ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፲፬


ክፍል ፲፬

ሰኔ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በፌየት፣ ኒው ዮርክ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት ለዴቪድ ዊትመር የተሰጠ ራዕይ። በመፅሐፈ ሞርሞን ትርጉም ላይ የዴቪድ ዊትመር ቤተሰቦች የላቀ ፍላጎት አድሮባቸው ነበር። የትርጉሙን ስራ እስኪያጠናቅቅ ድረስ እና በሚመጣው የመጽሐፉ የባለቤትነት መብት በህግ ጥበቃን እስከሚያገኝ ድረስ ነቢዩ መኖሪያውን በፒተር ዊትመር ቀዳማዊ ቤት መስርቶ ነበር። ሶስቱ የዊትመር ወንድ ልጆች፣ እያንዳንዳቸው የስራውን እውነትነት ምስክርነት ስላገኙ፣ የእያንዳንዳቸውን ሀላፊነት በተመለከተ ይበልጥ አሳስቧቸው ነበር። ይህ እና ከዚህ የሚቀጥሉት ሁለቱ ራዕዮች (ክፍል ፲፭ እና ፲፮) የተሰጡት በኡሪም እና ቱሚም አማካይነት ለተጠየቀው መልስ ነበር። በኋላም ዴቪድ ዊትመር ከሶስቱ የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክሮች አንዱ ሆነ።

፩–፮፣ በወይኑ ስፍራ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ደህንነትን ያገኛሉ፤ ፯–፰፣ ከእግዚአብሔር ስጦታዎች ውስጥ ዘለአለማዊ ህይወት ከሁሉም በላይ ታላቅ ነው፤ ፱–፲፩፣ ክርስቶስ ሰማይ እና ምድርን ፈጠረ።

በሰዎች ልጆች መካከል ታላቅ እና ድንቅ ስራ ሊመጣ ነው።

እነሆ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ፈጣን እና ሀያል፣ ሁለት አንደበት ካለው ሰይፍ ይልቅ የተሳለ፣ መገጣጠሚያን እና መቅኔን የሚለየውን ቃሌን አድምጥ፤ ስለዚህ ቃላቴን እድምጥ።

እነሆ፣ የእርሻው ስፍራ ነጭ ሆኖ አዝመራው ዝግጁ ነው፣ ስለዚህ፣ ለነፍሱ ዘለአለማዊ ደህንነትን በእግዚአብሔር መንግስት ያከማች ዘንድ መሰብሰብ የሚሻ በኃይሉ ይጨድ፣ እናም ቀን ሆኑም እያለ ይሰብስብ።

አዎን፣ ማንም የሚያጭድ እናም የሚሰበስብ፣ እርሱ በእግዚአብሔር የተጠራ ነው።

ስለዚህ፣ ብትጠይቀኝ ትቀበላለህ፣ ብታንኳኳም ይከፈትልሀል።

ፅዮንን ወደፊት ለማምጣት እና ለመመስረት ፈልግ። በነገሮች ሁሉ ትእዛዛቴን ጠብቅ።

እናም፣ ትእዛዛቴን ብትጠብቅ እናም እስከመጨረሻው ብትጸና ከእግዚአብሔር ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ስጦታ የሆነውን ዘለአለማዊ ህይወት ይኖርሀል።

እናም እንዲህም ይሆናል፣ ለዚህ ትውልድ ንስሀ ታውጅ ዘንድ እናም ስለምትሰማው እና ስለምታየው ምስክር ሆነህ ትቆም ዘንድ፣ ቃልን የሚሰጥህን መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል በማመን በእምነት በስሜ አባቴን ትጠይቃለህ።

እነሆ፣ ሰማያት እና ምድርንጨለማም ሊጋርደው የማይችል ብርሀንን የፈጠርኩ እኔ የህያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ።

ስለዚህ፣ የወንጌሌን ሙላት ከአህዛብ ወደ እስራኤል ቤት ላመጣ ይገባኛል።

፲፩ እናም እነሆ፣ አንተ ዴቪድ ነህ፣ አንተም ለመርዳት ተጠርተሀል እናም ይህንንም ብታደርግ እና እምነትም ቢኖርህ በጊዜአዊ እና በመንፈሳዊ በረከቶች ትባረካለህ እናም ደመወዝህም ታላቅ ይሆናል። አሜን።