ምዕራፍ ፮
[ህዳር–ታህሳስ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.)]
የአዳም ዘር የመታሰቢያ መፅሐፍን ጻፉ—ጻድቅ ዝርያዎቹ ንስሐን ሰበኩ—እግዚአብሔር ለሔኖክ ራሱን ገለጠ—ሔኖክ ወንጌሉን ሰበከ—የደህንነት እቅድም ለአዳም ተገልጦ ነበር—ጥምቀትንና ክህነትን ተቀበለ።
፩ እናም አዳም የእግዚአብሔርን ድምጽ አደመጠ፣ እና ልጆቹን ንስሐ እንዲገቡ ጠራቸው።
፪ እናም አዳም ሚስቱን እንደገና አወቃት፣ እናም እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች፣ እርሱም ስሙን ሴት ብሎ ጠራው። እና አዳምም የእግዚአብሔርን ስም አከበረ፤ እንዲህም አለ፥ ቃየን በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር ምትክ ዘር ሰጠኝ።
፫ ለሴትም እግዚአብሔር እራሱን ገለጠ፣ እና ሴትም አላመጸም፣ ነገር ግን እንደ ወንድሙ አቤል አይነት ተቀባይነት ያለው መስዋዕትን አቀረበ። ለእርሱም ደግሞ ወንድ ልጅ ተወለደለት፣ እና ስሙንም ሄኖስ አለው።
፬ ከዚያም እነዚህ ሰዎች የጌታን ስም መጥራት ጀመሩ፣ እና ጌታም ባረካቸው።
፭ እናም በአዳም ቋንቋ የተጻፈበት የመታሰቢያ መፅሐፍን ጻፉ፣ ወደ እግዚአብሔር የሚጠሩት ሁሉም በመንፈስ እንዲፅፉ ለመነሳሳት ተሰጥቷቸዋልና።
፮ ንፁህና ያልተበላሸ ቋንቋ ስለነበራቸው፣ ልጆቻቸውም በእነርሱ መጻፍና ማንበብን ተምረዋል።
፯ አሁን ይህም በመጀመሪያ የነበረው ክህነት እስከ አለም መጨረሻም ይኖራል።
፰ አሁን በመንፈስ ቅዱስ ሲነሳሳም ይህን ትንቢት አዳም ተናገረ፣ እና የእግዚአብሔር ልጆች የትውልድ መዝገብም ተጠብቋል። እና ይህም የአዳም የትውልድ ሐረግ መፅሐፍ ነበር፣ እንዲህም ይላል፥ እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረበት ቀን በራሱ በእግዚአብሔር አምሳል አበጀው፤
፱ በእርሱ ሰውነት አምሳል ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፣ እናም ባረካቸው፣ እናም በእግዚአብሔር የእግሩ ማረፊያ በሆነው ምድር ላይ በተፈጠሩበትና ህያው ነፍሶች በሆኑበት ቀንም ስማቸውን አዳም ብሎ ጠራቸው።
፲ አዳምም አንድ መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፣ ልጅንም በአምሳያው እንደ መልኩ ወለደ፤ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው።
፲፩ አዳምም ሴትን ከወለደ በኋላ የኖረው ስምንት መቶ ዓመት ሆነ፣ እና ብዙ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።
፲፪ አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፣ ሞተም።
፲፫ ሴትም አንድ መቶ አምስት ዓመት ኖረ፣ ሄኖስንም ወለደ፣ እናም በእድሜዎቹ በሙሉ ተነበየ፣ እናም ልጁን ሄኖስን ስለእግዚአብሔር መንገድ አስተማረው፤ ስለዚህ ሄኖስም ተነበየ።
፲፬ ሴትም ሄኖስን ከወለደ በኋላ የኖረው ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ሆነ፣ ብዙ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።
፲፭ በምድር ገጽ ላይም የሰው ልጆች ቁጥር በጣም ብዙ ነበር። በእነዚህ ጊዜዎችም ሰይጣን በሰዎች መካከል ታላቅ ስልጣን ነበረው፣ በልባቸውም ቁጣን አነሳሳ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮም ጦርነትቶችና ደም መፋሰስ ሆነ፤ እና በሚስጥር ስራዎች ምክንያት፣ ሀይል በመፈለግ፣ የሰው እጅም በግድያ በወንድሙ ላይ ነበር።
፲፮ ሴትም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አሥራ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
