ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፺፰


ክፍል ፺፰

በነሀሴ ፮፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህ ራዕይ የመጣው በሚዙሪ ቅዱሳን በመሰደዳቸው ምክንያት ነበር። ተጨማሪ የቤተክርስቲያኗ አባላት በምዙሪ መስፈራቸው፣ በቅዱሳን ቁጥሮች፣ በፖለቲካና በኢኮኖሚ ተፅዕኖአቸው፣ እና በባህልና በሀይማኖት ልዩነቶች ምክንያት ፍርሀት የነበራቸውን አንዳንድ ሌሎች ሰፋሪዎችን ረብሾ ነበር። በሀምሌ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.)፣ አመጸኛ ህዝብ የቤተክርስቲያኗን ንብረት አፈረሱ፣ ሁለት የቤተክርስቲያኗ አባላትን ሬንጅ ቀብተው በላባ ሸፈኑ፣ እናም ቅዱሳን ከጃክሰን አውራጃ ወጥተው እንዲሄዱ በግድ ጠየቁ። ምንም እንኳ በሚዙሪ የነበሩት ችግሮች ዜና ለነቢዩ በከርትላንድ ውስጥ (በዘጠኝ መቶ ማይል ርቀት) እንደደረሰው ምንም ጥርጣሬ ባይኖርም፣ የጉዳዩ አሳሳቢነት በዚህ ቀን ሊታወቀው የሚችለው በራዕይ ብቻ ነበር።

፩–፫፣ የቅዱሳኑ ስቃይ ለጥቅማቸው ይሆናል፤ ፬–፰፣ ቅዱሳን ለሀገሩ ህገ መንግስት ተባባሪዎች ይሁኑ፤ ፱–፲፣ ታማኝ፣ ብልህ፣ እና መልካም ሰዎች በህዝባዊ መንግስት መደገፍ ይገባቸዋል፤ ፲፩–፲፭፣ በጌታ ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ዘለአለማዊ ህይወት ይኖራቸዋል፤ ፲፮–፲፰፣ ጦርነትን አስወግዱ እና ሰላምን አውጁ፤ ፲፱–፳፪፣ የከርትላንድ ቅዱሳን ተገሰጹ እናም ንስሀ እንዲገቡ ታዘዙ፤ ፳፫–፴፪፣ ጌታ በህዝቦቹ ላይ የተጣለባቸውን ስቃይ እና መከራን የሚያስተዳድሩ ህጎቹን ጌታ ገለጠ፤ ፴፫–፴፰፣ ጦርነት ተቀባይነት የሚያገኘው ጌታ ሲያዝዘው ነው፤ ፴፱–፵፰፣ ቅዱሳን፣ ንስሀ ቢገቡ የጌታን በቀል ለማምለጥ ለሚችሉ ጠላቶቻቸውን ይቅርታን ይስጡ።

ባልንጀሮቼ እውነት እላችኋለሁ፣ አትፍሩ፣ ልባችሁ ይፅኑ፤ አዎን፣ ዘወትር ተደሰቱ፣ እና በሁሉም ነገሮች ምስጋናን ስጡ፤

ጌታን በትዕግስት ጠብቁ፣ ጸሎቶቻችሁ ወደፀባኦት ጌታ ጆሮዎች ገብተዋል፣ እናም በዚህ ህትመት እና ምስክር ተመዝግበዋልና—እነዚህም እንዲፈጸሙ ጌታ መሀላ ገብቷል እና አውጇል።

ስለዚህ፣ እንዲሟሉም በማይለወጥ ቃል ኪዳን፣ ይህን የተስፋ ቃል ይሰጣችኋል፤ እና የተሰቃያችሁባቸው ነገሮች ሁሉ ለጥቅማችሁ፣ እና ለክብሬ፣ አብረው ይሰራሉ፣ ይላል ጌታ።

አሁንም፣ ስለምድሩ ህግጋት በእውነትም እላችኋለሁ፣ ህዝቤ የማዝዛቸውን ማንኛቸውንም ነገሮች ሁሉ እንዲያደርጉ ፍቃዴ ነው።

እና መብቶችን እና ልዩ መብቶችን በመጠበቅ የነጻነትን መሰረታዊ መርህ የሚደግፈው፣ ህገ መንግስት የሆነው የምድሩ ህግ ለሰው ዘር ሁሉ ነው፣ እና በፊቴም ተገቢ ነው።

