ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻


ክፍል ፻

በጥቅምት ፲፪፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) በፔሪስበርግ ኒው ዮርክ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ለስድኒ ሪግደን የተሰጠ ራዕይ። ሁለቱ ወንድሞች፣ ለብዙ ቀናት ከቤተሰቦቻቸው ተለያይተው ስለነበር፣ ስለእነርሱ አስበው ነበር።

፩–፬፣ ጆሴፍ እና ስድኒ ለነፍሳት ደህንነት ወንጌሉን ይስበኩ፤ ፭–፰፣ የሚናገሩትም በዚያች ሰዓት ይሰጣቸዋል፤ ፱–፲፪፣ ስድኒ ቃል ተቀባይ ይሁን እና ጆሴፍ ገላጭ እና በምስክርም ሀያል ይሁን፤ ፲፫–፲፯፣ ጌታ ንጹህ ህዝብ ያነሳል፣ እና የሚታዘዙም ይድናሉ።

በእውነት ባልንጀሮቼ ስድኒ እና ጆሴፍ፣ ጌታ ለእናንተ እንዲህ ይላል፣ ቤተሰቦቻችሁ ደህና ናቸው፤ በእጆቼም ውስጥ ናቸው፣ እና መልካም እንደሚመስለኝም አደርግባቸዋለሁ በእኔ ሁሉም ሀይል አለና።

ስለዚህ፣ ተከተሉኝ፣ እና የምሰጣችሁንም ምክር አድምጡ።

እነሆ፣ እናም አስተውሉ፣ በዚህ ስፍራ፣ በዚህ ክፍለ ሀገር አካባቢ ብዙ ህዝብ አሉኝ፤ እና ውጤታማ በር በዚህ አካባቢ፣ በዚህ በምስራቅ ምድር ውስጥ ይከፈታል።

ስለዚህ፣ እኔ ጌታ ወደዚህ ስፍራ ትመጡ ዘንድ ፈቀድኩኝ፤ ለነፍሳትም ደህንነት ይህም በእኔ ዘንድ አስፈላጊ ነበርና።

ስለዚህ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ወደ እነዚህ ህዝብ ድምጾቻችሁን ከፍ አድርጉ፤ በልባችሁ የምጨምረውን ሀሳብ ተናገሩ፣ እና በሰዎችም ፊት አታፍሩም፤

የምትናገሩት በዚያች ሰዓት፣ አዎን፣ በዚያች ጊዜም፣ ምን እንደምትናገሩ ይሰጣችኋልና

ነገር ግን የምታውጁትን ማንኛውንም ነገር በስሜ፣ በሁሉም ነገሮች በተረጋጋ ልብ፣ በትሁት መንፈስ ታውጁ ዘንድ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።

እና ይህን የተስፋ ቃል እሰጣችኋለሁ፣ ይህን ስታደርጉ ለምትሉት ማንኛቸውም ነገሮች ሁሉ ምስክር ይሰጣችሁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ይላካል።

እና አንተ አገልጋዬ ስድኒ ለዚህ ህዝብ ቃል ተቀባይ እንድትሆን ፍቃዴ ነው፤ አዎን፣ በእውነትም በዚህ ሀላፊነት፣ እንዲሁም እንደ አገልጋዬ ጆሴፍ ቃል ተቀባይ እንድትሆኑ፣ እሾምሀለሁ።

እና ለእርሱም በምስክር ሀያል እንዲሆን ሀይል እሰጠዋለሁ።

፲፩ እና ቅዱሳን መጻህፍትን ሁሉ ለመዘርዘር ሀያል እንድትሆንም ዘንድ፣ ለእርሱም ቃል ተቀባይ እንድትሆን ዘንድ ሀይልን እሰጥሀለሁ፣ እና በምድር ላይ ስላለችው መንግስቴ ነገሮች በሚመለከት የሁሉም ነገሮች እርግጠኛነትን ታውቅ ዘንድ እርሱም ለአንተ ገላጭ ይሆናል።

፲፪ ስለዚህ፣ በጉዞአችሁ ቀጥሉ እና ልባችሁ ይደሰቱ፤ እነሆ፣ እና አስተውሉ፣ እኔ እስከመጨረሻም ከእናንተ ጋር ነኝና።

፲፫ አሁንም ፅዮንን በተመለከት ቃልን እሰጣችኋለሁ። ምንም እንኳን ለጥቂት ዘመን ብትገሰፅም፣ ፅዮን ትድናለች

፲፬ ወንድሞቻችሁ፣ አገልጋዮቼ ኦርሰን ሀይድ እና ጆን ጉልድ፣ በእጆቼ ውስጥ ናቸው፤ እና ትእዛዛቴን እስከጠበቁ ድረስ ይድናሉ።

፲፭ ስለዚህ፣ ልባችሁ ይፅናኑ፤ በቅንነት ለሚራመዱት፣ እና ለቤተክርስቲያኗ ቅድስ እና ጥቅም ሁሉም ነገሮች አብረው ይሰራሉና።

፲፮ ለራሴም በፅድቅ የሚያገለግሉኝ ንጹህ ህዝብ አስነሳለሁና፤

፲፯ እና የጌታን ስም የሚጠሩት፣ እና ትእዛዛቱን የሚጠብቁ ሁሉ ይድናሉ። እንዲህም ይሁን። አሜን።