ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፳፰


ክፍል ፻፳፰

ከነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ስለሙታን ጥምቀት ተጨማሪ መመሪያን የያዘ፣ በመስከረም ፮፣ ፲፰፻፵፪ (እ.አ.አ.) በናቩ የተጻፈ ደብዳቤ።

፩–፭፣ የአካባቢ እና አጠቃላይ መዛግብት ስለሙታን መጠመቅ መከናወን ማረጋገጥ አለባቸው፤ ፮–፱፣ ዘገባዎቹም የሚያስተሳስሩ ናቸው እና በምድር እናም በሰማይ የተመዘገቡ ናቸው፤ ፲–፲፬፣ የማጥመቂያ ገንዳው የመቃብር ተምሳሌት ነው፤ ፲፭–፲፯፣ ኤልያስ ከሙታን ጥምቀት ጋር ተዛማጅነት ያለውን ሀይልን ዳግም መለሰ፤ ፲፰–፳፩፣ ያለፉት ዘመናት ቁልፎች፣ ሀይላት፣ እና ስልጣናት ሁሉ ዳግም ተመልሰዋል፤ ፳፪–፳፭፣ አስደሳች እና የከበረ ምስራች ለህያው እና ለሙታን ታውጇል።

ስፍራዬን ትቼ ከመሄዴ በፊት ከጊዜ ወደጊዜ እንደምፅፍላችሁ እና ብዙ ርዕሶችን በሚመለከት መግለጫዎች እንደምሰጣችሁ እንዳመለከትኳችሁ፣ በጠላቶቼ እየተሰደድኩኝ እያለሁ፣ ርእሱ በአዕምሮዬ ውስጥ ስላለ እና በስሜቴ ላይ በብርቱም ስለሚገፋፋኝ፣ ስለሙታን መጠመቅ ርዕስ እቀጥላለሁ።

ዘጋቢውን በሚመለከት ጥቂት የራዕይ ቃላትን ፅፌላችኋለሁ። ይህን ርዕስ በሚመለከት አሁን የማረጋግጣቸው ጥቂት ተጨማሪ አስተያየቶች አሉኝ። ያም፣ ከዚህ በፊት በደብዳቤዬ እንደገለፅኩት፣ የአይን ምስክር የሚሆን፣ እና በጆሮዎቹ ሰምቶ በጌታ ፊት እውነትን ይመዝገብ ዘንድ ዘጋቢ ማስፈለጉን ነው።

አሁን፣ ከዚህ ጉዳይ ጋር በሚገናኝም፣ ለአንድ ዘጋቢ በሁሉም ጊዜያት ለመገኘት እና ሁሉንም ስራዎች ያከናውን ዘንድ አዳጋች መሆኑን ነው ይህን ችግር ለማስወገድ፣ በእያንዳንዱ ከተማው ዎርዶች የስብሰባ መዛግብትን ያለስህተት ለመጻፍ ብቁ የሆነ ዘጋቢ ለመመደብ ይቻላል፤ እና ቃል ጉባኤውን ለመጻፍም፣ በአይኑ እንዳያቸውና በጆሮዎቹ እንደሰማቸው፣ ቀናትን፣ ስሞችን፣ እና ሌሎችን፣ እና የጉዳይን ሁሉ ታሪኮችን በመመዝገብ፣ መዝገቡን በማረጋገጥ በጣም ጥንቁቅ እና ትክክለኛ ይሁን፤ እሰጣችኋለው፤ በሁለት ወይም በሶስት አንደበት ምስክርነት ሁሉም ቃል ይጸና ዘንድ በዚያ ከነበሩም፣ በሚጠሩበት በማንኛውም ጊዜ ይህን ለማረጋገጥ የሚችሉ የነበሩትን ሶስት ግለሰቦችን ስም ይጻፍም።

ከዚያም፣ ዘገባው እውነት እንደሆነ የሚያስረዳ የፈረመባቸውን የምስክር ወረቀቶች የሚቀበል አጠቃላይ ዘጋቢም ይኑር። ከዚያም የ ቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ ዘጋቢ በአጠቃላይ በ ቤተክርስቲያኗ መፅሀፍ ውስጥ ከምስክር ወረቀቶች እና ከነበሩት ምስክሮች ጋር በቤተክርስቲያኗ የተመደቡትን ሰዎች አጠቃላይ ጸባይ እውቀቱን በመጠቀም የተጻፈውን መዝገብ እውነትኛነት እና መዛግብቱም እውነት እንደሆኑ እንደሚያምንም ሊፅፋቸው ይችላል። እና ይህም በአጠቃላይ ቤተክርስቲያኗ መፅሀፍ ውስጥ ሲደረግ፣ መዝገቡም ቅዱስ ይሆናል፣ እና ስነስርዓቱም ልክ በአይኖቹ እንዳያቸው፣ በጆሮዎቹ እንደሰማቸው፣ እና በአጠቃላይ በቤተክርስቲያኗ መፅሀፍ ውስጥም እንደመዘገባቸው ይሆናል።

