ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፴፱


ክፍል ፴፱

ጥር ፭፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በፈየት ኒው ዮርክ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት ለጄምስ ኮቪል የተሰጠ ራዕይ። ለአርባ አመታት የሜተዲስት ቄስ የነበረው ጄምስ ኮቪል ጌታ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት የሚሰጠውን ማንኛውንም ትእዛዝ ለማክበር ከጌታ ጋር ቃል ኪዳን ገባ።

፩–፬፣ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ኃይል አላቸው፤ ፭–፮፣ ወንጌልን መቀበል ክርስቶስን መቀበል ነው፤ ፯–፲፬፣ ጄምስ ኮቪል እንዲጠመቅ እና በጌታ የወይን ስፍራ እንዲሰራ ታዘዘ፤ ፲፭–፳፩፣ የጌታ አገልጋዮች ከዳግም ምጽአት በፊት ወንጌልን ይስበኩ ፳፪–፳፬፣ ወንጌልን የሚቀበሉ ለጊዜአዊ እና ለዘለአለም ይሰባሰባሉ።

ከዘለአለም እስከዘለአለም ህያው የሆንኩትን ታላቁ እኔ ነኝን፣ እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስን ድምፅ አድምጥ እናም ስማ—

በጨለማ የሚያበራውን እና በጨለማም ያሉት የማይረዱበት፣ የአለም ብርሀን እና ህይወት የሆነውን፤

በመካከለኛው ዘመን የእኔ ወደሆኑት መጣሁ እና የእኔም የሆኑትም አልተቀበሉኝም፤

ነገር ግን ለተቀበሉኝ ሁሉ ልጆቼ ይሆኑ ዘንድ ኃይልን ሰጠኋቸው፤ እናም ለሚቀበሉኝም እንዲሁ፣ ልጆቼ እንዲሆኑ ኃይልን እሰጣቸዋለሁ።

እናም እውነት፣ እውነት እልሀለሁ፣ ወንጌሌን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እናም ወንጌሌን የማይቀበል እኔን አይቀበልም።

እናም ይህ የእኔ ወንጌል ነው—የንሰሀና የውሀ ጥምቀት፣ እናም በመቀጠል ሁሉን ነገሮችን የሚያሳየውንና የመንግስተ ስማይን ስላማዊ ነገሮችን የሚያስተምረውና አጽናኝ የሆነው፣ የእሳት እና የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ይከተላል።

እናም አሁን፣ እነሆ፣ አገልጋዬ ጄምስ እልሀለሁ፣ ስራዎችህን ተመልክቻለሁ እናም አውቅሀለሁ።

እናም እውነት እልሀለሁ፣ በዚህ ወቅት ልብህ በፊቴ የቀና ነው፤ እናም፣ እነሆ፣ በራስህም ላይ ታላቅ በረከቶችን አድርጌአለሁ፤

ሆኖም፣ በመታበይ እና በአለም ነገሮች ምክንያት ብዙ ጊዜ ስላልተቀበልከኝ፣ ታላቅ መከራን አይተሀል።

ነገር ግን፣ እነሆ፣ ተነሳና ተጠመቅ፣ እናም ስሜንም እየጠራህ ኃጢአቶችህን እጠብ፣ መንፈሴንና የማታውቀውን ታላቅ በረከትን ትቀበላለህ የሚለውን ድምጼንም የምታደምጥ ከሆነ የመዳንህ ቀናት መጥተዋል።

፲፩ እናም ይህን የምታደርግ ከሆነ፣ ለታላቅ ስራ አዘጋጅቼሀለሁ። በዚህ የመጨረሻው ቀናት የላክሁትን የወንጌሌን ሙላት፣ እንዲሁም የእስራኤል ቤት የሆኑትን ህዝቤን እንዲመለሱ ለማድረግ የላክሁትን ቃል ኪዳን ትሰብካለህ።

፲፪ እናም እንዲህም ይሆናል ኃይልም በአንተ ላይ ይሆናል፤ ታላቅ እምነትም ይኖርሀል፣ እናም ከአንተም ጋር እሆናለሁ፣ ከፊትህም እሄዳለሁ።

፲፫ በወይን ስፍራዬም እንድትሰራ፣ እናም ቤተክርስቲያኔን ትገነባ፣ እና በከፍታዎችም ላይ እንድታብብና ሀሴትንም ታደርግ ዘንድ ፅዮንን ለማምጣት ተጠርተሀል።

፲፬ እነሆ፣ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ ወደ ኦሀዮ እንድትሄድ እንጂ፣ ወደ ምስራቅ ሀገሮች እንድትሄድ አልተጠራህም።

፲፭ እናም በኦሀዮ ህዝቤ ራሳቸውን እስካሰባሰቡ ድረስ፣ በሰዎች ልጆች መካከል የማይታወቅን በረከትን አስቀምጫለሁ፣ እናም በራሶቻቸውም ላይ ይፈሳል። ከዚያም ወንዶቹ በህዝብ ሁሉ መካከል ይሄዳሉ።

፲፮ እነሆ፣ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ እጄን በፍርድ በህዝብ ላይ ከማድረግ እንደምቆጠብ በማሰብ፣ በኦሀዮ የሚገኙ ህዝብ በታላቅ እምነት ወደ እኔ ይጣራሉ፣ ነገር ግን ቃሌን አልክድም።

፲፯ ስለዚህ፣ ለመጨረሻም ጊዜ ይገረዝ ዘንድ፣ በታላቅ ኃይልህ ስራህን ጀምር እናም ታማኝ ሰራተኞችን ወደ ወይን ስፍራዬ ጥራ።

፲፰ እናም ንሰሀ እስከገቡና የወንጌሌን ሙላት እስከተቀበሉ እንዲሁም እስከተቀደሱ ድረስ፣ እጄን በፍርድ ከማድረግ እቆጠባለሁ።

፲፱ ስለዚህም፣ ከፍ ባለ ድምጽም፣ መንግስተ ሰማይ ቀርባለች በማለት፥ ሆሳዕና! የልዑል እግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን ብለህ በመጮህ ወደፊት ሂድ።

ለምፅዓቴም ቀን ከፊት ለፊቴ መንገድን በማዘጋጀት፣ በውሀ በማጥመቅ ወደፊት ሂድ፤

፳፩ ጊዜው ተቃርቧልና፤ ቀኑን እና ሰአቱን ማንም ሰው አያውቅም፤ ነገር ግን በእርግጥም ይመጣል።

፳፪ እና እነዚህንም ነገሮች የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እናም ለጊዜውና ለዘለአለም ወደ እኔ ይሰበሰባሉ።

፳፫ እናም ዳግም፣ እንዲህም ይሆናል በውሀ ባጠመቅሀቸው ሁሉ ላይ፣ እጆችህን ትጭናለህ፣ እናም የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ይቀበላሉ፣ እንዲሁም የምጽአቴን ቀን ምልክቶች ይጠባበቃሉ እናም እኔንም ያውቃሉ።

፳፬ እነሆ፣ በቶሎም እመጣለሁ። እንዲህም ይሁን። አሜን።