ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፸፰


ክፍል ፸፰

በመጋቢት ፩፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። በዚያ ቀን ነቢዩ እና ሌሎች መሪዎች የቤተክርስቲያኗን ጉዳይ ለመወያየት ተሰብስበው ነበር። ይህም ራዕይ ነቢዩ፣ ስድኒ ሪግደን፣ እና ኒዌክ ኬ. ውትኒ ወደ ምዙሪ በመጓዝ እና ፅዮንን ለመመስረት እና ድሆችን ለመርዳት ገንዘብ የሚያስገኝ፣ የቤተክርስቲያኗን የንግድ እና የማተም ጥረቶችን የሚረዳ “ድርጅት” እንዲመሰርቱ መመሪያ የሚሰጥ ነበር። ይህም ድርጅት፣ የትብብር ድርጅት ተብሎ የሚታወቀው፣ የተመሰረተው በሚያዝያ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) እና የፈረሰው በ፲፰፻፴፬ (እ.አ.አ.) ነበር (ክፍል ፹፪ን ተመልከቱ)። ከፈረሰ በኋላ፣ በጆሴፍ ስሚዝ አመራር፣ “የድሀውን ህዝቤ የጎተራ ስራዎችን” የሚለው “የንግድ እና የማተሚያ ድርጅት” የሚለውን በራዕይ ውስጥ ቀይሯል፣ እናም “ስርዓት” የሚለው ቃል “ድርጅት” የሚለውን ቃል ተክቷል።

፩–፬፣ ቅዱሳን ጎተራ ማዘጋጀት እና መመስረት ይገባቸዋል፤ ፭–፲፪፣ ንብረቶቻቸውን በጥበብ መጠቀም ወደ ደህንነት ይመራል፤ ፲፫–፲፬፣ ቤተክርስቲያኗ ከምድራዊ ሀይላት ጥገኝነት ነጻ መሆን ይገባታል፤ ፲፭–፲፮፣ ሚካኤል (አዳም) በቅዱሱ (ክርስቶስ) አመራር ያገለግላል፤ ፲፯–፳፪፣ ታማኞች ብጹአን ናቸው፣ ሁሉንም ነገሮች ይወርሳሉና።

ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ እንዲህ ሲል ተናገረው፥ ራሳችሁን የሰበሰባችሁት፣ በቤተክርስቲያኔ ታላቅ ክህነት የተሾማችሁት አድምጡኝ፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ፤

እናም በፊቴ ባቀረባችሁት ነገር ደህንነት ለእናንተ ይሆንላችሁ ዘንድ፣ ከበላይ የሾማችሁን፣ በጆሮአችሁ የጥበብ ቃላትን የሚናገራችሁን የእርሱን ምክር ስሙ፣ ይላል ጌታ አምላክ።

በእውነትም እንዲህ እላችኋለሁ፣ ጊዜው መጥቷል፣ እና አሁንም ተቃርቧል፤ እናም እነሆ፣ እናም ተመልከቱ፣ በዚህ ስፍራ እና በፅዮን ምድርም፣ የድሀውን ህዝቤ የጎተራ ስራዎችን የሚቆጣጠር እና የሚመሰረት የህዝቤ ድርጅት መኖር አለበት—

ይህም ለቤተክርስቲያኔ ቋሚ እና ዘለአለማዊ አመሰራረት እና ስርዓት፣ ራሳችሁ የተቀበላችሁትን ምክንያት ወደፊት ለመግፋት፣ ለሰው ደህንነት እና በሰማይ ላለው ለአባታችሁ ክብር፤

ሰማያዊ ነገሮችን ለማግኘትም፣ እናንተም በሰማያዊ ነገሮች፣ አዎን፣ እናም በምድራዊ ነገሮችም በእኩል እንድትተሳሰሩ ዘንድ ነው።

በምድራዊ ነገሮች እኩል ካልሆናችሁ ሰማያዊ ነገሮችን ለማግኘት እኩል አትሆኑምና፤

በሰለስቲያል አለም ውስጥ ስፍራን እንድሰጣችሁ ከፈለጋችሁ፣ ያዘዝኳችሁን እና የምጠብቅባችሁን ነገሮች በማድረግ ራሳችሁን ማዘጋጀት አለባችሁና።

