ክፍል ፺፭
በሰኔ ፩፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህ ራዕይ የማምለኪያ እና የመማሪያ ቤት፣ በልዩም የጌታ ቤት፣ እንዲሰሩ ቀጣይ መለኮታዊ መመሪያ የተሰጠበት ነው (ክፍል ፹፰፥፻፲፱–፻፴፮ን ተመልከቱ)።
፩–፮፣ ቅዱሳን የጌታን ቤት ለመስራት ባሳዩት ድክመት ይገሰጻሉ፤ ፯–፲፣ ጌታ ቤቱን በመጠቀም ህዝቡን ከላይ ሀይልን ሊያለብሳቸው ይፈልጋል፤ ፲፩–፲፯፣ ቤቱም የማምለኪያ ቦታ እና ለሐዋርያት ትምህርት ቤት እንዲሆን ይቀደስ።
፩ በእውነት ለምወዳችሁ ለእናንተ ጌታ እንዲህ ይላል፣ እና የምወዳቸውንም ኃጢአታቸውን ለመሰረይ እገስጻቸዋለሁ፣ በቅጣትም ከፈተና በሁሉም ነገሮች የሚድኑበትን መንገድ አዘጋጃለሁና፣ እና ወድጃችኋለሁም—
፪ ስለዚህ፣ በፊቴ መቀጣት እና መገሰፅ ያስፈልጋችኋል፤
፫ ቤቴን ስለመገንባት የሰጠኋችሁን፣ ታላቅ ትእዛዝ በሁሉም ነገሮች ስላላሰባችሁበት፣ አስከፊ የሆነን ኃጢአት በእኔ ላይ ሰርታችኋልና፤
፬ እንግዳ የሆነን ስራዬን አከናውን ዘንድ፣ በሁሉም ስጋ ለባሽ ላይ መንፈሴን አፈስ ዘንድ፣ ሐዋሪያቴን ለመጨረሻ ጊዜ የወይኑ ስፍራዬን እንዲመለምሉ ለማዘጋጀት ያዘጋጀሁት ንድፍ ታላቅ ትእዛዝ በሁሉም ነገሮች አላሰባችሁበትም፤
፭ ነገር ግን እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በመካከላችሁ የጠራኋቸው የተሾሙ ብዙ አሉ ነገር ግን የተመረጡት ጥቂቶች ናቸው።
፮ ያልተመረጡትም በጣም አሳዛኝ ኃጢአት ሰርተዋል፣ በዚያም በቀትርም ጊዜ በጨለማ ይሄዳሉ።
፯ እና ለዚህም ምክንያት ጾማችሁ እና ልቅሶአችሁ፣ ወደ ፀባኦት ጌታ፣ ይህም ሲተረጎም የመጀመሪያው ቀን ፈጣሪ፣ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው ወደሆነው፣ ወደ እርሱ ጆሮዎች ይመጡ ዘንድ የክብር ስብሰባችሁን እንድትጠሩ ትእዛዝን ሰጠኋችሁ።
፰ አዎን፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ቤትን ትገነቡ ዘንድ ትእዛዝ ሰጠኋችሁ፣ በዚህ ቤትም የመረጥኳቸውን ከላይ መንፈሳዊ ስጦታ ልሰጣችሁ አቅጃለሁ፤
፱ ይህም አብ ለእናንተ የሚገባው ቃል ኪዳን ነውና፤ ስለዚህ እንደ ኢየሩሳሌም ሐዋሪያቴ፣ እንድትቆዩ አዛችኋለሁ።
፲ ይህም ቢሆን፣ አገልጋዮቼ በጣም አሳዛኝ ኃጢአትን ሰርተዋል፤ እና በነቢያት ትምህርት ቤትም አለመስማማት ተነስቷል፤ ይህም ለእኔ በጣም አሳዛኝ ነው ይላል ጌታ፤ ስለዚህ እንዲገሰጹ ላኳቸው።
፲፩ እውነት እላችኋለሁ፣ ቤትን እንድትገነቡ ፍቃዴ ነው። ትእዛዛቴን ብታከብሩ ይህን ለመገንባት ሀይል ይኖራችኋል።
፲፪ ትእዛዛቴን ካላከበራችሁ፣ የአብ ፍቅር ከእናንተ ጋር አይቀጥልም፣ ስለዚህ በጭለማ ትሄዳላችሁ።
፲፫ አሁን ይህ ጥበብ፣ እና የጌታ አዕምሮ ነው—በአለም በሚሰሩበት ሳይሆንም፣ ቤት ይሰራ፣ በአለም አይነት ኑሮ እንድትኖሩ አልሰጠኋችሁምና፤
፲፬ ስለዚህ፣ ለዚህ ሀይል ለምትመድቡት እና ለምትሾሙት ለሶስታችሁ በማሳያችሁ ስርዓት ይሰራ።
፲፭ እና በዚህ ውስጠኛ አደባባይም፣ መጠኑ አስራ ሰባት ሜትር ስፋት ይሁን፣ እና ርዝመቱም ሀያ ሜትር ይሁን።
፲፮ እና የውስጠኛው አደባባይ የታች ክፍል ለቅዱስ ቁርባን ለማቅረብ፣ እና ለስብከታችሁ፣ እና ለጾማችሁ፣ እና ለጸሎታችሁ፣ እና ከሁሉም በላይ የሆነውን ፍላጎታችሁን ለምታቀርቡበት ለእኔ ይቀደስ፣ ይላል ጌታ።
፲፯ እና የውስጠኛው አደባባይ ከፍተኛው ክፍልም ለሐዋሪያቴ ትምህርት ቤት ለእኔ ይቀደስ፣ አለ አህመን ልጅ፤ ወይም በሌላ ቃላት አልፈስ፤ ወይም በሌላ ቃላት፣ ኦሜገስ፤ እንዲሁም ጌታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ። አሜን።