የእነዚህን ነገሮች ስርዓት በጣም የተለየ ነው በማለት ታስቡ ይሆናል፤ ነገር ግን ይህም የወንጌሉ እውቀት ሳይኖራቸው ለሞቱት ለሙታን ደህንነት ጌታ ከአለም መመስረት በፊት የሾመውን እና ያዘጋጀውን ስርዓት እና ዝግጅትን በመከተል የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማሟላት ብቻ እንደሆነ ልንገራችሁ።

በተጨማሪም፣ በራዕይ ፳፥፲፪ ውስጥ ተመዝግቦ እንደምታገኙት፣ ባለራዕዩ ዮሐንስ ስለሙታን ርዕስ ሲያሰላስል እንዲህ ነበር ያወጀው—ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በእግዚአብሔር ፊት ቆመው አየሁ፥ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።

በዚህ ጥቅስ ውስጥም መፅሀፍት ተከፍተው እንደነበርም ታገኛላችሁ፤ እና ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተፈረደባቸው፤ በዚህም ምክንያት፣ የተነገረላቸውም መፅሀፍት ስራዎቻቸውን ዘገባ የያዙ መሆን አለባቸው፣ እና በምድር ላይ ተጠብቀው ያሉትን መዛግብት የሚጠቅስ ነው። እና የህይወት መፅሀፍ የሆነው መፅሀፍም በሰማይ ውስጥ የተጻፈው መዝገብ ነው፤ ይህም መሰረታዊ መርህ ስፍራዬን ትቼ ከመሄዴ በፊት በላኩላችሁ ደብዳቤ ውስጥ የነበረው ትእዛዝ ከሰጣችሁ ራዕይ ጋር በግልፅም ይስማማል—መዛግብቶቻችሁ ሁሉ በሰማይ የተመዘገቡ ናቸው።

አሁን፣ ለዚህ ስነስርዓት መሰረት የሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ራዕይ አማካይነት የሚገኘው የክህነት ሀይል ነው፣ በዚህም በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፣ እና በምድርም የፈታችሁ ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል። ወይም፣ በሌላ ቃላት፣ የትርጉሙን ሌላ አስተያየት በመውሰድ፣ በምድር የመዘገባችሁት ሁሉ በሰማይ የተመዘገበ ይሆናል፣ እና በምድርም የማትመዘግቡትም ሁሉ በሰማያት አይመዘገብም፤ ለደህንነታቸው እግዚአብሔር አለም ከመፈጠሩ በፊት ባዘጋጀው ስርዓት መሰረት፣ ስለሙታናቸው በተጠበቁት መዛግብቶቻቸው መሰረት እነዚህን ስነስርዓቶች ለራሳቸው ወይም በወኪላቸው ቢያከናውኑትም፣ ከመጻህፍቱ መሰረት፣ ሙታናችሁ እንደ ስራቸው ይፈረድባቸዋል።

የተነጋገርንበት—በምድር የሚመዘገበው ወይም የሚያስረው እና በሰማይ የሚያስረው ሀይል ለአንዳንዱ በጣም ደፋር የሆነ ትምህርት ይመስላል። ይሁን እንጂ፣ በአለም ዘመናት ሁሉ፣ ጌታ ለማንም ሰው፣ ወይም ለተለያዩ ሰዎች፣ በእውነት ራዕይ የክህነት ዘመንን በሚሰጥበት በማንኛውም ጊዜ ይህ ሀይል ዘወትር ይሰጣል። ከዚህ በኋላ፣ በስልጣን፣ በጌታ ስም፣ እነዚህ ሰዎች ምንም ቢያደርጉ፣ እና በእውነት እና በታማኝነት ቢያደርጉት፣ እና የእነዚህን ትክክለኛ እና የታመኑ መዛግብትን ቢጠብቁ፣ በምድር ላይ እና በሰማያት ውስጥ ህግ ይሆናል፣ እና በታላቁ ያህዌህ ህግጋት መሰረት ሊሰረዝም አይችልም። ይህም የታመነ አባባል ነው። ማን ይሰማዋል?

