ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፶፰


ክፍል ፶፰

በነሀሴ ፩፣ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በፅዮን ጃክሰን የግዛት ክፍል ሚዙሪ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ነቢዩና አብረውት የተጓዙት በጃክሰን የግዛት ክፍል ሚዙሪ ውስጥ ከገቡ በኋላ በመጀመሪያው ሰንበት፣ የሀይማኖት ስብሰባ ነበር እና ሁለት አባላትም ተጠምቀው ነበር። በዚያ ሳምንትም፣ ከቶምሰን ቅርንጫፍ የመጡት የኮልዝቪል ቅዱሳን እና ሌሎችም በስፍራው ደረሱ (ክፍል ፶፬ን ተመልከቱ)። በዚህ አዲስ መሰብሰቢያ ስፍራ ውስጥ ጌታ ስለነሱ ምን ፈቃድ እንዳለው ለማወቅ ብዙዎቹ ጓጉተው ነበር።

፩–፭፣ በስቃይ የሚጸኑ በክብር ይነገሳሉ፤ ፮–፲፪፣ ቅዱሳኑ ለበጉ ጋብቻ እና ለጌታ እራት ይዘጋጁ፤ ፲፫–፲፰፣ ኤጲስ ቆጶሳት በእስራኤል ውስጥ ፈራጆች ናቸው፤ ፲፱–፳፫፣ ቅዱሳን የአገርን ህግጋት ያክብሩ፣ ፳፬–፳፱፣ ሰዎች ነጻ ምርጫቸውን መልካምን ለማድረግ ይጠቀሙበት፤ ፴–፴፫፣ ጌታ ያዛል ይሽራልም፣ ፴፬–፵፫፣ ንስሀ ለመግባት፣ ሰዎች ኃጢአቶቻቸውን መናዘዝና መተው አለባቸው፤ ፵፬–፶፰፣ ቅዱሳን ውርሳቸውን ገዝተው በሚዙሪ ይሰብሰቡ፤ ፶፱–፷፭፣ ወንጌሉ ለእያንዳንዱ ፍጥረት መሰበክ አለበት።

አድምጡ፣ የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች ሆይ፣ እናም ቃሌንም ስሙ፣ እናም ስለራሳችሁ እና ስለላኳችሁ ስለዚህ አገር ያለኝን ፈቃድም ከእኔ ተማሩ።

እውነት እላችኋለሁ፣ በህይወትም ይሁን በሞት ትእዛዜን የሚጠብቅ የተባረከ ነው፤ እናም በመከራው ታማኝ የሆነው፣ እርሱ በመንግስተ ሰማይ ያለው ዋጋ ታላቅ ይሆናል።

ከዚህ በኋላ ስለሚመጡት ነገሮች አምላካችሁ ያቀደውን፣ እናም ብዙ መከራን ተከትሎ የሚመጣውን ክብር፣ በእዚህ ጊዜ በተፈጥሮ አይኖቻችሁ ልታዩ አትችሉም።

ከብዙ መከራ በኋላ በረከቶች ይመጣሉና። ስለዚህ በብዙ ክብር አክሊልም የምትጭኑበት ቀን ይመጣል፤ ሰአቱ አልደረሰም፣ ነገር ግን እየቀረበ ነው።

በልባችሁ ልታሮሩት እና ቀጥሎ የሚመጣውን ትቀበሉ ዘንድ፣ ይህን አስቀድሜ የምነግራችሁን አስታውሱ።

እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ለዚህ ምክንያት ነው የሰደድኳችሁ—ታዛዥ እንድትሆኑ፣ እና ወደፊት ስለሚመጡት ነገሮች ለመመስከር ልባችሁ እንዲዘጋጁ

ደግሞም የእግዚአብሔር ፅዮን ስለምትሰራበት ምድር መሰረቱን በመገንባት፣ እና ምስክርነቱንም በመስጠት ትከበሩ ዘንድ ነው፤

እና ደግሞም የሶባ ግብዣ ለደሀው እንዲዘጋጅ፤ አዎን፣ የሶባ ግብዣ፣ የሰነበተ ወይን እንዲዘጋጅ፣ ይህም አለም የነቢያት አንደበት እንደማይወድቁ እንዲያውቅ ነው፤

አዎን፣ ሁሉም አገሮች የሚጋበዙበት በደንብ የተዘጋጀው የጌታ ቤት እራት የሆነው ይዘጋጅ ዘንድ ነው።

መጀመሪያ፣ ባለጠጋውና የተማረው፣ ጥበበኛውና መሳፍንቱ፤

፲፩ እና ከዚያም በኋላ የሀይሌ ቀን ይመጣል፤ ከዚያም ደሀው፣ አንካሳው፣ እና አይነ ስውሩም፣ እና ደንቆሮውም ወደ በጉ ጋብቻ ይመጣሉ፣ እናም ለሚመጣው ታላቅ ቀን የተዘጋጀውን የጌታን እራት ይበላሉ።

