ክፍል ፹፬
በመስከረም ፳፪ እና ፳፫፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። በመስከረም ወር ውስጥ፣ ሽማግሌዎች ከምስራቅ ስቴቶች ተልዕኮአቸው መመለስ እናም የአገልግሎታቸውን ሀተታ ማቅረብ ጀምረው ነበር። በዚህ የደስታ ዘመን ውስጥ አብረው እያሉ ነው ይህ መልእክት የመጣው። ነቢዩ ይህንንም የክህነት ራዕይ በማለት ሰይሞታል።
፩–፭፣ አዲሲቷ ኢየሩሳሌም እና ቤተመቅደሱ በሚዙሪ ውስጥ ይገነባሉ፤ ፮–፲፯፣ የክህነት ዘር ከአዳም እስከ ሙሴ ድረስ ተሰጥቷል፤ ፲፰–፳፭፣ ታላቁ ክህነት የእግዚአብሔርን እውቀት ቁልፍ ይዟል፤ ፳፮–፴፪፣ አነስተኛው ክህነት የመላእክትን አገልግሎት እና የማዘጋጃውን ወንጌል ቁልፍ ይዟል፤ ፴፫–፵፬፣ ሰዎች ዘለአለማዊ ህይወትን የሚያገኙት በክህነት ስልጣን መሀላ እና ቃል ኪዳን በኩል ነው፤ ፵፭–፶፫፣ የክርስቶስ መንፈስ ለሰዎች ያበራላቸዋል፣ እናም አለም በኃጢአት ተይዟል፤ ፶፬–፷፩፣ ቅዱሳን ስለተቀበሉት ነገሮች መመስከር አለባቸው፤ ፷፪–፸፮፣ እነርሱም ወንጌሉን ይስበኩ፣ ምልክቶችም ይከተላሉ፤ ፸፯–፺፩፣ ሽማግሌዎች ካለ ኮረጆም ወይም ከረጢት ይሂዱ፣ እናም ጌታ ለፍላጎታቸው ይንከባከባቸዋል፤ ፺፪–፺፯፣ ወንጌልን የሚቃወሙ ወረርሽኝ እና እርግማን ይጠብቃቸዋል፤ ፺፰–፻፪፣ ስለ ፅዮን መዳን የሚዘመረው አዲስ መዝሙር ተሰጥቷል፤ ፻፫–፻፲፣ እያንዳንዱም ሰው በሀላፊነቱ ይቁም እናም በጥሪውም ያገልግል፤ ፻፲፩–፻፳፣ የጌታ አገልጋዮች የመጨረሻ ቀናት የጥፋት ርኵሰትን ያውጁ።
፩ ለአገልጋዩ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ እና ለስድስት ሽማግሌዎች፣ በልባቸው አንድ ሲሆኑ እና ድምጻቸውን ወደላይ ከፍ ሲያደርጉ የተሰጠ የኢየሱስ ክርስቶስ ራዕይ።
፪ አዎን፣ በነብያቱ አንደበት እንደተናገረው፣ ለህዝቦቹ ዳግም መመለስ፣ እናም አዲሲቷ ኢየሩሳሌም ከተማ በምትሆነው፣ በፅዮን ተራራ በመቆም ለቅዱሳኑ መሰብሰቢያ እንድትሆን በመጨረሻዎቹ ቀናት የተመሰረተችውን ቤተክርስቲያን በተመለከተ ጌታ የተናገረው ቃል።
፫ ያም ከተማ፣ በጌታ ጣት በሚዙሪ ስቴት ምዕራፍ ድንበር ውስጥ በተመደበው፣ እና በጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ እና ጌታ በተደሰተባቸው እጅ በተመረቀው፣ በቤተመቅደስ ቅንጣት ምድር ተጀምሮ ይገነባል።
፬ እውነት ይህ የጌታ ቃል ነው፣ የአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ከተማ በሚሰበሰቡት ቅዱሳን፣ በዚህ ስፍራ፣ እንዲሁም በቤተመቅደስ ስፍራ ተጀምራ ትገነባለች፣ ይህም ቤተመቅደስ በዚህ ትውልድ ይሰራል።
፭ በእውነትም ለጌታ ቤት እስከሚገነባ ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍምና፣ እናም ደመናም ያርፍበታል፣ ደመናውም ቤቱን የሚሞላው የጌታ ክብር ይሆናል።
