ክፍል ፸፯
በመጋቢት ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) አካባቢ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንደሚገልጸው፣ “ቅዱሳን መጻህፍትን ከመተርጎም ጋር በተገናኘ፣ ስለቅዱስ ዮሐንስ ራዕይ የሚቀጥለውን መግለጫ ተቀበልኩ”።
፩–፬፣ አራዊት መንፈስ አላቸው እናም በዘለአለማዊ ደስታ ይኖራሉ፤ ፭–፯፣ ይህች ምድር የ፯ ሺህ አመታት ጊዜያዊ ህይወት አላት፤ ፰–፲፣ የተለያዩ መላእክት ወንጌልን ደግመው መለሱ እና በምድርም አገለገሉ፤ ፲፩፣ ፻፵፬ ሺህዎቹ መታተም ፲፪–፲፬፣ ክርስቶስ በሰባት ሺህ አመታት መጀመሪያ ውስጥ ይመጣል፤ ፲፭፣ ሁለት ነቢያት በአይሁድ ሀገሮች ይነሳሉ።
፩ ጥ. በራዕይ ምዕራፍ ፬፣ እና ቁጥር ፮ ውስጥ በዮሐንስ የተነገረው የብርጭቆ ባሕር ምንድን ነው?መ. ይህም ምድር በተቀደሰ፣ በማይጠፋ፣ እና ዘለአለማዊ ሁኔታዋ ነው።
፪ ጥ. በዚህ ተመሳሳይ አንቀፅ ውስጥ ስለተነገሩት አራቱ እንስሳት ምን ሊገባን ያስፈልገናል?መ. እነዚህ ገላጩ ዮሐንስ፣ ሰማይን፣ የእግዚአብሔርን ገነትን፣ የሰውን፣ እናም የእንስሣትን፣ እና በምድርም የሚንቀሳቀሱት፣ እና የሰማይ አዕዋፋት ደስታን፤ መንፈሳዊ ነገሩ ጊዜአዊ በሆነው ምስል መሆኑን፤ እናም ጊዜአዊ ነገሩም መንፈሳዊ በሆነው የተመሰለ መሆኑን፤ የእንስሳ እና እግዚአብሔር የፈጠራቸው ሌሎች ፍጡራንም ደግመው የሰው መንፈስ በሰውየው ምስል እንደሆነ ለማሳየት የተጠቀመባቸው ምሳሌያዊ መግለጫዎች ናቸው።
፫ ጥ. አራቱ እንስሳት በልዩ እንስሣት የተወሰኑ ናቸው፣ ወይስ ክፍሎችን እና ስርዓቶችን የሚወክሉ ናቸው?መ. ለዮሐንስ ህያዋን ፍጡራን በየክፍሎቻቸው በተወሰነ ምድባዊ ስርዓታቸው ወይም በፍጥረት ተፅዕኖ አካባቢያቸው ውስጥ ክብራቸውን በመወከል፣ በዘለአለማዊ ደስታቸው ሲደሰቱ፣ የታዩት፣ በአራት ልዩ እንስሳት የተወሰኑ ናቸው።
፬ ጥ. እንስሣቱ በነበራቸው አይኖች እና ክንፎች ምን ሊገባን ያስፈልገናል?መ. አይኖቻቸው ብርሀን እና እውቀትን እና በእውቀት የተሞሉ መሆናቸውን የሚወክሉ ናቸው፤ እናም ክንፎቻቸውም የመነቃነቅ፣ የመስራት፣ እናም ሌሎች ሀይላትን የሚወክሉ ናቸው።
፭ ጥ. በዮሐንስ ስለተነገሩት ሀያ አራት ሽማግሌዎች ምን ሊገባን ያስፈልገናል?መ. ዮሐንስ ያያቸው ሽማግሌዎች፣ በአገልግሎት ስራ ታማኝ የነበሩ እና ሞተው የነበሩት ሽማግሌዎች እንደሆኑ፣ በሰባቱ አብያተክርስቲያናት አባል የሆኑ፣ እና በእግዚአብሔር ገነት በሰማይ እንደሚገኙ ሊገባን ያስፈልገናል።
፮ ጥ. ዮሐንስ ስላየው፣ ከጀርባው በሰባት ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍ ምን እንዲገባን ያስፈልገናል?መ. ይህም የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ሚስጥራት፣ እና ስራዎች፤ በሰባት ሺ አመታት ኑሮ፣ ወይም ጊዜአዊ ህይወት፣ ጊዜ የተደበቁትን የዚህን ምድር አስተዳደር በሚመለከት እንደያዘ ሊገባን ያስፈልጋል።
፯ ጥ. ስለታተሙት ሰባት ማኅተሞች ምን ሊገባን ያስፈልገናል?መ. የመጀመሪያው ማኅተም የመጀመሪያውን ሺህ አመታት ነገሮችን እንደያዘ፣ እናም ሁለተኛውም ደግሞ የሁለተኛውን ሺ አመታት፣ እናም እስከሰባተኛው እንዲሁ እንደሚቀጥል ሊገባን ያስፈልጋል።
