ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፳፩


ክፍል ፳፩

ሚያዝያ ፮፣ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በፈየት፣ ኒው ዮርክ፣ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ራዕዩ የተሰጠው ቤተክርስቲያኗ በተደራጀችበት ቀን በዴቭድ ዊትመር ቀዳማዊ፣ ቤት ውስጥ ነበር። ቀደም ብለው የተጠመቁት ስድስት ሰዎች ተሳትፈዋል። እነዚህ ሰዎች በአንድ ድምጽ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ለማቋቋም ፍላጎታቸውን እና ውሳኔያቸውን ገልጸዋል (ክፍል ፳ን ተመልክቱ)። ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊን እና ኦሊቨር ካውድሪን እንደ ቤተክርስቲያኗ አመራር ለመቀበል መርጠዋል። እጅ በመጫን ጆሴፍ ኦሊቨርን ለቤተክርስቲያን ሽማግሌነት ሾሞታል ኦሊቨር በተመሳሳይ ሁኔታ ጆሴፍን ሾሞታል። ከቅዱስ ቁርባን ስርዐት በኋላ፣ ጆሴፍ እና ኦሊቨር በእያንዳንዱ ተሳታፊዎች ላይ እጅ በመጫን መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ አድርገዋል እንዲሁም እንደቤተክርስቲያን አባልነት አጽንተዋቸዋል።

፩–፫፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ባለራዕይ፣ ተርጓሚ፣ ነቢይ፣ ኃዋሪያ እና ሽማግሌ እንዲሆን ተጠራ፤ ፬–፰፣ የእርሱም ቃል የፅዮንን መነሻ ይመራል፣ ፱–፲፪፣ አጽናኝ በሆነው ሲናገር የሚናገረውን ቅዱሳን ያምናሉ።

እነሆ፣ በመካከላችሁ መዝገብ ይቀመጣል፤ እናም ባለራዕይ፣ ተርጓሚ፣ ነቢይ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ፣ በእግዚአብሔር በአብ ፈቃድ እና በጌታህ በኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ የቤተክርስቲያኗ ሽማግሌ ተብለህ ትጠራለህ፣

በመንፈስ ቅዱስ በመመራት መሰረቱን ለመጣል በመነሳሳት፣ እናም ወደተቀደሰ እምነት ትገነባው ዘንድ ተጠርተሀል

ቤተክርስቲያኗ በጌታ ዓመት በአስራ ስምንት መቶ ሰላሳኛው ሚያዚያ ተብሎ በሚጠራው አራተኛው ወር በስድስተኛው ቀን ተመሰረተች

ስለዚህ፣ በፈቴ በቅድስና በመራመድ የሚቀበላቸውን ቃላቱን እና ትእዛዛቶቹን እናንት የቤተክርስቲያኗ አባላት ታደምጣላችሁ፤

ቃሉን ልክ ከእኔ አንደበት እንደወጣ አድርጋችሁ ሁሉ ትዕግስት እና እምነት ትቀበላላችሁ።

ምክንያቱም ይህንን ስታደርጉ የሲዖል ደጆችም አያሸንፏችሁም፤ አዎን እናም ጌታ አምላክ የጭለማን ኃይል ከላያችሁ ላይ ይገፋል እናም ለእናንተ ጥቅም እና ለስሙ ክብር ሰማያት እንዲንቀጠቀጡ ያደርጋል።

ጌታ አምላክ እንዲህ ይላል፥ ለአንዴ እና ለመጨረሻ የፅዮንን መሰረት ለማስፋት በታላቅ ኃይል አነሳስቼዋለሁ፣ እናም ትጋቱን አውቃለሁ፣ እንዲሁም ጸሎቱን ሰምቻለሁ።

ለፅዮን የሚያለቅሰውን ልቅሶ ተመልክቼአለሁ፣ እናም ለእርሷ ካሁን በኋላ እንዳያዝን አደርገዋለሁ፣ ለኃጢአቱ ስርየት የሚደሰትበት እና በረከቴ በስራው ላይ የሚገለጥበት ቀን መጥቷል።

ስለሆነም፣ እነሆ፣ በወይኑ ስፍራዬ የሚሰሩትን በታላቅ በረከት እባርካቸዋለሁ፣ እና እነርሱም በኃጢአተኛ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ ለአለም ኃጢአት፣ አዎን፣ ኃጢአት ስርየት ልባቸውን ለሚያዋርዱ እንደተሰቀለ በእኔ በኩል በአጽናኙ በሚሰጡት ቃሉ ያምኑታል።

ስለዚህ በአንተ በሐዋሪያዬ በኦሊቨር ካውድሪ እንዲሾም ፍቃዴ ነው፤

፲፩ በ እሱ እጅ ሽማግሌ ስለሆንክ እርሱ ለአንተ የመጀመሪያ ስለሆነ ስሜን በመሸከም ለዚህች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሽማግሌ ትሆን ዘንድ ይህ ለአንተ ስርዐት ነው።

፲፪ እናም ለቤተክርስቲያኗ ለዚህ ቤተክርስቲያን፣ እናም በአለም ፊት፣ አዎን፣ በአህዛብ ፊት፤ የመጀመሪያ ሰባኪ ትሆን ዘንድ፤ አዎን፣ ለአይሁድም እንዲሁ ሰባኪ ትሆናለህ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። አሜን።