፮ እናም የሙሴ ልጆች፣ በአማቱ በዮቶር እጆች በኩል በተቀበለው ቅዱስ ክህነት፤
፯ እናም ዮቶር በካሌብ እጅ ይህን ተቀበለ፤
፰ እና ካሌብም ይህን ከኢሊዮ እጅ ተቀበለ፤
፱ ኢሊዮ ይህን ከጀርሚ እጅ ተቀበለ፤
፲ እናም ጀርሚም ይህን ከጋድ እጅ ተቀበለ፤
፲፩ እና ጋድም ከኢሳይያስ እጅ፤
፲፪ እናም ኢሳይያስም ይህን ከእግዚአብሔር እጅ ተቀበለ።
፲፫ ኢሳይያስም በአብርሐም ቀናት ኖረ፣ እናም በእርሱም ተባርኮ ነበር—
፲፬ ይህም አብርሐም ክህነትን፣ እስከ ኖሀ ድረስ ከነበሩት ከአባቶቹ ዘሮች በተቀበለው ከመልከ ጼዴቅ ተቀበለ፤
፲፭ እናም ከኖህ እስከ ሄኖክ፣ በአባቶቻቸው ዘር በኩል ተቀበሉ፤
፲፮ እናም ከሄኖክም በወንድሙ ሽመቃ ምክንያት ወደተገደለው፣ በእግዚአብሔር ትእዛዛት ምክንያት የመጀመሪያው ሰው በነበረው በአባቱ አዳም እጅ ክህነትን ወደተቀበለው አቤል—
፲፯ ይህም ክህነት በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን በሁሉም ትውልዶች የሚቀጥል፣ እና ለቀናቱ መጀመሪያ ወይም ለአመታቱ መጨረሻ አመታት የሌለው ነው።
፲፰ እናም ጌታ ክህነትን በአሮን እና በዘሮቹ ላይ፣ በሁሉም ትውልዶች ውስጥ፣ አረጋገጠ፣ ይህም ክህነት ደግሞም ይቀጥላል እናም በቅዱሱ የእግዚአብሔር ስርዓት በኩል የሆነው ክህነት ለዘለአለምም ይቀጥላል።
፲፱ እናም ይህም ታላቅ ክህነት ወንጌሉን ያስተዳድራል እናም የመንግስቱን ሚስጥር ቁልፎች፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን እውቀት ቁልፎችን፣ ይዟል።
፳ ስለዚህ፣ በዚህም ስርዓት ውስጥ፣ የአምላክ አይነት ሀይል ይታያል።
፳፩ ካለዚህም ስርዓት፣ እናም ካለክህነት ስልጣን፣ የአምላክነት ሀይል ለሰዎች በስጋ አይታይም።
፳፪ ካለዚህ ማንም ሰው የእግዚአብሔርን ፊት፣ እንዲሁም አብን፣ ለመመልከት እና ለመኖር አይችልም።
፳፫ አሁን ሙሴ በምድረበዳ ይህን ለእስራኤል ልጆች በግልፅ አስተማረ፣ እናም የእግዚአብሔርን ፊት ይመለከቱ ዘንድ እንዲችሉም ህዝቦቹን ለመቀደስ በትህትና ፈለገ፤
፳፬ ነገር ግን፣ ልቦቻቸውን አደነደኑ እናም በእርሱም ፊት ለመፅናት አልቻሉም፤ ስለዚህ፣ ጌታ በቁጣው፣ ንዴቱ በእነርሱ ላይ ስለተቀጣጠለ፣ በምድረበዳ ሳሉ ሁሉ ክብሩ ወደሆነው እረፍቱ አይገቡም ብሎ መሀላ ገባ።
፳፭ ስለዚህ፣ ሙሴን፣ እናም ደግሞም ቅዱስ ክህነትን ከመካከላቸው ወሰደ፤
፳፮ እናም የመላእክትን አገልግሎት ቁልፍን እና የመዘጋጃ ወንጌሉን የያዘው፣ አነስተኛው ክህነትም ቀጠለ።
፳፯ ይህም ወንጌል፣ ጌታ በቁጣው በአሮን ቤት በእስራኤል ልጆች መካከል ከእናቱ ማኅፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ እስከተሞላው፣ እግዚአብሔር እስካነሳው ዮሐንስ ድረስ እንዲቀጥል ያደረገው የንስሀ እና የጥምቀት፣ እና የኃጢአት ስርየት፣ እና የስጋዊ ትእዛዛት ህግ ወንጌል ነው።
