ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፷፯


ክፍል ፷፯

ህዳር መጀመሪያ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በሀይረም ኦሀዮ ውስጥ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። የልዩ ጉባኤ ጊዜ ነበር፣ እናም በነቢዩ በኩል ከጌታ የመጡት ራዕዮች መታተም ተወያይቶ ውሳኔም ተደርሶበት ነበር (የክፍል ፩ ርዕስን ተመልከቱ)። ውልያም ደብሊው. ፌልፕስ የቤተክርስቲያኗን ማተሚያ በኢንድፔንደንስ፣ ምዙሪ መስርቶ ነበር። በጉባኤው ራዕዮችን በ Book of Commandments (መጽሐፈ ትእዛዛት) ለማተም እና ፲ ሺህ ቅጂዎች ለማተም ተወሰነ (ይህም ቀድሞ ባልታወቁ ችግሮች ምክንያት ወደ ፫ ሺህ ተቀንሶ ነበር)። ብዙ ወንድሞችም፣ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነትም እንደተገለጠላቸው፣ በዚያ ጊዜ ለመታተም የተሰበሰቡት ራዕዮች እውነት እንደሆኑ ምስክርነቶችን ሰጥተው ነበር። የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንደመዘገበው ክፍል ፩ ተብሎ የሚታወቀውን ራዕይ ከተቀበለ በኋላ፣ በራዕዮቹ ውስጥ የነበሩት ቃላት ጥቂት ንግግሮች ነበሩባቸው። ይህም ራዕይ ተከተለ።

፩–፫፣ ጌታ የሽማግሌዎችን ጸሎት ይሰማል እናም ይጠብቃቸዋል፤ ፬–፱፣ ከራዕዮቹ ጥቂቱን ክፍል እንዲያባዛለት ከጠቢባን አንዱን ጠየቀ፤ ፲–፲፬፣ ታማኝ ሽማግሌዎች በመንፈስ ህያው ይሆናሉ እናም የእግዚአብሔርንም ፊት ያያሉ።

እናንት የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች፣ በአንድነት የተሰበሰባችሁ፣ ጸሎቶቻችሁን የሰማሁ፣ ልባችሁንም የማውቅ፣ እና ልመናችሁም በፊቴ የሆነው፣ እነሆ እናም አድምጡ።

እነሆ እናም አስተውሉ፣ አይኖቼ በእናንተ ላይ ናቸው፣ እናም ሰማያት እና ምድርም በእጆቼ ውስጥ ናቸው፣ እናም የዘለአለም ሀብትንም እሰጥ ዘንድ የእኔ ናቸው።

ለእናንተ የቀረቡላችሁን በረከቶች ትቀበሉ ዘንድ እንደሚገባችሁ ለእምነታችሁ ተግታችኋል፤ ነገር ግን እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ በልባችሁ ፍርሀት አለ፣ እናም በእውነት የማትቀበሉበት ምክንያቱ ይህ ነው።

እናም አሁን እኔ ጌታ በፊት ለፊታችሁ የተቀመጡት ትእዛዛት እውነት እንደሆኑ ምስክርነትን እሰጣችኋለሁ።

አይኖቻችሁ በአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ ላይ ነበሩ፣ እናም ቋንቋውን ታውቃላችሁ፣ እናም ፍጹም አለመሆኑን ታውቃላችሁ፣ እናም በልባችሁም ከቋንቋው በላይ ለመግለፅ እውቀት እንዲኖራችሁ ፈልጋችሁም ነበር፤ ይህንም ታውቃላችሁ።

አሁን፣ በመፅሐፈ ትእዛዛት ውስጥ፣ እንዲሁም ከመካከሉ ታናሽ የሆነውንም ፈልጉ፣ እናም በመካከላችሁ ከሁሉም በላይ ጠቢብ የሆነውንም ምረጡ፤

ወይም፣ በመካከላችሁ እንደዚህ አንይነት ለመጻፍ የሚችል ማንም ቢኖር፣ ከዚያም እነዚህ እውነት እንደሆኑ አናውቅም በማለታችሁም መልካም አደረጋችሁ፤

ነገር ግን፣ እንደዚህ አይነት አንድም መጻፍ ባትችሉ፣ እውነት እንደሆኑ ባለመመሰከራችሁም ትኮነናላችሁ።

በውስጣቸው ጽድቅ ያልሆነ እንደሌሉ ታውቃላችሁና፣ እናም ፅድቅ የሆነው ከላይ፣ ከብርሀናት አባት ይመጣልና።

እና ዳግም፣ እውነት እላችኋለሁ ይህ እድላችሁ ነው፣ እናም ከቅናት እና ፍርሀት ራሳችሁን ብታርቁ፣ እናም በፊቴም ትሁት ብትሆኑ፣ ወደ አገልግሎቱ እንደተሾማችሁ ቃል ኪዳንን እሰጣችኋለሁ፣ በብቃት ትሁት አይደላችሁምና፣ መጋረጃውም ይገፈፋል እናም አይታችሁኝም እኔ ማን እንደሆንኩም በሰውነት ወይም በስጋዊ አዕምሮ ሳይሆን፣ በመንፈስ ይህን ታውቃላችሁ።

፲፩ በእግዚአብሔር መንፈስ የተነሳሳ ካልሆነ በስተቀር፣ ማንም ቢሆን በስጋ እግዚአብሔርን ያየው አንድስ እንኳ የለም።

፲፪ ማንም ተፈጥሮአዊ ሰው በእግዚአብሔር ፊት፣ በስጋዊ አዕምሮም፣ ይቆም ዘንድ አይችልም።

፲፫ አሁንም በእግዚአብሔር ፊት፣ ወይም የመላእክትን አገልግሎት፣ ትመለከቱ ዘንድ አትችሉም፤ ስለዚህ፣ ፍጹም እስክትሆኑም ድረስ በትዕግስት ፅኑ።

፲፬ አዕምሮዎቻችሁም ወደ ነበሩበት አይመለሱ፤ እናም ብቁ ስትሆኑም፣ በጊዜዬ፣ በአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ እጆች በኩል የተሰጣችሁን ታያላችሁ እናም ታውቃላችሁም። አሜን።