ደግሞም፣ አስቀድሞ ስለተፈጸመው፣ ማቴዎስ ፲፮፥፲፰፣ ፲፱እኔም እልሀለሁ፣ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፣ የሲዖል ደጆችም አያሸንፏትም። የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሀለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፣ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።

፲፩ አሁን የዚህ ጉዳይ ታላቅ እና የከበረው ሚስጥር፣ እና በፊታችን የተዘረጋው እጅግ የላቀው መልካም ነገር የቅዱስ ክህነት ሀይላትን በማግኘት ላይ የተመሰረተ ነው። እነዚህ ቁልፎች ለተሰጡትም ለእርሱ ስለሰው ልጆች፣ ስለሙታን እና ህያዋን ደህንነት በሚመለከት ተጨባጭ እውቀትን ለማግኘት ችግር አይኖርም።

፲፪ በዚህም ውስጥ ግርማ እና ክብርህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት አለ—የውሀ ጥምቀት ስነስርዓት፣ በዚህም በሞት ምሳሌነት መጥለቅ፣ አንዱ መሰረታዊ መርህ ከሌላው ጋር እንዲስማማ፤ በውሀ ውስጥ መጠለቅና ከውሀው መውጣት እንደ ሟች ከመቃብር በትንሳኤ በሚነሱበት ምሳሌ ነው፤ ከዚህ በኋላም፣ ይህ ስነስርዓት የተመሰረተውም እንደ ሞት አምሳል የሆነው የሙታን ጥምቀት ስነስርዓትን ግንኙነት ለመስራት ነው።

፲፫ በዚህም ምክንያት፣ የማጥመቂያ ገንዳው የተመሰረተው በመቃብር አምሳል ሲሆን በዝቅተኛ ስፍራም የሚቀመጥ ሆኖ፣ እና አንዱም ከሌላው ጋር ይወያይ ዘንድ ለህያዋንም ሆነ ለሙታን ሁሉም ነገር አምሳያ እንዳለው ለማሳየት ህያዋን እንዲሰበሰቡ የታዘዙበት ስፍራ ነው—ጳውሎስ እንዳወጀውም፣ ምድራዊው ከሰማያዊ ጋር ይስማማ ዘንድ ነው፣ ፩ ቆሮንቶስ ፲፭፥፵፮፣ ፵፯፣ እና ፵፰

፲፬ ነገር ግን አስቀድሞ ፍጥረታዊው ቀጥሎም መንፈሳዊው ነው እንጂ መንፈሳዊው መጀመሪያ አይደለም። የፊተኛው ሰው ከምድር ምድራዊ ነው፤ ሁለተኛው ሰው ከሰማይ የመጣ ጌታ ነው። ምድራዊው እንደ ሆነ ምድራዊ የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው፥ ሰማያዊው እንደ ሆነ ሰማያዊ የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው። በእውነትም የተመዘገቡት፣ የዚያንም ሙታናችሁን በሚመለከትም ምድራዊ መዛግብት እንዳሉ ሁሉ፣ የሰማያዊ መዛግብትም ይኖራሉ። ስለዚህ ይህም የሚያትም እና የሚያስተሳስር ሀይል ነው፣ እና ቃሉም በአንድ ትርጉም፣ በእውቀት ቁልፍ ላይ የተመሰረቱ የመንግስት ቁልፎች ናቸው።

፲፭ አሁንም፣ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ደህንነታችንን በሚመለከትም፣ እነዚህ ሙታንንና ህያዋንን የሚመለከቱ መሰረታዊ መርሆች በቀላል እንደማይታለፉ ላረጋግጥላችሁ። ደህንነታቸውም ለእኛ ደህንነት አስፈላጊ እና መሰረታዊ ነው፣ ጳውሎስ ስለአባቶች እንዳለው—ያለ እኛ ፍጹማን ሊሆኑ አይችሉም—ወይም እኛ ያለሙታኖቻችን ፍጹም ልንሆን አንችልም።

፲፮ አሁንም፣ የሙታን ጥምቀት በሚመለከት፣ ሌላ የጳውሎስን ጥቅስ እሰጣችኋለሁ፣ ፩ ቆሮንቶስ ፲፭፥፳፱እንዲያማ ካልሆነ፣ ስለ ሙታን የሚጠመቁ ምን ያደርጋሉ? ሙታንስ ከቶ የማይነሡ ከሆነ፣ ስለ እነርሱ የሚጠመቁ ስለ ምንድር ነው?