፲፯ ሄኖስ መቶ ዘጠና አመት ኖረ፣ ቃይናንንም ወለደ። ሄኖስና የቀሩት የእግዚአብሔር ሕዝቦችም ሹሎን ከሚባለው አገር ወጡ፣ እና ቃይናን ብሎ በልጁ ስም በጠራበት በቃል ኪዳን ምድር ውስጥ ኖሩ።
፲፰ ሄኖስም ቃይናንን ከወለደ በኋላ የኖረው ስምንት መቶ አሥራ አምስት ዓመት ሆነ፣ ብዙ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ሄኖስ የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምስት ዓመት ሆነ፣ ሞተም።
፲፱ ቃይናንም ሰባ ዓመት ኖረ፣ መላልኤልንም ወለደ፤ ቃይናንም መላልኤልን ከወለደ በኋላ የኖረው ስምንት መቶ አርባ ዓመት ሆነ፣ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ቃይናንም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አሥር ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
፳ መላልኤልም ስልሳ አምስት ዓመት ኖረ፣ ያሬድንም ወለደ፤ መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኋላ የኖረው ስምንት መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። መላልኤልም የኖረበት ዘመን ሁሉ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ሆነ፣ ሞተም።
፳፩ ያሬድም መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ኖረ፣ ሔኖክንም ወለደ፤ ያሬድም ሔኖክን ከወለደ በኋላ የኖረው ስምንት መቶ ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። ያሬድም ለሔኖክ የእግዚአብሔርን መንገድ በሙሉ አስተማረው።
፳፪ ይህም የእግዚአብሔር ልጅ የነበረውና እግዚአብሔር ራሱም ያነጋገረው የአዳም ልጆች ትውልድ መዝገብ ነው።
፳፫ እነዚህም የጽድቅ ሰባኪ ነበሩ፣ እና ተናገሩም ተነበዩም፣ እና በሁሉም ስፍራ ያሉትን ሰዎች ንስሀ እንዲገቡ ጠሩአቸው፤ ለሰው ልጆችም እምነትን አስተማሩ።
፳፬ እንዲህም ሆነ ያሬድም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
፳፭ ሔኖክም መቶ ስልሳ አምስት ዓመት ኖረ፣ ማቱሳላንም ወለደ።
፳፮ እንዲህም ሆነ ሔኖክ በሕዝቦቹ መሀከል በሀገሩ ተጓዘ፤ እየተጓዘም ሳለ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሰማይ ወርዶ አረፈበት።
፳፯ እናም ከሰማይ እንዲህ የሚልን ድምጽ ሰማ፥ ልጄ ሔኖክ፣ ለእነዚህ ህዝቦች ተንብይና እንዲህ በላቸው—ንስሀ ግቡ፣ ጌታ እንዲህ ብሏልና፥ በዚህ ህዝብ እኔ ተቆጥቼአልሁ፣ እናም ሀያሉም ቁጣዬ በእነርሱ ላይ ተቀጣጥላለች፤ ልቦቻቸው ጠጥረዋል፣ ጆሮዎቻቸውም ደንቁረዋል፣ እናም አይኖቻቸውም ወደሩቅ አያዩም፤
፳፰ ከፈጠርኳቸው ጊዜ ጀምሮም ብዙ ትውልዶችም ከእኔ ዞር ብለው ሄደዋል፣ እና እኔንም ክደዋል፣ እና በጭለማም የራሳቸውን ምክር ፈልገዋልና፤ ግድያንም በራሳቸው ፅያፍ ፈጥረዋል፣ እና ለአባታቸው አዳም የሰጠሁትን ትእዛዛትም አላከበሩም።
፳፱ ስለዚህ፣ ራሳቸው በሀሰት ምለዋል፣ እና በመሀላቸውም ሞትን በራሳቸው ላይ አምጥተዋል፤ እና ንስሀ ባይገቡ ሲኦልን አዘጋጅቼላቸዋለሁ።
፴ እና ይህንንም አዋጅ ከምድር መጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ፣ ከመሰረቱ ጀምሮ፣ በራሴ አንደበትና በአገልጋዮቼ በአባቶቻችሁ አንደበት አውጄዋለሁ፣ እንዲሁም እስከ አለም መጨረሻ ጊዜ ድረስም ወደአለም ይላካል።
፴፩ ሔኖክ እነዚህን ቃላት ሲሰማም፣ በጌታ ፊት ወደመሬት ወደቀ፣ እና በጌታ ፊትም እንዲህ በማለት ተናገረ፥ ለምንድን ነው በፊትህ ሞገስን ያገኘሁት፣ እኔም ገና ልጅ ነኝ፣ እና ህዝቦች ሁሉ አይወዱኝም፤ አፌ ኰልታፋ ነውና፤ ስለዚህ እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ?