፰ ጥ. በራዕይ ፯ኛ ምዕራፍ እና ፩ኛ ቁጥር ውስጥ ስለተነገሩት አራት መላዕክት ምን ሊገባን ያስፈልገናል?መ. እነዚህ መላዕክት ከእግዚአብሔር እንደተላኩ፣ ለእነርሱም፣ ህይወትን ለማዳን እናም ለማጥፋት፣ በምድር አራት ክፍሎች ላይ ሀይል እንደተሰጣቸው፤ እነዚህም ዘለአለማዊውን ወንጌል ለእያንዳንዱ ሕዝብ፣ ነገድ፣ ቋንቋ፣ እና ወገን በአደራ የሚሰጡ መሆኑን፤ ሰማያትን ለመዝጋት፣ በህይወትም ለማተም፣ ወይም የጭለማ አካባቢዎችንም ለመጣል ሀይል እንዳላቸው እንዲገባን ያስፈልጋል።
፱ ጥ. በራዕይ ፯ኛ ምዕራፍ እና ፪ኛ ቁጥር፣ ከምስራቅ ስለሚነሳው መልአክ ምን እንዲገባን ያስፈልገናል?መ. ከምስራቅ የሚነሳው መልአክ በእስራኤል አስራ ሁለቱ ጎሳ ላይ የህያው እግዚአብሔር ማተሚያ የተሰጠው እንደሆነ እዲገባን ያስፈልጋል፤ ስለዚህ፣ ዘለአለማዊ ወንጌሉን ይዞ፣ የአምላካችንን ባሪያዎች ግምባራቸውን እስክናትማቸው ድረስ ምድርን ቢሆን ወይም ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጕዱ፣ ብሎ ወደ አራቱ መላእክት ይጮሀል። እናም፣ ከተቀበላችሁትም፣ ይህም የእስራኤልን ነገዶች ለመሰብሰብ እና ሁሉንም ነገሮች ደግሞ ለመመለስ የሚመጣው ኤልያስ ነበር።
፲ ጥ. በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የተጠቀሱት ነገሮች የሚከናወኑበት በምን ጊዜ ነው?መ. የሚከናወኑት በስድስት ሺህ አመታት ውስጥ፣ ወይም በስድስተኛው ማኅተም በሚከፈትበት ነው።
፲፩ ጥ. ከእስራኤል ጎሳዎች ሁሉ መካከል፣ የአንድ መቶ አርባ አራት ሺዎቹ መታተም—ከእያንዳንዱ ጎሳ አስራ ሁለት ሺ—ምን ሊገባን ያስፈልገናል?መ. የታተሙት ዘለአለማዊውን ወንጌል እንዲያስተዳድሩ በእግዚአብሔር ቅዱሱ ስርዓት የተሾሙት ሊቀ ካህናት እንደሆኑ እንዲገባን ያስፈልጋል፤ እነዚህም ወደ በኩር ቤተክርስቲያን የመምጣት ፈቃድ ያሏቸውን እንዲያመጡ በምድር አገሮች ላይ ሀይል በተሰጣቸው መላዕክት ከእያንዳንዱ ሕዝብ፣ ነገድ፣ ቋንቋ፣ እና ወገን መካከል የተሾሙት ናቸውና።
፲፪ ጥ. በራዕይ ምእራፍ ፰ ውስጥ ስለተጠቀሰው የመለከት መነፋት ምን ሊገባን ያስፈልገናል?መ. እግዚአብሔር አለምን በስድስት ቀናት እንደሰራ፣ እና በሰባተኛው ቀን ስራውን እንደጨረሰ፣ እናም እንዲቀደስም እንዳደረገው፣ እናም ደግሞም በሰባተኛው ቀን ሰውን ከምድር አፈር እንዳበጀው፣ እንዲሁም፣ በሰባት ሺ አመታት መጀመሪያ ላይ ጌታ አምላክ ምድርን እንደሚቀድስ፣ እናም የሰውን ደህንነት እንደሚፈፅም፣ እናም ሁሉንም ነገሮች እንደሚፈርድ፣ እናም ሁሉንም ነገሮች፣ በሁሉም ነገሮች መጨረሻ፣ ሲያትም በሀይሉ ካልጨመራቸው በስተቀር፣ ሁሉንም ነገሮች እንደሚያድን እንዲገባን ያስፈልጋል፤ እናም፣ በሰባተኛው ሺ አመታት መጀመሪያ፣ የሰባቱ መላዕክት መለከት ድምፅ የስራው መዘጋጃ እና መጨረሻ—ዳግሞ ከመምጣቱ በፊት መንገዱ የሚዘጋጅበት ነው።
፲፫ ጥ. በራዕይ ምዕራፍ ፱ ውስጥ የተጻፉት ነገሮች የሚከናወኑበት መቼ ነው?መ. እነዚህ የሚከናወኑት ሰባተኛው ማኅተም ከተከፈተ፣ ከክርስቶስ መመለስ በፊት ነው።
፲፬ ጥ. በራዕይ ምዕራፍ ፲ ውስጥ እንደተጠቀሰው፣ ዮሐንስ ስለበላት ታናሽ መጽሐፍ ምን ሊገባን ያስፈልገናል?መ. ይህም የእስራኤልን ነገዶች ለመሰብሰብ የተሰጠው ተልዕኮ፣ እናም ስርዓት እንደሆነ እንዲገባን ያስፈልጋል፤ እነሆ፣ እንደተጻፈው፣ ይህ መጥቶ ሁሉንም ነገሮች ዳግሞ መመለስ ያለበት ኤልያስ ነው።
፲፭ ጥ. በራዕይ ምዕራፍ አስራ አንድ ውስጥ ስለተጠቀሱት ሁለቱ ምስክሮች ምን ሊገባን ያስፈልገናል?መ. እነዚህም በመጨረሻው ቀናት፣ በዳግም መመለሱ ጊዜ፣ እና ከተሰበሰቡ እና የኢየሩሳሌም ከተማን በአባቶቻቸው ምድር ላይ ለሚሰሩ ለአይሁዶች እንዲተነቢዩ በአይሁድ ሀገሮች የሚነሱት ሁለት ነቢያት ናቸው።