፳፰ በልጅነቱም ሳለ ነበር የተጠመቀው፣ እናም በስምንት ቀን እድሜውም፣ የአይሁድን መንግስት ለመጣል፣ እና በእጆቹ ሁሉም ሀይል ለተሰጠው ጌታ መምጫ ያዘጋጀው እና በህዝቦቹም ፊት የጌታን መንገድ ያቀና ዘንድ ወደዚህ ሀይል በእግዚአብሔር መልአክ ተሹሞ ነበር።
፳፱ እና ደግሞም፣ የሽማግሌ እና የኤጲስ ቆጶስ ሀላፊነትም ከታላቁ ክህነት ጋር አስፈላጊ ሆኖ የተያያዘ ነው።
፴ እና ደግሞም፣ የመምህር እና የዲያቆን ሀላፊነትም፣ በአሮን እና በልጆቹ ላይ ከተረጋገጠው፣ ከአነስተኛው ክህነት ጋር አስፈላጊ ሆነው የተያያዙ ናቸው።
፴፩ ስለዚህ፣ የሙሴን ልጆች በተመለከተ እንዳልኩትም—የሙሴ ልጆች እና ደግሞም የአሮን ልጆች ተቀባይ የሆነውን የሚቃጠል መሥዋዕትንና ሌላ መሥዋዕትን በጌታ ቤት ውስጥ፣ በዚህ ትውልድ ለጌታ በተቀደሰው ስፍራ እንደመደብኩት በሚገነባው ቤት፣ ያቀርባሉ—
፴፪ እናም የሙሴ እና የአሮን ወንድ ልጆችም፣ እነርሱም እናንተ ናችሁ፣ በፅዮን ተራራ ላይ በጌታ ቤት ውስጥ በጌታ ክብር ይሞላሉ፤ እና ደግሞም የጠራኋቸውና ቤተክርስቲያኔን እንዲገነቡ የላኳቸውም የእነርሱ ልጆች ናቸው።
፴፫ እነዚህን የተናገርኩባቸውን ሁለት ክህነቶች በማግኘት እና ጥሪያቸውን ለማጉላት ታማኝ የሆኑት፣ ሰውነታቸውን በማደስ በመንፈስ ይቀደሳሉና።
፴፬ እነርሱም የሙሴ እና የአሮን ወንድ ልጆች፣ እናም የአብርሐም ዘር፣ እና ቤተክርስቲያንና መንግስት፣ እናም በእግዚአብሔር የተመረጡ ይሆናሉ።
፴፭ እና ደግሞም ይህን ክህነት የሚቀበሉትም ሁሉ እኔን ይቀበሉኛል፣ ይላል ጌታ፤
፴፮ አገልጋዮቼን የሚቀበል እኔን ይቀበለኛልና፤
፴፯ እናም እኔን የሚቀበለኝም አባቴን ይቀበላል፤
፴፰ እናም አባቴን የሚቀበልም የአባቴን መንግስት ይቀበላል፤ ስለዚህ አባቴ ያለው ሁሉ ለእርሱም ይሰጠዋል።
፴፱ እናም ይህም በክህነት ባለ መሀላ እና ቃል ኪዳን መሰረት ነው።
፵ ስለዚህ፣ ይህን ክህነት የሚቀበሉም፣ ሊሰበር የማይችለውን፣ ወይም ሊጠፋ የማይቻለውን፣ ይህን መሀላ እና ቃል ኪዳን ከአባቴ ዘንድ ይቀበላሉ።
፵፩ ነገር ግን ከተቀበለው በኋላ ይህን ቃል ኪዳን የሚሰብረው፣ እና ከዚህም ሁሉ የሚዞርም፣ በዚህ አለምም ሆነ በሚመጣው አለም ለኃጢአቱ ምህረት አያገኝም።
፵፪ እናም እናንተ ወደተቀበላችሁት፣ በዚህ ቀን ለምትገኙትም ከሰማያት በራሴ ድምፅ ወዳረጋገጥሁላችሁ ክህነት ለማይመጡም ወዮላቸው፤ እናም የሰማይ ሰራዊትን እና መላእክቴን እናንተን በሚመለከት ሀላፊነት ሰጥቻቸዋለሁ።
፵፫ እና አሁንም ራሳችሁን በተመለከተ እንድትጠነቀቁም፣ ለዘለአለም ህይወት ቃላትም በትጋት ታደምጡ ዘንድ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።