፲፪ እነሆ፣ እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።

፲፫ እና ምስክርም ከፅዮን፣ አዎን፣ ከእግዚአብሔር ቅርስ ከተማ አንደበት ይሄድ ዘንድ—

፲፬ አዎን፣ ለዚህ ምክንያት ነው ወደዚህ የሰደድኳችሁ፣ እና አገልጋዬ ኤድዋርድ ፓርትሪጅንም የመረጥኩት፣ እናም ተልዕኮውን በዚህ አገር ውስጥ የሰጠሁት።

፲፭ ነገር ግን ያለማመን እና ልበ ደንዳናነት ከሆኑት ኃጢአቶቹ ንስሀ ካልገባ፣ እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።

፲፮ እነሆ ይህ ተልዕኮው ለእርሱ ተሰጥቶታል፣ እናም ዳግመኛም አይሰጥም።

፲፯ በዚህ ተልዕኮ የሚቆመው፣ እንደቀደሙት ቀናት፣ በእስራኤል ፈራጅ እንዲሆን፣ የእግዚአብሔር ቅርስ መሬቶችን ለልጆቹ እንዲያከፋፍል ተመድቧልና፤

፲፰ እናም የእርሱን ሕዝብ በእግዚአብሔር ነቢያት በኩል በተሰጡት የመንግስቱ ህግጋት አማካይነት በጻድቁ ምስክር፣ እናም በአማካሪዎቹ እርዳታም እንዲፈርድ ተመድቧል።

፲፱ እውነት እላችኋለሁና፣ በዚህ አገር ህግጋቴ ይጠበቃል።

ማንም ሰው መሪ ነኝ ብሎ አያስብ፤ ነገር ግን እንደ ፈቃዱ ምክር የሚፈርደውን፣ ወይም በሌላ ቃል፣ የሚመክር ወይም በፍርድ ወንበር የሚቀመጠው እግዚአብሔር እርሱ ይምራው።

፳፩ የአገርን ህግጋት ማንም ሰው አይጣስ፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ህግጋትን የሚጠብቅ የአገርን ህግጋት መጣስ አያስፈልገውምና።

፳፪ ስለዚህ፣ ለመንገስ መብት ያለው እርሱ እስኪነግስ፣ እና ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስከሚያደርግ፣ ባሉት ባለስልጣናት ተገዙ።

፳፫ እነሆ፣ ከእጄ የተቀበላችኋቸው ህግጋት የቤተክርስቲያኗ ህግጋት ናቸው፣ እና በዚህም ብርሀን ያዙአቸው። እነሆ፣ ይህ ጥበብ ነው።

፳፬ እና አሁን ይህ አገር መኖሪያው ስለሆነው አገልጋዬ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ እና አማካሪዎቹ አድርጎ ስለሾማቸውም፤ እናም ጎተራዬን እንዲጠብቅ ተሹሞ በዚህ አገር ስለሚኖረውም ስለእርሱ እናገራለሁ፤

፳፭ ስለዚህ፣ እርስ በራሳቸው እና ከእኔም ጋር እንደሚመክሩት፣ ቤተሰቦቻቸውን ወደዚህ አገር ያምጡ።

፳፮ እነሆ፣ በሁሉም ጉዳዮች ትእዛዝ መስጠቴ ተገቢ አይደለም፤ ምክንያቱም በሁሉም ነገር መገደድ ያለበት እርሱም ሰነፍ ነው እናም ብልህ አገልጋይ አይደለም፤ ስለዚህ ምንም ዋጋን አይቀበልም።

፳፯ እውነት እላችኋለሁ፣ ሰዎች መልካም ስራን በጉጉት ማከናወን፣ እናም ብዙ ነገሮችን በራሳቸው ነጻ ምርጫ ማድረግ፣ እናም ብዙ ጽድቅንም መስራት አለባቸው፤

፳፰ ሀይል በእነርሱ ውስጥ ነውና፣ በዚህም ራሳቸውን ይወክላሉ። እናም ሰዎች መልካም ስራን ከሰሩ ዋጋቸውን አያጡም።

፳፱ ነገር ግን እስኪታዘዝ ድረስ ምንም የማያደርግ፣ እና ትእዛዝን በሚጠራጠር ልብ የሚቀበል፣ እና በስንፍና የሚጠብቅ፣ እርሱ ይፈረድበታል

