ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፴፯


ክፍል ፻፴፯

በጥር ፳፩፣ ፲፰፻፴፮ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ በቤተመቅደስ ውስጥ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ጊዜውም በዚያ ጊዜ ቤተመቅደስን ለመምረቅ በመዘጋጀት ስርዓቶችን በሚያስተዳድርበት ጊዜ ነበር።

፩–፮፣ ነቢዩ ወንድሙን አልቭንን በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ አየ፤ ፯–፱፣ የሙታን ደህንነት ትምህርት ተገለጠ፤ ፣ ሁሉም ልጆች በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ይድናሉ።

ሰማያት ተከፈቱልን፣ እና የእግዚአብሔርን ሰለስቲያል መንግስትን እና የእዚያን ክብር አየሁ፣ በሰውነት ይሁን ከዚያ ውጪ አላወቅሁም።

በእሳት ነበልባል የተከበበው፣ የዚያ መንግስት ወራሾች የሚገቡበት በር በጣም ታላቅ ውበት እንዳለውም አየሁ።

ደግሞም አብና ወልድ የሚቀመጡበትን በጣም ብሩህ የሆነውን የእግዚአብሔር የክብር ዙፋንንም ተመለከትኩ።

በወርቅ ምንጣፍ አምሳል የሆኑትን የመንግስቱን ውብ መንገዶችንም አየሁ።

አባት አዳምን እና አብርሐምንም፤ እና አባቴና እናቴንም፤ ለብዙ ጊዜ ሞቶ የነበረው ወንድሜ አልቭንንም አየሁ።

እና ጌታ እስራኤልን ዳግም ለመሰብሰብ እጁን ከመዘርጋቱ በፊት ከዚህ ህይወት ሄዶ ስለነበረ፣ እና ለኃጢአት ስርየት ስላልተጠመቀ፣ በዚያ መንግስት ውስጥ እንዴት ውርስ እንዳገኘም ተደነቅሁኝ።

እንዲህም ሲል የጌታ ድምፅ ወደ እኔ መጣ፥ ለመቆየት ቢፈቀድላቸው ይቀበሉት የነበሩት፣ ይህን ወንጌል ባለማወቅ የሞቱት ሁሉ የእግዚአብሔር ሰለስቲያል መንግስት ወራሾች ይሆናሉ።

ደግሞም በሙሉ ልባቸው ይህን ይቀበሉ የነበሩ፣ ካለዚህ እውቀት ከዚህ በኋላ የሞቱት ሁሉ የዚያ መንግስቱ ወራሾች ይሆናሉ፤

እኔ ጌታ ሁሉንም ሰዎች በስራዎቻቸው መሰረት፣ እንደልባቸውም ምኞት እፈርድባቸዋለሁና

እና በተጠያቂነት እድሜም ከመድረሳቸው በፊት የሞቱትን ልጆች ሁሉ በሰማይ ሰለስቲያል መንግስት ውስጥ እንደዳኑም ተመለከትኩኝ።