፵፬ ከእግዚአብሔር አንደበት ከሚመጣው እያንዳንዱ ቃልም ትኖራላችሁና።
፵፭ የጌታ ቃል እውነት ነውና፣ እናም እውነት የሆነውም ብርሀን ነው፣ እናም ብርሀን የሆነውም መንፈስ፣ እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ነው።
፵፮ እናም መንፈስም ወደአለም ለሚመጣው ለእያንዳንዱ ሰው ብርሀን ይሰጣል፤ እናም መንፈስም በአለም ውስጥ ያለውን የመንፈስን ድምፅ ለሚያደምጥ ሰው ሁሉ ያበራለታል።
፵፯ እናም የመንፈስን ድምፅ የሚያደምጠው እያንዳንዱም ሰው ወደ እግዚአብሔር፣ እንዲሁም ወደአብ፣ ይመጣል።
፵፰ እናም አብም ያደሰውን እና በእናንተ ያረጋገጠውን ቃል ኪዳን ያስተምረዋል፣ ይህንንም ያረጋገጠው ለእናንተ ጥቅም ነው፣ እናም ለእናንተ ጥቅም ብቻ ሳይሆን ለአለም ሁሉ ጥቅም ነው።
፵፱ እና አለምም ሁሉ በኃጢአት ተይዟል፣ እናም በጭለማ እና በኃጢአት ባርነት ስር ያቃስታል።
፶ እናም በዚህም በኃጢአት ባርነት ስር እንደሆኑም ታውቃላችሁ፣ ምክንያቱም ወደእኔ አይመጡምና።
፶፩ ወደእኔ የማይመጣው በኃጢአት ባርነት ስር ነውና።
፶፪ እናም ድምጼን የማይቀበልም ከድምጼ ጋር የተዋወቀ አይደለም፣ እናም ከእኔ አይደለም።
፶፫ እናም በዚህም ጻድቃንን ከኃጥአን ትለያላችሁ፣ እናም አሁንም አለም ሁሉ በኃጢአት እና ጭለማ ስር እንደሚያቃስቱ ታውቃላችሁ።
፶፬ እናም ባለፉት ጊዜያት አዕምሮአችሁ ባለማመን ምክንያት ጨልሞባችሁ ነበር፣ እናም የተቀበላችሁትን እንደተራ ተቀበላችሁታልና—
፶፭ ክንቱነት እና ያለማመን መላዋን ቤተክርስቲያን በፍርድ ላይ አድርገዋል።
፶፮ እናም ይህም ፍርድ በፅዮን ልጆች፣ እንዲሁም በሁሉም ላይ ያርፋል።
፶፯ እና እነርሱም ንስሀ እስኪገቡ እና አዲሱን ቃል ኪዳን፣ እንዲሁም መፅሐፈ ሞርሞንን እና የሰጠኋቸውን የወደፊት ትእዛዛትን፣ በመናገር ብቻ ሳይሆን በጻፍኳቸው መሰረት በማድረግ እስከሚያስታውሱ ድረስ ከዚህ ፍርድ በታች ይቆያሉ—
፶፰ ይህንንም የሚያስታውሱት ለአባታቸው መንግስትም የሚገባ ፍሬ ያመጡ ዘንድ ነው፤ አለበለዚያም መቅሰፍት እና ፍርድ በፅዮን ልጆች ላይ ይወርድባቸዋል።
፶፱ የመንግስት ልጆች ቅዱስ ምድሬን ይበክላሉን? በእውነት፣ እላችኋለሁ፣ አይበክሉም።
፷ በእውነትም፣ ድምጼ የሆናችሁ እናንተ፣ ቃላቴን አሁን ለምትሰሙ ይህን እላችኋለሁ፣ እነዚህን ነገሮች እስከተቀበላችሁ ድረስ የተባረካችሁ ናችሁ፤
፷፩ በአእምሮአችሁ በእርጋታ እና በጸሎት መንፈስ፣ በመሆን የሰማችሁትንም እነዚያን ነገሮች ለአለም ትመሰክሩ ዘንድ—በዚህ ትእዛዝ ኃጢአታችሁን ይቅር እላለሁና።
፷፪ ስለዚህ፣ ወደ አለም ሁሉ ሂዱ፤ እናም ልትሄዱ በማትችሉበትም ቦታ፣ ከእናንተ ምስክራችሁ ወደ አለም ሁሉ ወደ እያንዳንዱ ፍጥረት እንዲሄድ፣ ላኩ።
፷፫ እናም ለሐዋሪያቴ እንዳልኳቸውም፣ ለእናንተም እላለሁ፣ ለእናንተም ይህን ሐዋሪያቴ፣ እንዲሁም የእግዚአብሔር ሊቀ ካህናት ናችሁ፤ እናንተም አባቴ የሰጠኝ ናችሁ፤ ጓደኛዎቼም ናቸሁ፤
