ክፍል ፺
በመጋቢት ፰፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ይህ ራዕይ የቀዳሚ አመራርን ለመመስረት የቀጠለ እርምጃ ነው (የክፍል ፹፩ ርዕስን ተመልከቱ)፤ በዚህም ምክንያት፣ የተጠቀሱት አማካሪዎች በመጋቢት ፲፰፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) ተሾሙ።
፩–፭፣ የመንግስት ቁልፎች ለጆሴፍ ስሚዝ እና በእርሱም በኩል ለቤተክርስቲያኗ ተሰጥተዋል፤ ፮–፯፣ ስድኒ ሪግደን እና ፍረድሪክ ጂ ዊሊያምስ በቀዳሚ አመራር ያገልግሉ፤ ፰–፲፩፣ ወንጌሉ ለእስራኤል ህዝብ፣ ለአህዛብ፣ እና ለአይሁድ፣ እያንዳንዱም ሰው በሚሰማው ቋንቋ ይሰበክለት፤ ፲፪–፲፰፣ ጆሴፍና አማካሪዎቹ ቤተክርስቲያኗን በስርዓት ያደራጁ፤ ፲፱–፴፯፣ የተለያዩ ግለሰቦች በቅንነት እንዲሄዱ እና በመንግስቱ እንዲያገለግሉ በጌታ ተመክረዋል።
፩ ጌታ እንዲህ ይላል፣ ልጄ ሆይ እውነት፣ እውነት እልሀለሁ፣ በልመናህ መሰረት፣ ኃጢአቶችህ ተሰርየውልሀል፣ የአንተ እና የወንድሞችህ ጸሎቶች ወደ ጆሮዎቼ መጥተዋልና።
፪ ስለዚህ፣ የተሰጠህን የመንግስት ቁልፎች ለመያዝ ከዚህ ጀምሮ ተባርከሀል፤ ይህም መንግስት ለመጨረሻ ጊዜ እየመጣ ያለው ነው።
፫ እውነት እልሀለሁ፣ በዚህ አለምም ሆነ በሚመጣው አለም ሳለህ፣ የመንግስት ቁልፎች ከአንተ በምንም መንገድ አይወሰድብህም፤
፬ ይህም ቢሆን፣ አዎን፣ በአንተ በኩል የእግዚአብሔር ቃላት ለሌላ፣ እንዲሁም ለቤተክርስቲያኗ፣ ይሰጣሉ።
፭ እና የእግዚአብሔርን ቃላት የሚቀበሉ ሁሉ፣ እንደ ቀላል ነገር እንዳይቆጥሯቸው፣ እና በዚህም ፍርድ እንዳይመጣባቸው፣ እና ማእበሉ ሲወርድ፣ እና ነፋሱም ሲነፍስ፣ እና ዝናብም ሲጥል፣ እና ቤታቸውንም ሲገፋው እንዳይደናቀፉ እና እንዳይወድቁ፣ እንዴት እንደሚይዟቸው ይጠንቀቁ።
፮ ደግሞም፣ ለወንድሞችህ ስድኒ ሪግደንና ፍረድሪክ ጂ ዊሊያም እውነት እላቸዋለሁ፣ ኃጢአቶቻቸውም ደግሞ ተሰርየዋል፣ እና የዚህን የመጨረሻ መንግስት ቁልፎችን መያዝን በተመለከተ ከአንተ ጋር እንደ እኩል ይቆጠራሉ፣
፯ ደግሞም እንዲደራጅ ያዘዝኩትን የነብያት ትምህርት ቤት ማስተዳደሪያ ቁልፎችን መያዝን በተመለከተ ከአንተ ጋር እንደ እኩል ይቆጠራሉ፤
፰ በዚህም፣ የሚያምኑት ሁሉ፣ ለፅዮን፣ እና ለእስራኤል ህዝብ፣ እና ለአህዛብ ደህንነት በአገለግሎታቸው ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ፤
፱ በአገልግሎትህ ቃልን ይቀበሉ ዘንድ፣ እና በአገልግሎታቸውም ቃል፣ እስከ ምድር ዳርቻ ይሄድ ዘንድ፤ መጀመሪያ ወደ አህዛብ፣ እና ከዚያም እነሆ አስተውሉ፣ ወደ አይሁድም ይዞራሉ።
፲ ከዚያም ህዝብን፣ የአህዛብን አገሮች፣ የጆሴፍን ቤት፣ የደህንነታቸውን ወንጌል ለማሳመን የጌታ እጅ በሀይል የሚገለጥበት ቀን ይመጣል።
፲፩ በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፣ የወንጌል ሙላትን ለዚህ ሀይል በተሾሙት በኩል፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ራዕይ በሚፈስባቸው በአፅናኙ አገልግሎት፣ እያንዳንዱ ሰው በገዛ ልሳን እና በራሱ ቋንቋ ይሰማል።
፲፪ አሁንም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በአገልግሎቱ እና በአመራሩ እንድትቀጥሉ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።
፲፫ እና የነቢያትን ትርጉም ስትጨርሱ፣ ከዚህ በኋላ የቤተክርስቲያኗን እና የትምህርት ቤቱን ጉዳዮች ትመራላችሁ፤
፲፬ እና ከጊዜ ወደ ጊዜም፣ በአፅናኙ እንደሚገለጸው፣ ተነግረው የማይታወቁ የመንግስትን ሚስጥራት በራዕይ ተቀበሉ፤
፲፭ እና ቤተክርስቲያኖችንም በስርዓት አደራጁ፣ እና አጥኑና ተማሩ፣ እና ሁሉንም መልካም መጻህፍት፣ ቋንቋዎች፣ ልሳኖች፣ እና ህዝብን እወቁ።