ሰውን የፈጠርኩ፣ እኔ ማን ነኝ ትእዛዛቴንስ የማያከብረውን ጥፋተኛ እንዳይሆነ የማልይዘው እኔ እኔ ማን ነኝ? አል ጌታ፤

፴፩ ቃል ገብቼ እና ያልፈጸምሁ እኔ ማን ነኝ? ይላል ጌታ፤

፴፪ አዛለሁ እናም ሰዎች አያከብሩም፣ እሸራለሁ እና በረከቶችንም አይቀበሉም።

፴፫ ከዚያም በልባቸው እንዲህ ይላሉ፥ ይህ የጌታ ስራ አይደለም፣ ቃል ኪዳኖቹ አልተሟሉምና። ነገር ግን ለእነዚህ ወዮላቸው፣ ዋጋቸው ከላይ ሳይሆን ከስር አድፍጦ ይጠብቃቸዋልና።

፴፬ እናም አሁን ስለዚህ አገር ሌሎች ተጨማሪ መመሪያዎችን እሰጣችኋለሁ።

፴፭ ገንዘቡን ለቤተክርስቲያኗ ኤጲስ ቆጶስ በመስጠት አገልጋዬ ማርቲን ሀርስ ለቤተክርስቲያኗ ምሳሌ መሆኑ ይህ በእኔ ዘንድ ጥበብ ነው።

፴፮ ደግሞም፣ ውርስን ለመቀበል ወደ እዚህ አገር ለሚመጣ ሰው ሁሉ ይህ ህግ ነው፤ እና በገንዘቡም ህጉ እንደሚመራው ያደርግበታል።

፴፯ ለጎተራ፣ እናም ለማተሚያ ቤት፣ የሚሆን ቦታ በኢንዲፔንደንስም መሬቶች እንዲገዙ ይህም ደግሞ በእኔ ዘንድ ጥበብ ነው።

፴፰ መልካም እንደመሰለው ውርሱን እንዲቀበልም፣ ሌሎች መመሪያዎችም ለአገልጋዬ ማርቲን ሀርስ በመንፈስ ይሰጡታል፤

፴፱ ለኃጢአቱም ንስሀ ይግባ፣ የአለምን ምስጋናን ይፈልጋልና።

እናም አገልጋዬ ውልያም ደብሊው ፈልፕስም በተሾመበት ስልጣን ሀላፊነቱን ያከናውን፣ እናም ውርሱንም በዚህ አገር ይቀበል።

፵፩ እናም እርሱም ንስሀ ይገባ ዘንድ ያስፈልገዋል፣ ምክንያቱም ከሌሎች በላይ ስልጣን ለማግኘት ስለሚፈልግ፣ እናም በፊቴም በበቂ የዋህ ስላልሆነ፣ እኔ ጌታ አልተደሰትኩበትም።

፵፪ እነሆ፣ ለኃጢያቶቹ ንስሀ የሚገባም፣ ይቅርታን ይቀበላል፣ እናም እኔ ጌታ ደግሜ አላስታውሳቸውም

፵፫ በዚህም ሰው ለኃጢአቶቹ ንስሀ እንደገባ ታውቃላችሁ—እነሆ፣ ይናዘዛቸዋል እናም ይተዋቸዋልም

፵፬ እናም አሁን ስለተቀየሩት የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች ይህን እላለሁ፣ በእምነት በሆነ ጸሎት ካልፈለጉ በቀር፣ እና ጌታ ካልመደበላቸው በስተቀር፣ ውርሳቸውን የሚቀበሉበት ጊዜ፣ ገና ብዙ አመታት፣ ይቀራሉ።

፵፭ እነሆ፣ ህዝብን ከአለም ዳርቻዎች ድረስ በአንድነት ይሰበስቧቸዋልና

፵፮ ስለዚህ፣ ራሳችሁን በአንድነት አሰባስቡ፣ እና በዚህ አገር እንዲቀሩ ያልተጠሩትም በአካባቢው ባሉት ክፍለ ሀገሮች ወንጌሉን ይስበኩ፣ እና ከዚያም በኋላ ወደየቤቶቻቸው ይመለሱ።

፵፯ በመንገዳቸውም ላይ ይስበኩ፣ እናም ስለእውነትም በሁሉም ቦታዎች ምስክርነት ይስጡ፣ እናም ባለጠጎችን፣ እናም ከፍ ያሉትንም ሆነ ዝቅ ያሉትን፣ እናም ደሆችንም ንስሀ እንዲገቡ ይጥሯቸው።