፷፬ ስለዚህ፣ ለሐዋሪያቴም እንዳልኳቸው ለእናንተም ደግሜ እላለሁ፣ በቃላቶቻችሁ የሚያምኑት እናም ኃጢአታቸው ይሰረይ ዘንድ በውሀ የሚጠመቁ እያንዳንዱ ነፍሳትም መንፈስ ቅዱስን ይቀበላሉ።
፷፭ እናም ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል—
፷፮ በስሜም ብዙ ድንቅ ስራዎች ይሰራሉ፤
፷፯ በስሜም አጋንንትን ያወጣሉ፤
፷፰ በስሜም የታመሙትን ይፈውሳሉ፤
፷፱ በስሜም የእውሩን አይኖች ያበራሉ፣ እናም የደንቆሮዎችን ጆሮዎች ይከፍታሉ፤
፸ እናም የዲዳውም ምላስ ይናገራል፤
፸፩ እናም ማንም ሰው መርዝ ቢሰጣቸውም አይጎዳቸውም፤
፸፪ እናም የእባብ መርዝም ሊጎዳቸው በእነርሱ ላይ ሀይል አይኖረውም።
፸፫ ነገር ግን፣ በእነዚህ በሚሆኑነገሮች በራሳቸው እንዳይታበዩ፣ ወይም በአለም ፊትም እንዳይናገሩ ትእዛዝ እሰጣቸዋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ጥቅም እና ደህንነት ተሰጥተዋልና።
፸፬ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በቃላቶቻችሁ የማያምኑት፣ እናም መንፈስ ቅዱስን ይቀበሉ ዘንድ በስሜ በውሀ ውስጥ ለኃጢአታቸው ስርየት ያልተጠመቁት፣ ይፈረድባቸዋል፣ እናም እኔ እና አባቴ ወዳለንበት ወደአባቴ መንግስትም አይመጡም።
፸፭ እናም ለእናንተ የተሰጠው ይህ ራዕይ እና ትእዛዝ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ በአለም ሁሉ ላይ የሚሰራ ነው፣ እናም ወንጌሉም ላልተቀበሉት ሁሉም ነው።
፸፮ ነገር ግን፣ መንግስት ለተሰጣቸው ሁሉ በእውነት እላለሁ—ለቀደመው ክፉ ስራቸው ንስሀ ይገቡ ዘንድ፣ ለክፉና ለማያምን ልቦቻቸውም፣ እናም በላኳችሁ ጊዜ ያመጹት በፅዮን ያሉት ወንድሞቻችሁም ይነቀፋ ዘንድ ይህም ከእናንተ ለእነርሱ መሰበክ ይገባል።
፸፯ እና ባልንጀሮቼ፣ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ባልንጀሮቼ ብዬ እጠራችኋለሁና፣ ደግሜም እላችኋለሁ፣ ከእነርሱ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ወንጌልን ለመስበክ በሀይሌ በሚጓዙበት ቀናት እንደነበሩት ባልንጀሮቼ ትሆኑ ዘንድ ይህን ትእዛዝ ለእናንተ መስጠቴ አስፈላጊ ነው፤
፸፰ ሁለት እጀ ጠባብም ይሁን ኮረጆም ወይም ከረጢት እንዲኖራቸው አልፈቀድኩላቸውምና።
፸፱ እነሆ፣ አለምን ትፈትኑ ዘንድ ልኬአችኋለሁ፣ እና ለሠራተኛም ደመወዙ ይገባዋል።
፹ እናም ማንም የሚሄድና ይህን የመንግስትን ወንጌል የሚሰብክ፣ እናም በሁሉም ነገሮች በእምነቱ ጸንቶ የቆመ ሰው፣ በአዕምሮ ወይም በሰውነት፣ በእግርና እጆቹ፣ ወይም መገጣጠሚያዎቹ አይደክሙም ወይም አይዝሉም፤ እናም የራሱም ጠጉር ሳይታወቅ ምድር ላይ አይወድቅም። እናም አይራቡም ወይም አይጠሙም።