፴፪ ጌታም ለሔኖክ እንዲህ አለው፥ ሂድና እንዳዘዝኩህ አድርግ፣ እናም ማንም አይጎዳህም። አፍህን ክፈት፣ እናም ይሞላል፣ እኔም የምትናገረውን እሰጥሀለሁ፣ ሁሉም ስጋ ለባሽ በእጄ ላይ ነውና፣ እና መልካም እንደሚመስለኝም አደርጋለሁ።
፴፫ ለእነዚህ ሕዝብ እንዲህ በል፥ የፈጠራችሁን እግዚአብሔር አምላክን ታገለግሉ ዘንድ ዛሬ ምረጡ።
፴፬ እነሆ መንፈሴ በአንተ ላይ አርፏል፣ ስለዚህ ቃላትህን ሁሉ አጸድቃለሁ፤ ተራሮችም ከአንተ ፊት ይሸሻሉ፣ እናም ወንዞችም ከሚሄዱበትም ይዞራሉ፤ አንተም ከእኔ ጋር ሁን፣ እና እኔም ከአንተ ጋር፤ ስለዚህ ከእኔ ጋር ተራመድ።
፴፭ እና ጌታ ለሔኖክ ተናገረ፣ እንዲህም አለ፥ አይኖችህን በሸክላው ቀባቸው፣ እጠባቸውም፣ እና ታያለህ። እርሱም ይህን አደረገ።
፴፮ እና እግዚአብሔር የፈጠራቸውን መንፈሶች አየ፤ እና በተፈጥሮ አይኖች የማይታዩትን ነገሮች ሁሉ ደግሞ አየ፤ እናም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እንዲህ የሚል አባባል በምድር ውስጥ ነበር፥ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ባለራዕይ አስነስቷል።
፴፯ እናም እንዲህ ሆነ ሔኖክ በሃገሩ ውስጥ ከሕዝቦቹ መሀከል በመሄድ፣ በታላቅ ስፍራዎችና በተራሮች ላይ በመቆም፣ በደመቀ ድምፅ ስለ መጥፎ ሰራቸው በእነርሱ ላይ መሰከረ፤ እና ሁሉም ሰዎች በእርሱ ምክንያት ተቀይመው ነበር።
፴፰ እና ወደታላቅ ስፍራዎች በመሄድ፣ ለድንኳን ጠባቂዎች እንዲህ በማለት፣ እርሱን ለመስማት መጡ፥ ባለራእዩን ለማየት ወደዚያ ስፍራ ስንሄድ እዚህ ቆዩና ድንኳኖችን ጠብቁ፣ እየተነበየ ነውና፣ እና በሀገሩም የተለየ ነገር አለ፤ በመካከላችንም የዱር ሰው መጥቷል።
፴፱ እንዲህ ሆነ በሰሙትም ጊዜ ማንም ሰው እጆቻቸውን አላሳረፉበትም፤ የሰሙት ሁሉ ፍርሀት መጣባቸው፤ እርሱም ከእግዚአብሔር ጋር ይራመዳልና።
፵ እናም ማሂጃ የሚባል ሰውም ወደ እርሱ መጣና እንዲህ አለው፥ ማን እንደሆንክ እና ከየት እንደመጣህ በግልፅ ንገረን?
፵፩ እርሱም እንዲህ አላቸው፥ እኔ ከአባቶቼ ምድር፣ እስከዛሬ ድረስ ጻድቅ ከሆነው ሀገር ከቃይናን ነው የመጣሁት። አባቴም የእግዚአብሔርን መንገድ በሙሉ አስተምሮኛል።
፵፪ እንዲህም ሆነ፣ ከቃይናን ሀገርም በምስራቅ ባህር ስጓዝ፣ ራዕይ ታየኝ፤ እና አስተውሉ፣ እነሆ ሰማይን አየሁ፣ ጌታም አነጋግሮኝ፣ ትእዛዝም ሰጠኝ፤ ስለዚህ፣ ለዚህ ምክንያት፣ ትእዛዝን ለማክበርም እነዚህን ቃላት እናገራለሁ።
፵፫ ሔኖክም ንግግሩን ቀጥሎ እንዲህ አለ፥ እኔን ያናገረኝ ጌታም የሰማይ እግዚአብሔር ነው፣ የእኔ አምላክ፣ እና የእናንተም አምላክ ነው፣ እና እናንተም ወንድሞቼ ናችሁ፣ እና ለምን የራሳችሁን ምክር ትሰማላችሁ፣ እና የሰማይ እግዚአብሔርንስ ትክዳላችሁ?