፵፰ የምድር ኗሪዎች ንስሀ በሚገቡበት መጠን፣ ቤተክርስቲያኖችን ይመስርቱ።

፵፱ በቤተክርስቲያኗ ድምፅም፣ በኦሀዮ ቤተክርስቲያን፣ በፅዮን ምድር ለመግዛት ገንዘብ የሚቀበል ወኪል ይመረጥ።

እናም ለአገልጋዬ ስድኒ ሪግደን የፅዮን አገርን አገላለፅ፣ እና በመንፈስ እንደሚገለፅለትም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መግለጫ ይፅፍ ዘንድ ትእዛዝን እሰጠዋለሁ፤

፶፩ እናም በኤጲስ ቆጶስ ወይም በወኪሉ እጅ የሚገቡት ገንዘቦች የሚሰበሰቡበት ማዘዣ፣ እርሱም መልካም እንደሚመስለው ወይም እንደሚመራበት ለእግዚአብሔር ልጆች ውርስ መሬት ይገዛ ዘንድ ለሁሉም ቤተክርስቲያኖች ደብዳቤ እና ማዘዣ ያቅርብ።

፶፪ እነሆ እውነት እላችኋለሁ፣ ደቀ መዛሙርቶቹ እና የሰው ልጆች ልባቸውን እንዲከፍቱ፣ እንዲሁም ጊዜ እንደፈቀደ ክፍለ ሀገሩን ሁሉ ይገዛ ዘንድ የጌታ ፍላጎት ነው።

፶፫ እነሆ፣ ይህም ጥበብ ነው። ይህን ያድርጉ ያለበለዚያ ደም ካልፈሰሰ በቀር ምንም ወርስ አይቀበሉምና።

፶፬ ደግሞም፣ የሚገኝ መሬት እስካለ ድረስ፣ የተለያዩ ችሎታ ያላቸው ሰራተኞች ለእግዚአብሔር ቅዱሳን እንዲሰሩ ወደዚህ አገር ይላኩ።

፶፭ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በዕቅድ ይደረጉ፤ ጊዜ በጊዜም ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የቤተክርስቲያኗ ወኪል በምድር ላይ የመስራትን መብት እንዲታወቅ ያድርጉ።

፶፮ የመሰብሰቢያው ስራም በጥድፊያ ወይም በመሯሯጥ አይሁን፤ ነገር ግን ይህም በቤተክርስቲያኗ ጉባኤ ላይ ሽማግሌዎች ከጊዜ ወደጊዜ እንደሚቀበሉት እውቀት መጠን የሚመክሩት ይሁን።

፶፯ አገልጋዬ ስድኒ ርግደን ይህን አገር እና ቤተመቅደስ የሚሰራበትን ስፍራ ለጌታ ይቀድስ እናም ይመርቅ።

፶፰ የጉባኤ ስብሰባም ይጠራ፤ እናም ከዚያም በኋላ አገልጋዮቼ ስድኒ ርግደን እና ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ በመሬታቸው ላይ እንዲያከናውኑ የሰጠኋቸውን እናም ጉባኤዎቹ የመሯቸውን ለማከናወን ይመለሱ፣ እናም ኦሊቨር ካውድሪም ከእነርሱ ጋር ይሂድ።

፶፱ የሚያውቀውን እና በእርግጥ የሚያምነውን በሚጓዝበት መንገድ ሳይሰብክ ማንም ሰው ከዚህ አገር አይመለስ።

ለዛይባ ፒተርሰን የተሰጠው ይወሰድበት፤ እናም የቤተክርስቲያን አባልነቱንም መሆንም ይቀጥል፣ እናም ለኃጢአቶቹ በሚገባ እስከሚገሰጽ ድረስ በራሱ እጅ ከወንድሞች ጋር ይስራ፤ ኃጢአቶቹን ሁሉ አልተናዘዛቸውም፣ እናም ሊደብቃቸው ያስባልና።

፷፩ አንዳንዶቹ መመዘን ከሚቻለው በላይ የተባረኩት ወደዚህ አገር የሚመጡት የቀሩት የቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎችም በጉባኤ በዚህ አገር ውስጥ ይሰብሰቡ።

፷፪ አገልጋዬም ኤድዋርድ ፓርትሪጅም የእነርሱን ጉባኤ ይምራ።

፷፫ እናም በመንገዳቸውም ወንጌልን በመስበክ፣ ስለተገለጡላቸው ነገሮች ምስክር በመስጠት፣ ይመለሱ።

፷፬ በእውነት፣ ድምፅ ከዚህ ስፍራ ወደ አለም ሁሉ፣ እናም ወደ ምድር ዳርቻ ድረስ፣ ሊሄድ ይገባል—የሚያምኑትን በሚከተለው ምልክት፣ ወንጌሉ ለእያንዳንዱ ፍጥረት መሰበክ አለበት።

፷፭ እናም እነሆ የሰው ልጅ ይመጣል። አሜን።