፹፩ ስለዚህ፣ ለነገ ምን እንደምትበሉ፣ ምን እንደምትጠጡ፣ ወይም ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ።
፹፪ የሜዳ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ አይደክሙም፣ አይፈትሉም፤ እናም የዓለም መንግሥታት እንኳ በክብራቸው ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አልለበሱም።
፹፫ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።
፹፬ ስለዚህ፣ ነገ ለራሱ ይጨነቅ።
፹፭ እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ ነገር ግን ዘወትር የህይወትን ቃል በአዕምሮዎቻችሁ ውስጥ አከማቹ፣ እና ይህም በዚያች ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰው ተመዝኖ የሚሰጠው ይሰጣችኋል።
፹፮ ስለዚህ፣ ይህ ትእዛዝ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ለአገልግሎት በእግዚአብሔር ለተጠሩት ታማኝ ለሆኑት ሁሉ ስለሆነ፣ የመንግስትን ወንጌል ለማወጅ የሚሄድ ማንም ሰው ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ኮረጆም ወይም ከረጢት አይውሰድ።
፹፯ እነሆ፣ ጻድቅ ላልሆነው ስራዎቻቸው ዓለምን እንድትወቅሱ፣ እና ስለሚመጣው ፍርድም ታስተምሯቸው ዘንድ ልኬአችኋለሁ።
፹፰ እናም የሚቀበሏችሁም ቢሆን፣ እኔም በዚያም እገኛለሁ፣ በፊታችሁም እሄዳለሁና። በቀኛችሁ እና በግራችሁ እሆናለሁ፣ እናም መንፈሴም በልባችሁ ውስጥ ይገኛል፣ እናም ይደግፏቹም ዘንድ መላእክቴ በዙሪያችሁ ይሆናሉ።
፹፱ ማንም የሚቀበላችሁ እኔን ይቀበለኛል፤ እናም እርሱም ይመግባችኋል፣ እናም ያለብሳችኋል፣ እናም ገንዘብም ይሰጣችኋል።
፺ እናም የሚመግባችሁ፣ ወይም የምሚያለብሳችሁ፣ ወይም ገንዘብንም የሚሰጣችሁ፣ በምንም ዋጋው አይጠፋበትም።
፺፩ እናም እነዚህን ነገሮች የማያደርገው እርሱ ደቀ መዛሙርቴ አይደለም፤ በዚህም ደቀመዛሙርቴን ታውቋቸዋላችሁ።
፺፪ ለማይቀበላችሁም፣ ከእርሱ ተለይታችሁ ውጡ፣ እናም በሙቀትም ይሁን በቅዝቀዛ እግሮቻችሁን በውሀ፣ እንዲሁም በንጹ ውሀ አጽዱ፣ እናም ምስክርንም ለሰማይ አባታችሁ አቅርቡ፣ እናም ወደእርሱም ደግማችሁ አትመለሱ።
፺፫ እናም በምትገቡበትም መንደር ወይም ከተማ፣ ይህንኑ አድርጉ።
፺፬ ይህም ቢሆን፣ ተግታችሁ ፈልጉ እናም አትታክቱ፤ እናም እናንተን ወይም ቃላቶቻችሁን፣ ወይም እኔን በመመልከት ያላችሁን ምስክር ለማይቀበል ለዚያ ቤት ወይም መንደር ወይም ከተማ ወዮለት።
፺፭ እናንተን ወይም ቃላቶቻችሁን፣ ወይም እኔን በመመልከት ያላችሁን ምስክር ለማይቀበል ለእዚም ቤት ወይም መንደር ወይም ከተማ ደግሜ ወዮለት እላለሁ።