፵፬ ሰማያትን ሰራ፤ ምድርም የእግሩ ማረፊያ ናት፤ የዚህም መሰረት የእርሱ ነው። እነሆ፣ እርሱም ሰርቶታል፣ የሰውንም ሰራዊት በምድርም ፊት አምጥቷል።
፵፭ ሞትም በአባቶቻችን ላይም መጥቷል፤ ይህም ቢሆን እናውቃቸዋለን፣ እና ልንክዳቸው አንችልም፣ እና ከሁሉም የመጀመሪያውን፣ እንዲሁም አዳምን፣ እናውቃለን።
፵፮ በእግዚአብሔር ጣት በተሰጠን ምሳሌ መሰረት የመታሰቢያ መጻህፍትን በመካከላችን ፅፈናል፤ እና ይህም በራሳችን ቋንቋ የተሰጠን ነው።
፵፯ እና ሔኖክ የእግዚአብሔርን ቃላት ሲናገር፣ ሰዎቹም ተንቀጠቀጡ፣ እና በእርሱ ፊትም መቆም አልቻሉም።
፵፰ እርሱም እንዲህ አላቸው፥ ያ አዳም ስለወደቀ፣ እኛም አለን፤ በእርሱም ውድቀትም ሞት መጣ፤ እና በጉስቁልና በዋይታ ተካፋዮችም ሆነናል።
፵፱ እነሆ ሰይጣን በሰው ልጆች መካከል መጣ፣ እና እንዲያመልኩትም ፈተናቸው፤ እናም ሰዎችም ስጋዊ፣ ስሜትዊና፣ ዲያብሎሳዊ ሆነዋል፣ እና ከእግዚአብሔር ፊትም ተከልክለዋል።
፶ ነገር ግን እግዚአብሔር ለአባቶቻችን ሁሉም ሰዎች ንስሀ መግባት እንዳለባቸው አስታውቋቸዋል።
፶፩ ወደ አባታችን አዳምንም በድምጹ ጠርቶ እንዲህ ብሏል፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ አለምንና ስጋ ከመልበሳቸው በፊት ሰዎችን የፈጠርኩኝ እኔ ነኝ።
፶፪ ደግሞም እንዲህ አለው፥ ወደእኔ ብትመለስ፣ እና ድምጼንም ብታደምጥ፣ እና ብታምን፣ እና ለተላለፍካቸውም ነገሮች ንስሀ ብትገባ፣ እና ለሰው ልጆች ደህንነትን ለማምጣት በሚችለው ከሰማይ በታች በሚሰጠው በጸጋና እውነት በተሞላበት አንድያ ልጄ ስም፣ እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ በውሀ ብትጠመቅ፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታም ይሰጥሀል፣ እና ሁሉንም ነገሮችን በእርሱ ስም ጠይቅ፣ እና የምትጠይቀው ማንኛውም፣ ይህም ይሰጥሀል።
፶፫ አባታችን አዳምም ለጌታ ተናገረ፣ እና እንዲህም አለው፥ ለምንድን ነው ሰዎች ንስሀ መግባትና በውሀ መጠመቅ ያለባቸው? እና ጌታም ለአዳም እንዲህ አለው፥ ከዔድን ገነት ውስጥ ለተላለፍከው ይቅርታን ሰጥቼሀለሁኝ።
፶፬ በዚህም ምክንያትም ከህዝቦቹም መካከል ይህም አባባል መጣ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ለቀደመው ኃጢአት ስርያትን አድርጎላቸዋል፣ በዚህም የወላጆች ኃጢአት በልጆች ራስ ላይ አይመለስም፣ እነርሱም ከአለም መሰረት ጊዜ ጀምሮ ከኃጢአት ንጹህ ናቸውና።
፶፭ እና ጌታም ለአዳም እንዲህ ብሎ ተናገረ፥ ልጆች በኃጢአት እስከተጸነሱ ድረስ፣ ሲያድጉም እንዲህ ነው፣ ኃጢአት በልባቸው ይጸነሳል፣ እና የመልካሙን ነገር ሽልማት ያውቁ ዘንድ፣ መራራውንም ይቀምሳሉ።
፶፮ መልካሙን ከክፉው ያውቁ ዘንድ ተሰጥቶአቸዋል፤ ስለዚህ ለራሳቸው ሃላፊዎች ናቸው፣ እና ለአንተም ሌላ ህግና ትእዛዝ ሰጥቼሃለሁ።
