ክፍል ፻፲፭
በሚያዝያ ፳፮፣ ፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) በፋር ዌስት ሚዙሪ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠውን የእዚያን ስፍራና የጌታን ቤት መገንባት በሚመለከት የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያሳውቅ ራዕይ። ይህ ራዕይ ለቤተክርስቲያኗ አመራር ሀላፊዎች እና አባላት የተሰጠ ንግግር ነው።
፩–፬፣ ጌታ ቤተክርስቲያኑን የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ብሎ ጠራ፤ ፭–፮፣ ፅዮን እና ስቴኳ የቅዱሳን መጠበቂያ እና መሸሸጊያ ናቸው፤ ፯–፲፮፣ ቅዱሳን በፋር ዌስት ላይ የጌታን ቤት እንዲገነቡ ታዝዘዋል፤ ፲፯–፲፱፣ ጆሴፍ ስሚዝ የእግዚአብሔርን መንግስትን ቁልፍ በምድር ይዟል።
፩ ለአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ እና ደግሞም ለአገልጋዬ ስድኒ ሪግደን፣ እና ደግሞም ለአገልጋዬ ሀይረም ስሚዝ፣ እና ለተመደቡት ከዚህም በኋላ ለሚመደቡት አማካሪዎቻችሁ በእውነት ጌታ እንዲህ ይላል፤
፪ ደግሞም ለአንተ፣ ለአገልጋዬ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ እና ለአማካሪዎቹ፤
፫ ደግሞም በፅዮን ውስጥ በቤተክርስቲያኔ ከፍተኛ ሸንጎ አባል ለሆናችሁ ታማኝ አገልጋዮቼ፣ እንዲህም ተብሎ ይጠራልና፣ እና በአለም ሁሉ በውጪ ለተበተኑት ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች እና ህዝብ ሁሉ።
፬ በመጨረሻዎቹ ቀናትም ቤተክርስቲያኔ የምትጠራው በዚህ፣ እንዲሁም በየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ስም ነው።
፭ ለሁላችሁም እውነት እላችኋለሁ፥ ለህዝቦች መመሪያ ትሆኑ ዘንድ ተነሱ እና አብሩ፤
፮ እና በፅዮን ምድርና በካስማዎቿ ላይ አብሮ መሰብሰቡ ከአውሎ ነፋስ፣ እና ቁጣም ሳይቀላቀል በምድር ሁሉ ላይ ከሚፈሰው መጠበቂያ እና መሸሸጊያ ይሆን ዘንድ ተነሱ እናም አብሩ።
፯ ከተማው፣ ፋር ዌስት፣ ቅዱስና ለእኔ የተቀደሰ ምድር ይሁን፤ እና ከሁሉም በላይ ቅዱስ ይባላል፣ እናንት የቆማችሁበት ምድር ቅዱስ ነውና።
፰ ስለዚህ፣ ያመልኩኝ ዘንድ ለቅዱሳኔ መሰብሰቢያ እንዲሆን፣ ቤትን ትገነቡልኝ ዘንድ አዝዛችኋለሁ።
፱ እና ለዚህም ስራ መጀመሪያ፣ እና መሰረት፣ እና የማዘጋጃውም ስራ በሚቀጥለው በጋ ይሁን፤
፲ እና መጀመሪያውም በሚቀጥለው ሀምሌ ፬ ቀን ላይ ይሁን፤ እና ከዚያም ጊዜ በኋላ ህዝቤ በስሜ ቤት ይገነቡልኝ ዘንድ በቅንነት ይስሩ፤
፲፩ እና ከዚህ ቀን አንድ አመት በኋላ ለቤቴ መሰረትን መገንባት ዳግም ይጀምሩ።
፲፪ በዚህም ከዚያ ቀን ጀምሮ፣ ከማዕዘን ድንጋዩ እስከ ላይኛው ያለው እስከሚፈጸም፣ ምንም ነገር ሳይቅር ሁሉም እስከሚፈጸም ድረስ በቅንነት ይስሩ።
፲፫ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ጆሴፍ፣ ወይም አገልጋዬ ስድኒ፣ ወይም አገልጋዬ ሀይረም በስሜ ቤት ለመገንባት ተጨማሪ እዳ አይግቡ፤
፲፬ ነገር ግን ለእነርሱ በማሳያቸው ምሳሌ መሰረት ለስሜ ቤት ይሰራ።
፲፭ እና ህዝቤ ለአመራሮቻቸው በማሳየው ምሳሌ መሰረት ባይገነቡት፣ ከእጆቻቸው ይህን አልቀበልም።
፲፮ ነገር ግን ህዝቤ ለአመራሮቻቸው፣ እንዲሁም ለአገልጋዬ ጆሴፍ እና አማካሪዎቹ፣ በማሳያቸው ምሳሌ መሰረት ቢገነቡ፣ ከዚያም ከህዝቤ እጆች ይህን እቀበላለሁ።
፲፯ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ቅዱሳኔ በተሰበሰቡበት የፋር ዌስት ከተማ በፍጥነት መገንባቱ ፍቃዴ ነው።
፲፰ ደግሞም በአካባቢው በሚገኙት ስፍራዎችም፣ ከጊዜ ወደጊዜ በአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ በሚገለጹበት፣ ለካስማዎች ሌሎች ስፍራዎችም ይመደባሉ።
፲፱ እነሆ፣ እኔ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፣ እናም ከህዝቡም ፊት እቀድሰዋለሁና፤ የዚህን መንግስትና አገልግሎት ቁልፎች ሰጥቼዋለሁና። እንዲህም ይሁን። አሜን።