ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፳፭


ክፍል ፳፭

ሐምሌ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ ፔንስልቫኒያ በጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት የተሰጠ ራዕይ። (የክፍል ፳፬ ርዕስን ተመልከቱ)። ይህ ራዕይ ጌታ ለነቢዩ ሚስት ለኤማ ስሚዝ ያለውን ፈቃድ ይገልጣል።

፩–፮፣ ኤማ ስሚዝ፣ ባለቤቷን ለመርዳት እና ለማጽናናት የተጠራች የተመረጠች ሴት ነች፤ ፯–፲፩፣ እንዲሁም ለመጻፍ፣ ቅዱሳን መጻህፍትን ለማብራራት እና መዝሙሮችን ለመምረጥ ተጠርታለች፤ ፲፪–፲፬፣ የጻድቃን መዝሙር ለጌታ ጸሎት ነው፤ ፲፭–፲፮፣ በዚህ ራዕይ ውስጥ ያሉት የታዛዥነት መሰረታዊ መርሆች በሁሉም ዘንድ ተፈጻሚዎች ናቸው።

ለአንቺ እየተናገርኩ ሳለ፣ ልጄ ኤማ ስሚዝ፣ የጌታ አምላክሽን ድምጽ አድምጪ፤ እውነት እልሻለሁ፣ ወንጌሌን የሚቀበሉ ሁሉ በመንግስቴ ወንድ እና ሴት ልጆች ናቸው።

ፈቀዴን በተመለከተ ራእዬን እሰጥሻለሁ፤ ታማኝ ከሆንሽ እና በምግባረ በጎነት መንገድ በፊቴ የምትጓዢ ከሆነ፣ ህይወትሽን እጠብቀዋለሁ እናም በፅዮን ርስትን ትቀበያለሽ።

እነሆ፣ ኃጢአቶችሽ ተሰርየውልሻል፣ እናም እኔ የጠራሁሽ አንቺ የተመረጥሽ ሴት ነሽ።

ስላላየሻቸው ነገሮች አታጉረምርሚ፣ ከአንቺ እና ከአለም ታግደዋል፣ ይህም ወደፊት በሚመጣው በእኔ ዘንድ ጥበብ ነው።

የጥሪሽ ሀላፊነት ለባለቤትሽ ለአገልጋዬ ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ በመከራው ወቅት በአበረታች ቃላት፣ በትህትና መንፈስ፣ በመስጠት መጽናኛው እንድትሆኚው ነው።

እናም በሚሄድበት ጊዜ አብረሽው ትሄጂያለሽ፣ እናም አገልጋዬን ኦሊቨር ካውድሪን ወደፈቀድኩበት ስፍራ እልከው ዘንድ፣ የሚጽፍለት ሰው ሳይኖር ለእርሱም ጸሀፊም ትሆኛለሽ።

ቅዱሳን መጻህፍትን ለማብራራት እናም መንፈሴ እንደሰጠሽ ቤተክርስቲያኗን ታበረታቺ ዘንድ፣ በእርሱም እጅ ትሾሚያለሽ

እጁንም በራስሽ ላይ ይጭናል እናም መንፈስ ቅዱስን ትቀበያለሽ፣ እናም ጊዜሽ ለመጻፍ እና ብዙ ለመማር የተሰጠ ይሆናል።

እናም ባለቤትሽ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሚረዳሽ መፍርሀት የለብሽም፤ እንደ እምነታቸው፣ እንደ ፈቃዴ፣ ሁሉም ነገሮች ይገለጡላቸው ዘንድ፣ የእርሱ ጥሪ ለእነርሱ ነው።

እናም እውነት እልሻለሁ የዚህን አለም ነገሮች ወደጎን ትተያቸዋለሽ እናም የተሻሉ ነገሮችን ትሺያለሽ

፲፩ እናም እንዲሁም፣ በቤተክርስቲያኔ ውስጥ መኖራቸው ይህም ስለሚያስደስተኝ፣ እንደሚሰጥሽም መጠን የተቀደሱ መዝሙሮችን ትመርጪ ዘንድ ይሰጥሻል።

፲፪ ከልብ ከሆነ ዝማሬ ነፍሴ ትደሰታለችና፣ አዎን የጻድቅን መዝሙር በእኔ ዘንድ ጸሎት ነው፣ በረከትንም በራሳቸው ላይ በማድረግ ይመለስላቸዋልና።

፲፫ ልብሽን አቅኚ እናም ተደሰቺ፣ እና ከገባሽውም ቃል ኪዳን ጋርም ተጣበቂ።

፲፬ በትህትና መንፈስ ቀጥዪ፣ እናም ከትዕቢትም ተጠበቁ። ነፍስሽ በባልሽ እናም በእርሱ ላይ በሚመጣው ክብር ሀሴትን ታድርግ።

፲፭ ዘወትር ትእዛዛቴን ጠብቂ፣ እናም የጽድቅ አክሊልን ትቀበያለሽ። ይህንን ባታደርጊ፣ እኔ ወዳለሁበት ስፍራ መምጣት አትችዪምና

፲፮ እናም እውነት፣ እውነት እልሻለሁ፣ ለሁሉም የሆነው ይህ የእኔ ድምጽ ነው። አሜን።