ስለዚህ፣ እኔ ጌታ እናንተና የቤተክርስቲያኔ ወንድሞቻችሁ ለዚያ ለሀገሩ ህገ መንግስት ተባባሪዎች መሆናችሁን ተገቢ አደርጋችኋለሁ፤

የሰው ህግን በሚመለከትም፣ ከዚህ በላይ ወይም በታች የሆነው ከክፉ የሚመጣ ነው።

እኔ ጌታ አምላክ ነጻ አደረኳችሁ፣ ስለዚህ በእርግጥም ነጻ ናችሁ፤ እና ህጉም ነጻ አድርጎአችኋል።

ይህም ቢሆን፣ ክፉው ሲያስተዳድር ህዝቡ ያዝናል።

ስለዚህ፣ ታማኝ ሰዎች እና ብልህ ሰዎች በቅንነት ይፈለጉ፣ እና መልካምና ብልህ ሰዎች ለመደገፍ ፈልጉ፤ አለበለዚያም ከዚህ በታች የሆኑት ማንኛውም ከክፉ የመጣ ነው።

፲፩ እና ከእግዚአብሔር አንደበት ከሚመጣው በእያንዳንዱ ቃል እንድትኖሩ ዘንድ፣ ክፉን ሁሉ እንድትተዉና በጥሩ ነገሮች ላይ እንድትጸኑ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።

፲፪ ታማኝ ለሆነው በሥርዓት ላይ ሥርዓት፣ በትእዛዝም ላይ ትእዛዝ እሰጠዋለሁና፤ እና በዚህም እሞክራችኋለሁ እናም እፈትናችኋለሁም።

፲፫ እና ለእኔ ጉዳይ፣ ለስሜ ህይወቱን የሚሰጥም ዳግም ያገኘዋል፣ እንዲሁም ዘለአለማዊ ህይወትን።

፲፬ ስለዚህ፣ ጠላቶቻችሁን አትፍሩ፣ በቃል ኪዳኔ፣ እስከሞትም ድረስ፣ እንደምትጸኑ፣ ብቁም ሆናችሁ እንድትገኙ፣ በሁሉም ነገሮች እፈትናችሁ ዘንድ በልቤ አውጄዋለሁና፣ ይላል ጌታ።

፲፭ በቃል ኪዳኔ ካልጸናችሁ ለእኔ ብቁ አይደላችሁም።

፲፮ ስለዚህ፣ ጦርነትን አስወግዱና ሰላምንም አውጁ፣ እና የልጆችን ልብ ወደ አባቶች፣ እና የአባቶችንም ልብ ወደ ልጆች ለመቀየር በቅንነት ፈልጉ፤

፲፯ ደግሞም፣ የአይሁዶችን ልብ ወደ ነቢያት፣ እና የነቢያትንም ወደ አይሁዶች፤ አለበለዚያም እመጣና አለምን ሁሉ በእርግማን እመታታለሁ፣ እና በፊቴ ስጋ ለባሽ ሁሉ ይቃጠላል።

፲፰ ልባችሁ አይታወኩ፤ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያዎች አሉ፤ እና ስፍራን አዘጋጅቼላችኋለሁና፤ እናም አባቴ እና እኔ ባለንበት እናንተም ደግሞ ትሆናላችሁ።

፲፱ እነሆ፣ እኔ ጌታ በከርትላንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉት ብዙዎች አልተደሰትኩም፤

ኃጢአታቸውን፣ እና ክፉ መንገዶቻቸውን፣ የልባቸውን ኩራት፣ እና መጎምጀታችን፣ እና ርኵሰታቸውን አይተውም፣ እና የሰጠኋቸውን የጥበብ እና የዘለአለም ቃላትን አይከተሉም።

፳፩ እውነት እላችኋለሁ፣ ንስሀ ባይገቡ እና ያልኳቸውን ማንኛቸውንም ነገሮች ባታደርጉ፣ እኔ ጌታ እገስጻቸዋለሁ እና የፈቀድኩትን ሁሉ አደርጋለሁ።