፲፯ ደግሞም፣ ከዚህ ጥቅስ ጋር በተገናኘ አይኑን በክህነት ስልጣን ዳግም መመለስ ላይ፣ በመጨረሻዎቹ ቀናት ላይ ለሚገለጡት ክብሮች፣ እና ከሁሉም ርእሶች በላይ የከበረው ይህ፣ እንዲሁም ለሙታን መጠመቅ በዘለአለም ወንጌል ክፍል ስለሆነው ትኩረትን ሰጥቶት ከነበረው ከነብያቱ የአንዱን ጥቅስ እሰጣችኋለሁ፤ በመጨረሻው ምዕራፍ፣ አንቀፅ ፭ እና ፮ ውስጥ ሚልክያስ እንዳለው፥ እነሆ፣ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ። መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፣ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።

፲፰ ለዚህም ግልጽ የሆነ ትርጉም ለመስጠት በቻልኩ ነበር፣ ነገር ግን እንዳለም አላማዬን ያሟላ ዘንድ ይህ በቂ ነው። በዚህ ጉዳይ፣ በአባቶች እና ልጆች መካከል በአንድ በተወሰነ ርዕስ ወይም በሌላ፤ አንድ ወይም ሌላ የሚያስተሳስር ግንኙነት ከሌለ ምድር በእርግማን እንደምትመታ ማወቁ በቂ ነው—እና እነሆ ያ ርዕስ ምንድን ነው? ይህም ለሙታን መጠመቅ ነው። ያለእነርሱ ፍጹም ልንሆን አንችልም፤ ወይም እነርሱም ያለእኛ ፍጹማን ሊሆኑ አይችሉም። እነርሱም ይሁን እኛ በወንጌሉ ካልሞቱት በስተቀር ፍጹም ልንሆን አንችልም፤ አሁን መግባት በጀመረው የዘመን ፍጻሜ መግቢያ ውስጥ ሙላት እና የተፈጸመ እና ፍጹም አንድነት፣ እና ከአዳም ቀናት እስከ አሁን የተገለጡት የዘመናት፣ ቁልፎች፣ እና ሀይላት፣ እና ክብሮች መተሳሰራቸው አስፈላጊ ነውና። እና ይህም ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን ከዚህ ምድር መመስረት ጀምሮ ያልተገለጡት፣ ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ተሰውረው የነበሩት፣ እነዚያ ነገሮች ለህጻናት እና ለሚጠቡት በዚህ በዘመን ፍጻሜ ይገለጣሉ።

፲፱ አሁን፣ በተቀበልነው ወንጌል ውስጥ ምን እንሰማለን? የደስታ ድምፅ! የምህረት ድምፅ ከሰማይ፤ እና ከምድር ውስጥም የእውነትን ድምፅ፤ የምስራች ዜና ለሙታን፤ ከህያውና ከሙታን የደስታ ድምፅ፤ የታላቅ ደስታን የምስራች ነው። የምስራች የሚናገር፣ ሠላምን የሚያወራ፣ የመልካምን ወሬ የምስራች የሚናገር፣ ስለመዳን የሚያወራ፣ ፅዮንንም አምላክሽ ነግሶአል! የሚል ሰው እግሮቹ በተራሮች ላይ እጅግ እንዴት ያማሩ ናቸው። እንደ ቀርሜሎስ ጠል፣ እንደዚህም የእግዚአብሔር እውቀት በእነርሱ ላይ ያርፋል!

ደግሞም፣ ምን እንሰማለን? ከከሞራ የደስታ ዜና! የሰማይ መልአክ ሞሮኒ የነቢያትን ፍጻሜ—የሚገለጠውን መፅሀፍ ሲያውጅ። የጌታም ድምፅ በፈየት፣ በሰነካ የግዛት ክፍል ዱር ውስጥ ሶስቱ ምስክሮች ስለመፅሐፉ እንዲመሰክሩ ሲያውጅ! የሚካኤል ድምፅም በሰስኳሀና ወንዝ ዳር ዲያብሎስን እንደ ብርሀን መልአክ ሲቀርብ በማየት ሲመረምር! የጴጥሮስ፣ የያዕቆብ፣ እና የዮሐንስ ድምፅ በበረሀ ውስጥ በሀርመኒ፣ ሰስኳሀና የግዛት ክፍል ውስጥ እና በኮልስቪል፣ ብሩም የግዛት ክፍል ውስጥ በሰስኳሀና ወንዝ ላይ ራሳቸውን እንደ መንግስት እና እንደ ዘመን ፍጻሜ ቁልፎች ያዥ በመግለፅ ሲያውጁ!