፺፮ እኔ፣ ሁሉን የሚገዛው፣ ጥፋተኝነታቸውን ለመቅጣት እጆቼን በአህዛብ ላይ አሳርፌአለሁ።
፺፯ እናም መቅሰፍቶችም ይሆናሉ፣ እናም ስራዬን እስከምጨርስ ድረስም አይወሰዱም፣ ይህም በፅድቅ በአጭር ይቆረጣል—
፺፰ የሚቀሩት፣ እንዲሁም ከታናሹ ጀምሮ እስከታላቁ፣ ሁሉ እስከሚያውቁኝ ድረስ፣ እናም በጌታ እውቀትም ይሞላሉ፣ እናም ዓይን ለዓይን ይተያያሉ፣ እናም ድምፃቸውንም ያነሣሉ፥ እናም በአንድነትም ይህን አዲስ መዝሙር እንዲህ በማለት ይዘምራሉ፥
፺፱ ጌታ ፅዮንን ዳግም መልሷል፤ጌታ ሕዝቡ፣ እስራኤልን፣ አድኗል፣በጸጋ በሆነ ምርጫ፣እናም በአባቶቻቸው ቃል ኪዳን፣ይህም በእምነት የተከናወነ ነበር።
፻ ጌታ ህዝቡን ተቤዠእናም ሰይጣንም ታስሯል እና የጊዜ ቀመር አይኖርም።ጌታ ሁሉንም ነገሮች በአንድ ጠቅልሏል።ጌታ ፅዮንን ከላይ መልሶ አምጥቷል።ጌታ ፅዮንንም ከታችም መልሶ አምጥቷል።
፻፩ ምድርም አምጣለች እና ጥንካሬዋንም አምጥታለች፤እውነትም በሆዷ ውስጥ የተመሰረተ ነው፤እና ሰማያትም በእርሷ ላይ ፈገግ ይላሉ፤እናም እርሷም የአምላኳን ክብር ልብስ ለብሳለች፤እርሱም በሕዝቦቹ መካከል ቆሟልና።
፻፪ ክብር፣ እና ሀይል፣ እና ብርታት፣ለአምላካችን ይሁን፤ እርሱም በምህረት፣በፍትህ፣ በጸጋ፣ እና በሰላም የተሞላ ነውና፣ከዘለአለም እስከዘለአለም፣ አሜን።
፻፫ እና ደግሞም፣ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ዘለአለማዊ ወንጌሌን ለማወጅ የሚሄደው እያንዳንዱ ሰው፣ ቤተሰብ ያላቸው ቢሆን፣ እናም የገንዘብ ስጦታን ቢቀበሉ፣ ይህን ጌታ እንደሚመራቸው ለእነርሱ እንዲልኩ ወይም ለእነርሱ ጥቅም ያውሉት ዘንድ አስፈላጊ ነው፣ ይህም መልካም ነውና።
፻፬ እናም ገንዘብ የሚቀበሉት ቤተሰብ የሌላቸውም፣ ለራዕዮች መገለጥ እና መታተም እናም ለፅዮን መመስረት የተቀደሰ ይሆን ዘንድ፣ ወደ በፅዮን ወይም በኦሀዮ ላለ ኤጲስ ቆጶስ ይላኩት።
፻፭ እናም ማንም ሰው ኮት ወይም ሙሉ ልብስን ቢሰጣችሁ፣ አሮጌውን ወስዳችሁ ለደሀው ስጡ፣ እናም በደስታም ሂዱ።
፻፮ እናም በመካከላችሁ አንዱ ሰው በመንፈሱ ጠንካራ ቢሆን፣ በቅንነት እንዲታነጽ፣ ደግሞም ጠንካራ ይሆን ዘንድ፣ ከእርሱ ጋር ደካማ የሆነውን ይውሰድ።
፻፯ ስለዚህ፣ ከእናንተ ጋር በአነስተኛው ክህነት የተሾሙትን ውሰዱ፣ እናም ቀጠሮም ያድርጉ፣ እናም መንገድንም እንዲያዘጋጁላችሁ፣ እናም እናንተ ራሳችሁ ልታከናውኑት የማትችሉትን ቀጠሮ ያሟሉላችሁ ዘንድ በፊታችሁ ስደዷቸው።
፻፰ እነሆ፣ ይህም በቀደሙት ጊዜያት ሐዋሪያቴ ቤተክርስቲያኔን የገነቡበት መንገድ ነው።
፻፱ ስለዚህ፣ እያንዳንዱ ሰው በተሾመበት ይቁም፣ እናም በጥሪውም ያገልግል፤ እናም ራስ ለእግር እግር አስፈላጊ አይደለም አይበለው፤ ምክንያቱም ያለእግር ሰውነት ሊቆም ይቻለዋል?