፳፪ ደግሜም እላችኋልሁ፣ ያዘዝኳችሁን ማንኛቸውንም ነገሮች ብታደርጉ፣ እኔ ጌታ ቁጣን እና ንዴትን ከእናንተ አርቃለሁ፣ እና የሲዖል ደጆችም አያሸንፏችሁም።

፳፫ አሁን፣ ስለቤተሰቦቻችሁ በሚመለከት እናገራችኋለሁ—ሰዎች እናንተን ወይም ቤተሰቦቻችሁን አንዴ ቢመቷችሁ፣ እና በትዕግስት ብትጸኑ እና እነርሱንም ባትሰድቡ ወይም በቀልንም ባታደርጉ፣ ዋጋን ታገኛላችሁ፤

፳፬ ነገር ግን በትዕግስት ባትጸኑ፣ በእናንተ ላይ እንደተመዘነ ትክክለኛ ሚዛን ሆኖ ይቆጠራል።

፳፭ ደግሞም፣ ጠላታችሁ ለሁለተኛ ቢመታችሁ፣ እና ጠላታችሁን ባትሰድቡ፣ እና በትዕግስት ብትጸኑ፣ ዋጋችሁ አንድ መቶ እጥፍ ይሆናል።

፳፮ ደግሞም፣ ለሶስተኛ ጊዜ ቢመታችሁ፣ እና በትዕግስትም ብትጸኑ፣ ዋጋችሁ በአራት እጥፍ ያድጋል፤

፳፯ እና እነዚህ ሶስት ምስክሮችም ንስሀ ባይገባ በጠላታችሁ ላይ ይቆማሉ፣ እናም አይወገዱም።

፳፰ አሁንም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ያ ጠላት ወደ ፍርድ በፊቴ ባለመምጣቱ ከበቀሌ ካመለጠ፣ ዳግም ወደ እናንት ወይም ወደ ቤተሰባችሁ፣ እንዲሁም እስከ ሶስት እና አራት ትውልዶች ልጅ ልጆቻችሁ እንዳይመጣባችሁ በስሜ አስጠንቅቁት

፳፱ ከዚያም፣ በእናንተ ወይም በልጆቻችሁ፣ ወይም እስከ ሶስትና አራት ትውልዶች በልጅ ልጆቻችሁ ከመጣባችሁ፣ ጠላታችሁን በእጆቻችሁ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ።

ከዚያም ካልቀጣችሁት፣ እናንት ደግሞም ልጆቻችሁ እና እስከ ሶስት እና አራት ትውልዶች የልጅ ልጆቻሁም ለፅድቃችሁ ዋጋን ታገኛላችሁ።

፴፩ ይህም ቢሆን፣ ጠላታችሁ በእጆቻችሁ ውስጥ ነው፤ እና በስራው በኩል ዋጋ ከሰጣችሁት ተገቢን ነገር አደረጋችሁ፤ ህይወታችሁን የሚሻ ቢሆን፣ እና ህይወታችሁ በእርሱ አደጋ ላይ ከሆነ፣ ጠላታችሁ በእጆቻችሁ ውስጥ ነው እና ተገቢንም ነገር አደረጋችሁ።

፴፪ እነሆ፣ ይህም ለአገልጋዬ ኔፊ፣ እና ለአባቶቻችሁ፣ ለዮሴፍ፣ እና ያዕቆብ፣ እና ለይስሀቅ፣ እና ለአብርሐም፣ እና ለቀደሙት ነብያቴ እና ሐዋሪያቴ የሰጠሁት ህግ ነው።

፴፫ ደግሞም፣ ከየትኞቹም ሀገሮች፣ ነገዶች፣ ቋንቋዎችና ህዝብ ጋር እኔ ጌታ ካላዘዝኳቸው በስተቀር እንዳይዋጉ ለጥንቶቹ የሰጠሁት ህግ ነው።

፴፬ እና የትኛውም ሀገር፣ ነገድ፣ ወይም ህዝብ በእነርሱ ላይ ጦርነት ቢያውጅ፣ እነርሱ አስቀድመው ለዚያ ህዝብ፣ ሀገር፣ ወይም ቋንቋ የሰላም አርማን ያንሱ፤