፳፩ ደግሞም፣ በአረጋዊው አባት ዊትመር ቤት ውስጥ በፈየት፣ ሰነካ የግዛት ክፍል ውስጥ እና በተለያዩ ጊዜያት፣ እና በተለያዩ ስፍራዎች በየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ጉዞዎች እና ፈተናዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ድምፅ! እና ሚካኤል የመላእክት አለቃ ድምፅ፤ የገብርኤልየሩፋኤል፣ እና የተለያዩ መላዕክት፣ ከሚካኤል ወይም ከአዳም እስከ አሁን ዘመን ድረስ፣ በትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ፣ በስርዐት ላይ ስርዐትን፣ ጥቂት በዚህ፣ ጥቂት በዚያ በመስጠት፤ ወደፊት የሚመጣውን በማወጅ፣ ተስፋችንን በማረጋገጥ፣ ማፅናኛ በመስጠት፣ ሁሉም ዘመኖቻቸውን፣ መብቶቻቸውን፣ ቁልፎቻቸውን፣ ክብሮቻቸውን፣ ምስጋናዎቻቸውን፣ እና ክብሮቻቸውን፣ እና የክህነት ሀይሎቻቸውን ሲያውጁ ነው!

፳፪ ወንድሞች፣ ለዚህ ታላቅ ስራ ወደፊት አንሄድምን? ወደኋላ ሳይሆን ወደፊት ሂዱ። በርቱ፣ ወንድሞች፤ እና ወደ ድል ሂዱ! ልባችሁ ይደሰቱ፣ እና በጣምም ተደሰቱ። ምድርም በድንገት ትዘምር። ሙታንም ከአለም ፍጥረት በፊት ለተመደበው፣ ከወህኒም እንድናድናቸው ስላስቻለን ለንጉስ አማኑኤል የዘለአለማዊ ምስጋና መዝሙርን ይናገሩ፤ እስረኞቹ በነጻ ይሄዳሉና።

፳፫ ተራሮችም በደስታ ይጩሁ፣ እና ሸለቆዎች ሁሉ በጎላ ድምፅ አልቅሱ፤ እና እናንት ባህሮች እና ደረቅ ምድራት ሁሉ የዘለአለም ንጉሳችሁን አስደናቂነት ተናገሩ! እና እናንት ወንዞች፣ እና ጅረቶች፣ እና ትንንሽ ወንዞችም በደስታም ፍሰሱ። የሜዳው ጫካዎች እና ዛፎች ሁሉ ጌታን ያመስግኑ! እና እናንት ጠንካራ አለቶችም በደስታ አልቅሱ። እና ጸሀይ፣ ጨረቅ፣ እና የአጥቢያ ኮኮቦችም በአንድነት ዘምሩ፣ እና የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በደስታ እልል በሉ። እና ዘለአለማዊ ፍጥረቶችም ስሙን ለዘለአለም ያውጁ። ደግሞም እላለሁ፣ በጆሮዎቻችን ስለክብር፣ እና ደህንነት፣ እና ህያውነት፣ እና ስለዘለአለማዊ ህይወት፤ ስለመንግስታት፤ አለቅነትና ስልጣናት የሚያውጀው ከሰማያት የምንሰማው ድምጽ እንዴት የከበረ ነው!

፳፬ እነሆ፣ የጌታ ታላቅ ቀን ቀርቧል፤ እና ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው? ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን ያቀርቡ ዘንድ፣ እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል። ስለዚህ፣ እንደ ቤተክርስቲያንና እንደ ህዝብ እና እንደ የኋለኛውም ቀን ቅዱሳን የፅድቅ ለጌታ መጽዋዕትን እናቅርብ፤ እና በመጨረሻም በቅዱስ ቤተመቅደሱ ውስጥ፣ ለተቀባይነት ሁሉ ብቁ የሆነውን የሙታናችንን መዛግብት የያዘውን መፅሀፍ እናቅርብ።

፳፭ ወንድሞች፣ በዚህ ርዕስ ላይ የምላችሁ ብዙ ነገሮች አሉኝ፤ ነገር ግን ለጊዜው አበቃለሁ፣ እና ርዕሱንም በሌላ ጊዜ እቀጥላለሁ። እኔ፣ እንደ ወትሮው ሁሉ፣ ትሁት አገልጋያችሁ እና የማይቀየር ባልንጀራችሁ ነኝ፣

ጆሴፍ ስሚዝ።