም ቅዱስ ቁርባንን አቅርቡ።
፭ እና ከዚያም፣ ለእኔ ምንም ልዩነት ስለለው፣ መልካም እንደሚመስላችሁ፣ አዎን፣ እንዲሁም ሁላችሁም በአንድነት፣ ወይም ሁለት በሁለት፣ ተመልሳችሁ ምስክርነታችሁን ስጡ፤ ታማኝም ሁኑ፣ እናም ለምድር ኗሪዎችም፣ ወይም፣ በኃጢአትኞቹ ጉባኤዎች መካከልም የምስራችን ስበኩ።
፮ እነሆ፣ እኔ ጌታ ያገናኘኋችሁ የተስፋ ቃል እንዲሟላ፣ በመካከላችሁ ያሉት ታማኞችም በሚዙሪ አገር ውስጥ እንዲጠበቁ እና እንዲደሰቱ ነው። እኔ ጌታ ለታማኞች የተስፋ ቃል ሰጥቻለሁ እናም ለመዋሸት አልችልም።
፯ እኔ ጌታ ፈቃደኛ ነኝ፣ በመካከላችሁ ማንም በፈረሶች፣ ወይም፣ በበቅሎዎች፣ ወይም በሰረገሎች ለመጓዝ ቢፈልግ ካለው፣ ይህን ከጌታ እጅ ለሁሉም ነገሮች በምስጋና ልብ ቢቀበል፣ ይህን በረከት ይቀበላል።
፰ እነዚህ ነገሮችን በማመዛዘን እና መንፈስም እንደመራቸው በኩል ማድረጋቸው የእነርሱ ፈንታ ነው።
፱ እነሆ፣ መንግስቱ የእናንተ ነውና። እናም እነሆ፣ ዘወትር ከታማኙ ጋር ነኝ። እንዲህም ይሁን። አሜን።