፶፯ ስለዚህ በየትም ያሉ ሁሉም ሰዎች ንስሀ መግባት እንደሚገባቸው ልጆችህን አስተምራቸው፣ አለዚያም የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ በምንም አይችሉም፣ ምንም እርኩስ ነገር በዚያ ወይም በእርሱ ፊት መኖር አይችልምና፤ በአዳም ቋንቋ ስሙ የቅድስና ሰው ነውና፣ እና የአንድያ ልጅ ስምም የሰው ልጅ፣ በመካከለኛው ዘመን የሚመጣው የፅድቅ ዳኛ፣ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና።
፶፰ ስለዚህ እነዚህን ነገሮች በነጻ ለልጆችህ እንድታስተምር እንዲህ በማለት ትእዛዝን እሰጥሀለሁ፤
፶፱ በመተላለፍ ምክንያት ውድቅት መጥቷል፣ ያም ውድቀት ሞትን አምጥቷል፣ እና በምድር በውሃ፣ በደምና፣ በፈጠርሁት መንፈስ እንደተወለድክም ሁሉ፣ በአፈርም ህያው ነፍስ ሆንህ፣ እንዲሁም ወደ መንግስተ ሰማያት በውሃ፣ በመንፈስ በድጋሚ መወለድ አለብህ፣ በደምም እንዲሁም ከኃጢአት በሚያነጻህ በአንድያ ልጄ ደም መንጻት አለብህ፤ እና ከሁሉም ኃጢአት እንድትጸዳ፣ እና በዚህ አለም የዘለአለም ህይወት ቃላትን፣ እና በሚመጣው አለም የዘለአለም ህይወት፣ እንዲሁም የማይሞት ክብርን፣ ትደሰትበት ዘንድ ነው፤
፷ በውሀው ትእዛዝን ታከብራለህና፤ በመንፈሱም ትጸድቃለህ፣ እናም በደሙም ነጽተሀል፤
፷፩ ስለዚህ ይህም የሰማይ መዝገብ፤ አጽናኝ፣ የማይሞተው ክብር ሰላም ነገሮች፤ የሁሉም ነገሮች እውነት፤ ለሁሉም ነገሮች ህይወትን የሚሰጥ፣ ሁሉንም ነገሮች እንዲኖሩ የሚያደርገው፤ ሁሉንም ነገሮች የሚያውቅ፣ እና በጥበብ፣ በርህራሄ፣ በእውነት፣ በፍትህ፣ እናም በፍርድ አማካይነት ሁሉም ሀይል ያለው በውስጥህ እንዲኖር ተሰጥቶሀል።
፷፪ አሁንም እነሆ፣ እልሀለሁ፥ ይህ በመካከለኛው ዘመን በሚመጣው አንድያ ልጄ ደም አማካይነት የሚከናወነው የሰው ሁሉ የደህንነት እቅድ ነው።
፷፫ እና እነሆ፣ ሁሉም ነገሮች ተማሳሌት አሏቸው፣ እና መንፈሳዊውም ይሁን አለማዊ ነገሮች፣ ሁሉም ነገሮች የፈጠርኳቸውና የሰራኋቸው ስለእኔ እንዲመሰክሩ ነው፤ በሰማይ የሚገኙም ነገሮች፣ እና በምድር ላይ የሚገኙት ነገሮች፣ እና በምድር ውስጥያሉት ነገሮች፣ እና ከምድር በታች ያሉት፣ ከታችም እና ከላይም፥ ሁሉም ነገሮች ስለእኔ ይመሰክራሉ።
፷፬ እንዲህም ሆነ፣ ጌታ ከአባታችን ከአዳም ጋር ሲናገር፣ አዳምም ወደ ጌታ ጮኸ፣ እና በጌታ መንፈስም ተነጥቆ ተወሰደ፣ እና ወደ ውሀ ውስጥም ተወሰደ፣ እና በውሀ ውስጥም ተኛ፣ ከእዚያም ወዲያው ከውሀው ወጣ።
፷፭ እንዲህም ተጠመቀ፣ እና የጌታ መንፈስ በእርሱ ላይ አረፈበት፣ እና እንዲህም በመንፈስ ተወለደ፣ እና በውስጥ ሰውነቱም ህይወት ተሰጠው።
፷፮ እና ከሰማይ ድምጽ እንዲህ ሲል ሰማ፥ በእሳት፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ፣ ተጠምቀሃል። ይህም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለአለም የአብ፣ እና የወልድ መዝገብ ነው።
፷፯ አንተም ከዘለአለም እስከ ዘለአለም፣ ለቀናቱ የመጀመሪያ ወይም የመጨረሻ ከሌለው ከእርሱ ስርዓትም ሆነሀል።
፷፰ እነሆ፣ አንተ በእኔ አንድ ነህ፣ የእግዚአብሔርም ልጅ፤ እና እንደዚህ ሁሉም የእኔ ልጆች መሆን ይችላሉ፣ አሜን።