፲፮ እና ይህም፣ ኮሚቴውን መምራት፣ እና የዚህን ቤተክርስቲያን እና መንግስት ጉዳዮች በስርዓት ማደራጀት፣ በህይወታችሁ ሁሉ ጉዳያችሁ እና ተልዕኮአችሁ ይሆናል።
፲፯ አትፈሩ፣ ወይም አትዋረዱ፤ ነገር ግን በትዕቢታችሁ እና በኩራታችሁም ተገሰጹ፣ በነፍሶቻችሁ ወጥመድ ያመጣልና።
፲፰ ቤቶቻችሁንም በስርዓት አስተካክሉ፤ ስራ ፈትነትን እና ጽዱ አለመሆንን ከእናንተ አርቁ።
፲፱ አሁን፣ እውነት እልሀለሁ፣ ወድያውኑ ሲቻል፣ ለአማካሪህ እና ለጸሀፊህ፣ እንዲሁም ለፍረድሪክ ጂ ዊሊያምስ ቤተሰብ ስፍራ ይሰጥ።
፳ እና አዛውንቱ አገልጋዬ፣ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ቀዳማዊም፣ አሁን በሚኖርበት ስፍራ ከቤተሰቡ ጋር ይቀጥል፤ እና የጌታ አንደበት እስከሚወስንበትም ድረስ አይሸጥ።
፳፩ እና አማካሪዬ፣ እንዲሁም ስድኒ ሪግደን፣ የጌታ አንደበት እስከሚወስንበት ድረስ አሁን በሚኖርበት ይቆይ።
፳፪ እና ኤጲስ ቆጶሱ በቅንነት ወኪልን ለማግኘት ይፈልግ፣ እና ይህም ሰው ሀብት ያከማቸ፣ የእግዚአብሔር ሰው፣ እና ጠንካራ እምነት ያለው ይሁን—
፳፫ በዚህም እያንዳንዱን እዳ ለመክፈል ችሎታ ይኖረው ዘንድ፤ የጌታ ጎተራ በሰዎቹ አይኖች ፊት መጥፎ ስም አይኖረው ዘንድ ወኪሉ ሀብት ያከማቸ የእግዚአብሔር ሰው፣ እና ጠንካራ እምነት ያለው ይሁን።
፳፬ ተግታችሁ ፈልጉ፣ ዘወትር ጸልዩ፣ እናም እመኑ፣ እና በቅንነት ከተራመዳችሁ እና እርስ በራስ ቃል ኪዳን የገባችሁበትን ቃል ኪዳን ካስታወሳችሁ፣ ሁሉም ነገሮች ለእናንተ በጎነት አብረው ይሰራሉ።
፳፭ ቤተሰቦቻችሁ አነስተኛ ይሁኑ፤ በተለይም የቤተሰባችሁ አባል ያልሆኑትን በሚመለከት፤ በተለይም የአዛውንቱ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ቀዳማዊ ቤተሰብም፤
፳፮ ስራዎቼ እንዲከናወኑ፣ ለእናንተ የተሰጧችሁ ነገሮች ከእናንተ እንዳይወሰዱ እና ብቁ ላልሆኑት እንዳይሰጥ ዘንድ—
፳፯ እና በዚህም ያዘዝኳችሁን ነገሮች ለማከናወን እንዳትደናቀፉ ቤተሰቦቻችሁ አነስተኛ ይሁኑ።
፳፰ ደግሜ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ባሪያዬ ቪየና ዣክ ወጪዋን እንድትችል፣ እና ወደ ፅዮን ምድር ለመሄድ ገንዘብ ይሰጣት ዘንድ ፍቃዴ ነው፤
፳፱ እና የሚቀረው ገንዘብም ለእኔ ይቀደስ፣ እና በጊዜዬም ዋጋዋን ታገኛለች።
፴ እውነት እላችኋለሁ፣ ወደ ፅዮን ምድር እንድትሄድ፣ እና ከኤጲስ ቆጶስ እጅ ውርሷን እንድትቀበል ፍቃዴ ነው፤
፴፩ ታማኝ እስከሆነች ድረስ በሰላም እንድትሰፍር፣ እና ከዚህ በኋላ በቀኖቿ ስራ ፈት እንዳትሆን ፍቃዴ ነው።
፴፪ እነሆም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ይህን ትእዛዝ ጻፉ፣ እና በፅዮን ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችሁን፣ በፍቅር ሰላምታ፣ በጊዜዬ በፅዮን እንድትመሩ እንደተጠራችሁ ንገሯቸው።
፴፫ ስለዚህ፣ በዚህ ጉዳይ እኔን ማድከማቸውን ያቁሙ።
፴፬ እነሆ፣ እላችኋለሁ በፅዮን ያሉት ወንድሞቻችሁ ንስሀ ይግቡ፣ እና መላእክት በእነርሱ ይደሰቱ።
፴፭ ይህም ቢሆን፣ በብዙ ነገሮች አልተደሰትኩም፤ እና በአገልጋዬ ዊሊያም ኢ መክሌይን፣ ወይም በአገልጋዬ ስድኒ ጊልበርት አልተደሰትኩም፤ እና ኤጲስ ቆጶሱና ሌሎች ንስሀ የሚገቡበት ብዙ ነገሮች አላቸው።
፴፮ ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ እኔ ጌታ ከፅዮን ጋር እጣላለሁ፣ እና ጠንካራዋን ለምኛለሁ፣ እና እስክትሸነፍ እና በፊቴ ንጹህ እስክትሆን ድረስ እገስጻለሁ።
፴፯ ከስፍራዋ ልትነቃነቅ አትችልምና። እኔ ጌታ ተናግሬዋለሁ። አሜን።