ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፫


ክፍል ፫

ሐምሌ ፲፰፻፳፰ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ ፔንስልቬንያ ውስጥ መፅሐፈ ሌሒ ተብሎ ይጠራ የነበረውን የተተረጎመበት ፻፲፮ የመፅሐፈ ሞርሞን ገጾች የመጀመሪያ ክፍል መጥፋት በተመለከተ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ነቢዩ በቸልተኛነት እነዚህን ገጾች ለጥቂት ጊዜ የመፅሐፈ ሞርሞን ትርጉም ጸሐፊ በመሆን ያገለግል ለነበረው ማርቲን ሀሪስ ኣሳልፎ ሰጠ። ራዕዩ በኡሪምና ቱሚም አማካይነት የተሰጠ ነው። (ክፍል ፲ን ተመልክቱ።)

፩–፬፣ የጌታ ጎዳና አንድ እና ዘለአለማዊ ዙሪያ ነው፤ ፭–፲፭፣ ጆሴፍ ስሚዝ ንስሀ መግባት ወይም የመተርጎም ስጦታውን ማጣት አለበት፤ ፲፮–፳፣ መፅሐፈ ሞርሞን የሌሒ ዘሮችን ለማዳን ይመጣል።

የእግዚአብሔር ስራ፤ ጥበብ፤ እና ዓላማ ሊከሸፍም ሆነ ከንቱ ሊሆን አይችልም።

እግዚአብሔር በተጣመመ መንገድ አይጓዝም፣ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ አይዞርም፣ የተናገረውንም አይለውጥም፣ ስለዚህ መንገዱ ቀጥተኛ ነው፣ ጎዳናውም አንድ እና ዘለአለማዊ ዙሪያ ነው።

አስታውሱ፣ አስታውሱ የሚሰናከለው የሰው ስራ እንጂ የእግዚአብሔር ስራ አይደለም፤

ሰው ብዙ ራዕይ ቢቀበል፣ እናም ብዙ ታላላቅ ነገሮችን ለመስራት ሀይል ቢኖረውም፣ ነገር ግን በራሱ ጥንካሬ ቢታበይ፣ የእግዚአብሔርን ምክር ከንቱ ቢያደርግ እናም በስጋው እና በራሱ ፈቃድ ቢመራ፣ ውድቀትንና የእግዚአብሔርን በቀል በራሱ ላይ ማምጣት አለበት።

እነሆ፣ እነዚህ ነገሮች ተሰጥተውሀል፣ ነገር ግን የተሰጡህ ትእዛዛቶች እንዴት የጠበቁ ነበሩ፤ እናም ካልተላለፍካቸው፣ ለአንተ የተገባልህን የተስፋ ቃላት እንዲሁ አስታውስ።

እናም እነሆ፣ ምን ያህል ጊዜ የእግዚአብሔርን ትእዛዛትና ህግጋት ተላልፈሀል፤ እናም በሰዎችም ሀሳብ ምን ያህል ሄደሀል።

ስለሆነም እነሆ ሰውን ከእግዚአብሔር አስበልጠህ ፍርሀት አልነበረብህም። ምንም እንኳን ሰዎች የእግዚአብሔርን ምክር ከንቱ ቢያደርጉም እናም ቃሉንም ቢንቁ

ነገር ግን ታማኝ መሆን ነበረብህ፤ እናም እጁን ዘርግቶ ከጠላትም ክፉ ፍላፃ ይደግፍህ ነበር፤ እናም በመከራህ ጊዜ ሁሉ ከአንተ ጋር ይገኝ በነበር።

እነሆ አንተ ጆሴፍ ነህ፣ እናም የጌታን ስራ እንድትሰራ ተመርጠሀል፣ ነገር ግን በመተላለፍህ ምክንያት ካልተጠነቀቅህ ትወድቃለህ።

ነገር ግን አስታውስ፤ እግዚአብሔር መሀሪ ነው፤ ከሰጠሁህ ትእዛዛት ተጻራሪ የሆነውን ለሰራህበት ንስሐ ግባ፣ እናም አሁን የተመረጥህ ነህ፣ እናም ለስራው ዳግም ተጠርተሀል፤

፲፩ ይህን ካላደረግህ በቀር፣ ትተዋለህ እናም እንደሌሎችም ሰዎች ትሆናለህ፣ እና ስጦታም አይኖርህም።

፲፪ እናም እግዚአብሔር የሰጥህን የመተርጎም መንፈሣዊ ብርሀንና ሀይል አሳልፈህ በሰጠህ ጊዜ፣ የተቀደሰውን ነገር በኃጢአተኛ ሰው እጅ ውስጥ እንዲገባ አሳልፈህ ሰጥተሀል፣

፲፫ የእግዚአብሔርንም ምክር ከንቱ ላደረገ ሰው፣ እና በእግዚአብሔር ፊት የተደረገውን በጣም የተቀደሱ ቃል ኪዳኖችን ላፈረሰና፣ በራሱ ፍርድ ላይ ለሚመካና በራሱም ጥበብ ለሚታበይ ሰው አሳልፈህ ሰጥተሀል።

፲፬ እናም በዚህ መክንያት ነው ለጊዜው ስጦታህን ያጣኽው—

፲፭ ምክንያቱም የመሪህን ምክር ከመጀመሪያው ጀምሮ እንዲረገጥ አድርገኃልና።

፲፮ ሆኖም፣ ስራዬ ወደፊት ይቀጥላል፣ የአዳኝ እውቀት ወደ አለም በአይሁዶች ምስክርነት እንደመጣ እንዲሁ፣ የአዳኝ እውቀት ወደ ህዝቤ ይመጣል—

፲፯ እንዲሁም ለኔፋውያን፣ እናም ለያዕቆባውያን እናም ለዮሴፋውያን እናም ለዞራማውያን በአባቶቻቸው ምስክርነት ይመጣል—

፲፰ እናም ይህ ምስክርነት በአባቶቻቸው ክፋት ምክንያት እምነት በማጣት ወደመነመኑት፣ ጌታ ወንድሞቻቸው ኔፋውያንን፣ በኃጢአታቸው እና በእርኩስነታቸው የተነሳ፣ እንዲጠፉ ወዳደረጋቸው፣ ወደ ላማናውያን እና ልሙኤላውያን እና እስማኤላውያን እውቀት ይመጣል።

፲፱ በዚህ ዓላማ ምክንያት ነው ጽሁፎቹን የያዘው ይህ ሰሌዳ የተጠበቀው—ጌታ ለህዝቦቹ የገባው የተስፋ ቃል ይፈጸም ዘንድ፤

እናም ላማናውያን ወደ አባቶቻቸው እውቀት ይመጡ ዘንድ፣ እናም የጌታን የተስፋ ቃል ያውቁ ዘንድ፣ እናም ወንጌልንም ያምኑ ዘንድ፣ እናም በኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ስራ ይመኩ ዘንድ፣ እናም በእምነት በስሙ ይከብሩ ዘንድ፣ እናም በንሰሀቸው ይድኑ ዘንድ ነው ሰሌዳው የተጠበቀው። አሜን።