ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፳፰


ክፍል ፳፰

በመስከረም ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በፈየት ኒው ዮርክ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት ለኦሊቨር ካውድሪ የተሰጠ ራዕይ። የቤተክርስቲያን አባል የሆነው ሀይረም ፔጅ፣ አንድ የሆነ ድንጋይ ነበረው እናም በዚህ ድንጋይ በመረዳት የፅዮንን ግንባታ በተመለከተ እና የቤተክርስቲያኗን ስርዐት በተመለከተ ራዕይን እንደተቀበለ ተናገረ። በዚህም ብዙ አባላት ተታለሉ፣ እናም ኦሊቨር ካውድሪም መጥፎ ተጽዕኖ አደረበት። ከተቀጠረው ጉባዔ ቀደም ብሎ፣ ነቢዩ ጌታን ስለነገሩ በትጋት ጠየቀው፣ እና ይህም ራዕይ ተከተለ።

፩–፯፣ ጆሴፍ ስሚዝ የሚስጥሩን ቁልፍ ይዟል፣ እናም ለቤተክርስቲያኗ ራዕይ የሚቀበለው እርሱ ብቻ ነው፤ ፰–፲፣ ኦሊቨር ካውድሪ ለላማናውያን ይስበክ፤ ፲፩–፲፮፣ ሰይጣን ሀይረም ፔጅን አታለለው እናም የሀሰት ራእዮችን ሰጠው።

እነሆ፣ እንዲህ እልሀለሁ፣ ኦሊቨርበአጽናኙ የሰጠሁትን ራእዮች እና ትእዛዛትን በተመለከተ የምታስተምራቸው ነገሮች ሁሉ በቤተክርስቲያን እንድትሰማ ለአንተ ይሰጥሀል።

ነገር ግን፣ እነሆ፣ እውነት እውነት እልሀለሁ፣ በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከአገልጋዬ ከጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ በስተቀር ማንም ሰው ትእዛዛትን እና ራእዮችን እንዲቀበል አይሾምም፣ እርሱም እንደ ሙሴ ሁሉ ይቀበላቸዋል።

እና አንተም፣ ልክ እንደ አሮን፣ ለእርሱ ለምሰጣቸውን ነገሮች፣ በእምነት ትዛዛቱን እና ራእዮቹን በኃይል እና በስልጣን ለቤተክርስቲያኗ ለማወጅ ታዛዥ ትሆናለህ።

እናም ለመናገር ወይም ለማስተማር በአጽናኙ ወይም በሁሉም ጊዜ ለቤተክርስቲያኗ በትእዛዝ መልክ ከተመራህ፣ ይህንንም ልታደርገው ትችላለህ።

ነገር ግን በጥበብ እንጂ በትእዛዝ መልክ አትጻፍ፤

እናም የቤተክርስቲያኗ የበላይ እና ከአንተም የበላይ የሆነውን አታዝዘውም፤

ስለሆነም በእርሱ ምትክ ሌላ አስክሾም ድረስ የሚስጥራትን ቁልፎች እና የታተሙትን ራዕዮች ሰጥቼዋለሁ።

እናም፣ እነሆ፣ እልሀለሁ ወደላማናውያን ሄደህ ወንጌሌን ትሰብክላቸዋለህ፤ እናም ትምህርትህን በተቀበሉ መጠን በመካከላቸው ቤተክርስቲያኔን ትመሰርታለህ፤ እናም ራእዬን ትቀበላለህ ነገር ግን በትእዛዝ መልክ አትጻፋቸው።

እናም አሁን፣ እነሆ፣ እልሀለሁ፣ ይህ አልተገለጠም፣ እናም የፅዮን ከተማ የት እንዲሚገነባ ማንም አያውቅም፣ ነገር ግን ከዚህ በኋላ ይሰጣል። እነሆ እልሀለሁ፣ በላማናውያን ድንበር ላይ ይሆናል።

ጉባዔው እስኪፈጸም ድረስ ከዚህ ስፍራ እንዳትሄድ፤ እናም አገልጋዬ ጆሴፍ በጉባኤውም ድምጽ ጉባዔውን እንዲመራ ይሾማል፣ እናም የሚልህን ሁሉ ትናገራለህ።

፲፩ እናም ዳግም፣ ወንድምህን ሀይረም ፔጅን ወስደህ በአንተ እና በእርሱ መካከል ብቻ ከድንጋዩ የጻፈው ነገሮች ከእኔ እንዳልሆኑ እና ሰይጣንም እንዳታለለው ንገረው።

፲፪ ስለሆነም፣ እነሆ እነዚህ ነገሮች ለእርሱ አልተሰጡትም፣ ማናቸውም ነገሮች ቢሆኑ ለማንም የቤተክርስቲያን አባል የቤተክርስቲያኗን ቃል ኪዳን በሚጻረር መልክ አይሰጠውም።

፲፫ ስለሆነም ሁሉም ነገሮች በስራዐት እና በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በጋራ ስምምነት፣ በእምነት ጸሎት መከናወን አለባቸው።

፲፬ እናም በላማናውያን መካከል ከመሄድህ በፊት እንደ ቤተክርስቲያኗ ቃል ኪዳን መሰረት ይህ ነገር እንዲረጋጋ ትረዳለህ።

፲፭ እናም ከምትሄድበት ጊዜ ጀምሮ እስከምትመለስበት ጊዜ ድረስ የምታከናውነው ነገር ይሰጥሀል

፲፮ እናም ወንጌሌን በደስታ ድምጽ በማወጅ በሁሉም ጊዜ አንደበትህን መክፈት ይገባሀል። አሜን።