እናም አሁን፣ ጌታ በእውነት እንዲህ ይላል፣ ሁሉም ነገሮች፣ በእናንተ በዚህ ስርዓት አብራችሁ በተጣመራችሁበት፣ ለእኔ ክብር መደረጋቸው አስፈላጊ ነው፤

ወይም፣ በሌላ ቃላትም፣ አገልጋዬ ኒወል ኬ ውትኒ እና አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ እና አገልጋዬ ስድኒ ሪግደን በፅዮን ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ጋር ይማከሩ፤

አለበለዚያም፣ የተዘጋጁላቸውን ነገሮች ይሰወርባቸውም ዘንድ እና እንዳይገባቸው፣ ሰይጣን ልቦቻቸውን ከእውነቱ ሊያርቀው ይሻልና።

፲፩ ስለዚህ፣ በስምምነት ወይም ሊሰበር በማይችል በዘለአለማዊ ቃል ኪዳን ራሳችሁን እንድታዘጋጁ እና እንድታደራጁ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።

፲፪ እናም ይህን የሚሰብረውም ሹመቱን እና የቤተክርስቲያን ደረጃውን ያጣል፣ እና እስከቤዛ ቀንም በሰይጣን እንዲንገላታ ይሰጣል።

፲፫ እነሆ፣ ይህም እናንተን የማዘጋጅበት ዝግጅት፣ እናም የተሰጣችሁን ትእዛዝ ለማከናወን ትችሉ ዘንድ የምሰጣችሁ መሰረት እና ምሳሌ ነው፤

፲፬ መከራም የሚመጣባችሁ ቢሆን እንኳ፣ በእኔ አሳብ ቤተክርስቲያኗ ከሰለስቲያል አለም በታች ካሉት ሌሎች ፍጥረቶች ሁሉ በላይ ነጻ ሆና ትቆም ዘንድ፤

፲፭ ለተዘጋጀላችሁ አክሊል ትመጡ፣ እና በብዙ መንግስታት ላይ ገዢዎች ትሆኑ ዘንድ የማዘጋጅበት ዝግጅት፣ የምሰጣችሁ መሰረት እና ምሳሌ ነው፣ አዳም-ኦንዳይ-አማንን የመሰረተው ጌታ አምላክ፣ የፅዮን ቅዱስ፤

፲፮ ሚካኤልን እንደ ልኡል የሾመው፣ እናም እግሮቹን ያጸና፣ እናም በከፍታም ላይ ያስቀመጠው፣ እናም የደህንነትን ቁልፎች፣ የቀናት መጀመሪያ እና የህይወት መጨረሻ በሌለው፣ በቅዱሱ ምክር እና አመራር አማካይነት የደህንነትን ቁልፎች የሰጠው ጌታ አምላክም እንዲህ ይላል።

፲፯ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እናንት ትንሽ ልጆች ናችሁ፣ እናም አብ በእጆቹ ምን አይነት ታላቅ በረከቶች እንዳለው እና ለእናንተም እንዳዘጋጀ ገና አልገባችሁም፤

፲፰ እናም ሁሉንም ነገሮች አሁን መሸከም አትችሉም፤ ይህም ቢሆን፣ ተደሰቱ፣ እንደሚገባችሁ እመራችኋለሁና። መንግስት የእናንተ ናት እናም በእዚያም ያሉ በረከቶች የእናንተ ናቸው፣ እናም የዘለአለም ባለጠግነትም የእናንተ ናቸውና።

፲፱ እናም ሁሉንም ነገሮች በምስጋና የሚቀበል እርሱ የከበረ ይሆናል፤ እናም የምድር ነገሮችም፣ እንዲሁም በመቶ እጥፍ፣ አዎን በብዙ፣ ለእርሱ ይጨመሩለታልና።

ስለዚህ፣ ያዘዝኳችሁን ነገሮች እንዲሁ አድርጉ፣ ይላል ቤዛችሁ፣ እንዲሁም እናንተን ከመውሰዱ አስቀድሞ ሁሉንም ነገሮች የሚያዘጋጀው የአህመን ልጅ፤

፳፩ የበኩር ቤተክርስቲያን ናችሁና፣ እናም በደመናው ወደላይ ይወስዳችኋል፣ እናም ለእያንዳንዱም የድርሻውን ይሰጠዋልና።

፳፪ እናም ታማኝ እና ብልህ የሆነ መጋቢው ሁሉንም ነገሮች ይወርሳል። አሜን።