፴፭ እና ህዝቦቹ ለሰላም ያቀረቡትን፣ ወይም ሁለተኛውን ወይም ሶስተኛውን፣ ባይቀበሉ፣ እነዚህን ምስክሮች በጌታ ፊት ያምጡ፤

፴፮ ከዚያም እኔ ጌታ ትእዛዝን እሰጣቸዋለሁ፣ እና ከእነዚያ ሀገሮች፣ ቋንቋዎችና ህዝብ ጋር ጦርነትን ቢያደርጉ ድርጊታቸውን ተገቢ ብዬ እቀበለዋለሁ።

፴፯ እና እኔ ጌታ ጦርነታቸውን፣ እና እስከ ሶስት እና አራት ትውልድ፣ የልጆቻቸውን ጦርነት፣ እና የልጅ ልጆቻቸውን ጦርነት፣ በጠላቶቻቸውም ላይ በቀልን እስኪያገኙ ድረስ እዋጋላቸዋለሁ

፴፰ እነሆ፣ ይህም በፊቴ ተገቢ ይሆን ዘንድ ለሁሉም ህዝብ ምሳሌ ነው፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ።

፴፱ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ጠላታችሁ ወደ እናንተ ከመጣ በኋላ ንስሀ ቢገባ እና ለምህረት ወደ እናንተ እየለመነ ቢመጣ፣ ይቅርታ አድርጉለት፣ እና በጠላታችሁም ላይ እንደምስክር አትያዙበት—

እናም እስከ ሁለተኛና ሶስተኛ ድረስም ይቀጥል፤ እና ጠላታችሁ በእናንተ ላይ የተላለፈውን ንስሀ እስከገባለት ድረስ፣ እናንት እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት ይቅር በሉት።

፵፩ እና በመጀመሪያው ከተላለፋችሁ እና ንስሀ ካልገባ፣ ይህም ቢሆን ይቅርታ ስጡት።

፵፪ እና ለሁለተኛ ጊዜ ከተላለፋችሁ፣ እና ንስሀን ባይገባ፣ ይህም ቢሆን ይቅርታን ስጡት።

፵፫ እና ለሶስተኛ ጊዜ ቢተላለፋችሁ፣ እና ንስሀን ባይገባ፣ ደግሞም ይቅርታን ስጡት።

፵፬ ነገር ግን ለአራተኛ ጊዜ ቢተላለፋችሁ ይቅርታ አትስጡት፣ ነገር ግን እነዚህን ምስክሮች በጌታ ፊት አምጡ፤ እና ንስሀ እስከሚገባ ድረስ እና በእናንተ ላይ በተላለፈው ነገሮች ሁሉ በአራት እጥፍ ዋጋ እስከሚሰጣችሁ ድረስ አይደመሰሱም።

፵፭ ይህን ቢያደርግ፣ በሙሉ ልባችሁ ይቅርታን ትሰጡታላችሁ፤ እና ይህን ባያደርግ፣ እኔ ጌታ በጠላታችሁ ላይ በአንድ መቶ እጥፍ እበቀላለሁ

፵፮ እናም በሚጠሉኝ በልጆቹ ላይ፣ እና በልጅ ልጆቹ ላይ ሁሉ፣ እስከ ሶስትና አራት ትውልድ እበቀላለሁ።

፵፯ ነገር ግን፣ ልጆቹ ወይም የልጅ ልጆች ንስሀ ቢገቡ፣ እና በሙሉ ልባቸው እና በሙሉ ሀይላቸው፣ አዕምሮዋቸው፣ እናም ጉልበታቸው ወደ ጌታ ቢመለሱ፣ እና ለተላለፉት መተላለፊያዎች፣ ወይም አባቶቻቸው፣ ወይም የአባቶቻቸው አባቶች ለተላለፉበት ሁሉ በአራት እጥፍ ደግመው ቢመለሱ፣ ከዚያም የእናንተም ቁጣ ይመለስ፤

፵፰ እና በቀልም አይመጣባቸውም፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ፣ እና መተላለፋቸውም በጌታ ፊት እንደ ምስክር በእነርሱ ላይ አይመጡባቸውም። አሜን።