፻፲ ደግሞም፣ ሁሉም አብረው ይታነጹ ዘንድ፣ አሰራሩም በፍጹም ሆኖ ይቀጥል ዘንድ፣ አካል እያንዳንዱ ብልቶች ያስፈልጉታልና።
፻፲፩ እናም እነሆ፣ ሊቀ ካህናት፣ እና ደግሞም ሽማግሌዎች፣ እና ደግሞም አነስተኛዎቹ ካህናት ይጓዙ ዘንድ ይገባል፤ ነገር ግን ዲያቆናት እና መምህራን ቤተክርስቲያኗን እንዲጠብቁ፣ በቤተክርስቲያኗ የማይጓዙ አገልጋዮች በመሆን እንዲወከሉ ይገባቸዋል።
፻፲፪ እናም ኤጲስ ቆጶሱ፣ ኒወል ኬ ውትኒ፣ ደግሞም በአካባቢው እና በቤተክርስቲያናቱ መካከልም፣ የደሆችን ፍላጎት በመጠበቅ ሀብታሞችን እና ትእቢተኞችን ዝቅ በማድረግ ለመርዳት መጓዝ ይገባዋል።
፻፲፫ ሀላፊነትን እንዲወስድ እና በሚመራው መንገድ ስጋዊ ሀላፊነትን እንዲያከናውን ወኪልንም መጥራት ይገባዋል።
፻፲፬ ይህም ቢሆን፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወደ ኒው ዮርክ ከተማ፣ ደግሞም ወደ አልበኒ ከተማ፣ እናም ደግሞም ወደ ቦስተን ከተማ ይሂድ፣ እናም የእነዚህ ከተማ ሰዎችንም በወንጌሉ ድምጾች፣ በጎላ ድምፅ፣ እነዚህን ነገሮች ቢቃወሙ ስለሚጠብቃቸው ውድመት እና የከፋ ጥፋት ያስጠንቅቅ።
፻፲፭ እነዚህን ነገሮች ቢቃወሙ የፍርዳቸው ሰአት ደርሶአልና፣ እናም ቤታቸውም በውድመት ይቀርላቸዋል።
፻፲፮ በእኔ ይመን እናም እርሱም አያፍርም፤ እናም የራሱም ጠጉር ሳይታወቅ ምድር ላይ አይወድቅም።
፻፲፯ እናም እውነት እላችኋለሁ፣ የቀራችሁት አገልጋዮቼ፣ ጉዳያችሁ እንደሚፈቅድላችሁ፣ በተለያዩት ጥሪዎቻችሁ፣ ወደታላቅ እና ታዋቂ ከተማዎች እና መንደሮች፣ በፅድቅ አለምን ጻድቅ ላልሆኑ እና እግዚአብሔርን ለማያመልኩ ስራዎቻቸውን እየወቀሳችሁ፣ በግልፅ እና በሚገባ ሁኔታ የመጨረሻ ቀናት የጥፋት ርኩሰትን በመግለፅ ሂዱ።
፻፲፰ በእናንተም መንግስቶቻቸውን እደመስሳቸዋለሁ፤ ምድርን ማናውጥ ብቻ ሳይሆን፣ ኮከባዊውን ሰማያትንም አናውጣለሁ ይላል ሁሉን የሚገዛው አምላክ።
፻፲፱ እኔ ጌታ የሰማይን ሀይላት ለመጠቀም እጆቼን እዘረጋለሁና፤ አሁን ልታዩት አትችሉም፣ ነገር ግን ከትንሽ ጊዜ በኋላ ታዩታላችሁ፣ እናም እኔ እንደሆንኩኝ፣ እናም በህዝቤ መካከል ለመንገስ እንደምመጣም ታውቃላችሁ።
፻፳ እኔ አልፋና ኦሜጋ፣ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው፣ ነኝ። አሜን።