ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፴


ክፍል ፻፴

በሚያዝያ ፪፣ ፲፰፻፵፫ (እ.አ.አ.) በራመስ ኢለኖይ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጡ የመመሪያ ነገሮች።

፩–፫፣ አብና ወልድ ለሰዎች በግል ሊገለጡ ይችላሉ፤ ፬–፯፣ መላዕክት በሰለስቲያል አለም ውስጥ ይኖራሉ፤ ፰–፱፣ ሰለስቲያላዊ ምድር ታላቅ ኡሪምና ቱሚም ትሆናለች፤ ፲–፲፩፣ ወደ ሰለስቲያል አለም ለሚገቡት ሁሉ ነጭ ድንጋይ ተሰጥቷል፤ ፲፪–፲፯፣ የዳግም ምፅዓት ጊዜ ከነቢያት ተሰውሯል፤ ፲፰–፲፱፣ በዚህ ህይወት የተገኘው የመረዳት ችሎታ በትንሳኤ ጊዜ አብሮን ይነሳል፤ ፳–፳፩፣ ሁሉም በረከቶች ህግን በማክበር ይመጣሉ፤ ፳፪–፳፫፣ አብና ወልድ የስጋ እና አጥንት አካል አላቸው።

አዳኛችን በሚገለጥበት ጊዜ እርሱ እንዳለ እናየዋለን። እርሱም እንደ እኛው ሰው እንደሆነም እናያለን።

እና በዚህ በመካከላችን የሚገኘው ማህበራዊ ግንኙነት፣ አሁን የማናገኘውን ነገር ግን ዘለአለማዊ ክብር ተጨምሮበት፣ በዚያም እናገኘዋለን።

ዮሐንስ ፲፬፥፳፫—በዚያ አንቀፅ ውስጥ የአብ እና የወልድ መገለጥ፣ በተናጠል የታዩበት ነው፤ እና አብ እና ወልድ በሰው ልብ ውስጥ ያድራሉ የሚለው አስተሳሰብ የድሮ የሀይማኖት ቡድኖች ሀሳብ ነው፣ እና ሀሰትም ነው።

የእግዚአብሔር ጊዜ፣ የመላዕክት ጊዜ፣ የነቢያት ጊዜ፣ እና የሰው ጊዜ አቆጣጠር እንደየሚኖሩበት ፕላኔት መሰረት አይደለም?—የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ

አዎን ብዬም እመልሳለሁ። ነገር ግን ከዚህ ምድር የሆኑ ወይም የነበሩ ካልሆኑ በስተቀር፣ የሚያገለግሉ መላዕክት አይኖሩም።

መላእክት ይህን ምድር በሚመስል ፕላኔት አይኖሩም።

ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት፣ በመስታወት እና እሳት ባህር አለም ላይ፣ ሁሉም ነገሮች ጥንት፣ አሁን፣ እና ወደ ፊት ለክብራቸው በሚገለጥበት፣ እና ይህም በጌታ ፊት በሚቀጥልበት ሁኔታ ይኖራሉ።

እግዚአብሔር የሚኖርበት ስፍራ ታላቅ ኡሪምና ቱሚም ነው።

ምድር፣ በተቀደሰበት እና ዘለአለማዊ ሁኔታ በጥራት ትሰራለች እና በውስጧም ለሚኖሩት እንደ ኡሪምና ቱሚም ትሆናለች፣ በዚህም የዝቅተኛውን መንግስት፣ ወይም የታችኛው ስርዓት መንግስታትን ሁሉ በሚመለከት ነገሮች ሁሉ በእዚያ ለሚኖሩበት ይገለጥላቸዋል፤ እና ይህች ምድርም የክርስቶስ ትሆናለች።

ከዚያም በራዕይ ፪፥፲፯ ውስጥ የተጠቀሰው ነጭ ድንጋይም አንድ ለሚቀበለው ለእያንዳንዱ ሰው የመንግስት ከፍተኛውን ስርዓትን የሚመለከቱ ነገሮችን እንዲያውቁባቸው የሚደረግበት ኡሪምና ቱሚም ይሆናል፤

፲፩ እና ወደ ሰለስቲያል መንግስት ለሚመጡትም ከሚቀበሉት በስተቀር ማንም የማያውቀው አዲስ ስም የሚጻፍበት ነጭ ድንጋይ ለእያንዳንዱ ተሰጥቷል። አዲሱ ስምም እንደቁልፍ የሆነ ቃል ነው።

፲፪ የሰው ልጅ ከመምጣቱ በፊት ብዙ ደም መፋሰስን የሚያስከትሉ ችግሮች የሚጀምሩት በደቡብ ኬሮላይና እንደሆነ በጌታ አምላክ ስም እተነብያለሁ።

፲፫ ይህም ምናልባት በባሪያ ጥያቄ ይነሳ ይሆናል። በታህሳስ ፳፭፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) ስለዚህ ርዕስ በቅንነት እየጸለይኩ ሳለሁ፣ ይህን ድምፅ አወጀልኝ።

፲፬ በአንድ ወቅት የሰውን ልጅ የምጻት ጊዜ ለማወቅ በቅንነት ስጸልይ ነበር፣ ድምፅም የሚከተለውን ሲደጋግም የሰማሁት፥

፲፭ ልጄ ጆሴፍ፣ ሰማንያ አምስት አመት እስኪሆንህ ብትኖር፣ የሰውን ልጅ ፊት ለማየት ትችላለህ፤ ስለዚህ ይህ ይብቃህ፣ እናም በዚህም ጉዳይ ከዚህ በላይ አታስቸግረኝ።

፲፮ ይህ የተጠቀሰው ምጽአት ስለአንድ ሺህ ዘመን መጀመሪያ ይሁን ወይም ከዚህ በፊት የሆነ መገለጥ ወይም መሞት እንዳለብኝ እና በዚህም ፊቱን የማይ እንደሆነም ለመወሰን ባለመቻል እንደዚህም ተትቼ ነበር።

፲፯ የሰው ልጅ መምጫ ከዚህ ጊዜ በፊት ቀድሞም እንደማይሆን አምናለሁ።

፲፰ በዚህ ህይወት የምናገኘው ማንኛውም የመረዳት ችሎታ መሰረታዊ መርህ፣ ይህም ከሞት ስንነሳ አብሮን ይነሳል።

፲፱ እና አንድ ሰው በትጋቱ እና በታዛዥነቱ ከሌላው ሰው በላይ ተጨማሪ እውቀትን እና የመረዳት ችሎታን በዚህ ህይወት ቢያገኘ፣ በሚመጣው አለምም ውስጥ በበለጠ የተሻለ ሁኔታ ይኖረዋል።

ይህ አለም ከመመስረቱ አስቀድሞ ሁሉም በረከቶች የሚመረኮዙበት በሰማያት ውስጥ ሊሻር የማይችል የታወጀ ህግ አለ—

፳፩ እና የትኛውንም በረከት ከእግዚአብሔር ስናገኝ፣ ሁሉም ነገር በተመረኮዘበት ለዚያ ህግ ታዛዥ በመሆን ነው።

፳፪ አብ እንደ ሰው ሊዳሰስ እና ሊጨበጥ የሚችል የስጋ እና አጥንት አካል አለው፤ ወልድም ደግሞ እንዲሁ ነው፣ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ የስጋ እና አጥንት አካል የለውም፣ ነገር ግን የመንፈስ አካል ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ፣ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ለመኖር ባልቻለ ነበር።

፳፫ ሰው መንፈስ ቅዱስን ሊቀበል ይችላል፤ እና በላዩም ሊወርድበትና አብሮትም ላይቆይ ይችላል።